Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅመስከረም 17 ቀን 2010 ዓ.ም. የመስቀል በዓል በመስቀል አደባባይ ሲከበር

መስከረም 17 ቀን 2010 ዓ.ም. የመስቀል በዓል በመስቀል አደባባይ ሲከበር

ቀን:

መስከረም 17 ቀን 2010 ዓ.ም. የመስቀል በዓል በመስቀል አደባባይ ሲከበር ከአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ 2 ሺሕ አገልጋዮች ፅናፅን፣ መቋሚያና ከበሮ ይዘው በዓሉን በወረብ አድምቀውታል፡፡ ምዕመኑም ጧፍ በመለኮስ የደመራውን ምሽት አስውበውታል፡፡ በዕለቱ የውጭ አገር ዜጎችም ነጠላቸውን ጣል አድርገው ጧፍ አብርተው ታይተዋል

ህልሜ

ኑሮን መኖር እንጂ ለሞት አላስብም

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ህልሜ ዕውን ይሆናል አላንገራግርም

ያልተፈታው ህልሜ ገና እኮ ሽል ነው

ይሳካል አምናለሁ እኔ እማልመው

ድንቅ እኮ ነው ህልሜ በውኑ ሲፈታ

ቅዠት ሆኖ አይቀርም እንደ ንፋስ ባፍታ

እተጋለሁ በቅርብ እንዲፈታ

የእኔ ልፋት ትጋት ከቅንነት ጋራ

ህልሜን ይፈታዋል ይወጣል ተራራ

  • ንብረት ተካ፣ (የእኔ ባለ ውለታ)፣ (2009)

* * *

በረራ የተስተጓጎለባት ሌሊቱን በሙሉ በዳንስ አሳለፈች

ካሰቡበት ቦታ ፈጥነው ለመድረስ የአየር በረራን መርጠው፣ ትኬቱንም ቆርጠው በሰዓቱ ከአየር መንገዱ ለመድረስ ቢጥሩም ሳይሳካልዎት ቀርቶ በረራው ያመልጥዎት ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜ በንዴት ብው ብለው የሚያደርጉትንም ያጣሉ፣ በየዴስኩ እየሄዱ ቀጣዩ በረራ መቼ እንደሆነ ያጣራሉ፣ መፍትሔም ፍለጋ ይሯሯጣሉ፡፡ በማርፈድዎ ምክንያት አንድ ሙሉ ሌሊት እንዲያሳልፉ ቢገደዱስ ምን ያደርጉ ይሆን?

ማሺድ ማዞጄ የተባለች ተጓዥ ለቀጣይ በረራዋ በሰሜን ካሮሊና ከሚገኘው ቻርሎቴ አየር ማረፊያ ቀድማ መገኘት ነበረባት፡፡ ሆኖም በማርፈዷ ይህ አልተሳካም፡፡ በመሆኑም አንድ ሌሊት ማሳለፍ ነበረባት፡፡ ዩኤስኤ ቱዴይ እንዳሰፈረው፣ ማዞጄ መናደድን አልመረጠችም፡፡ ይልቁንም የሊዩኔል ሪቼን ‹‹ኦልናይት ሎንግ›› ሙዚቃ እዚያው የተሳፋሪዎቹ የበረራ ጊዜ መጠባበቂያ ሥፍራ በመክፈት ሌሊቱን በዳንስ ነበር ያሳለፈችው፡፡ በአየር መንገዱ የነበሩት ጥቂት ተጓዦች አብረዋት እንዲደንሱም ስትጋብዝ ነበር ተብሏል፡፡ ንዴትን በዳንስ እንዲሉ!በረራ የተስተጓጎለባት ሌሊቱን በሙሉ በዳንስ አሳለፈች

* * *

ፊትን ውድ በሆነ ፐርል ማስዋብ

ፐርል ከዓሳ ቅርፊት የሚገኝና ውድ የሆኑ ጌጣጌጦችን ለመስራት የሚያገለግል ነው፡፡ ሙሽራን በፐርል ማስዋብም የተለመደ ነው፡፡ ለእንገት፣ ለጣት፣ ለእጅና እግር እንዲሁም ለፀጉር ማስዋቢያ የሚውሉ ጌጣጌጦችም ከፐርል ይሰራሉ፡፡ ሰሞኑን ኤም ኤስ ኤን ይዞት የወጣው ዘገባ፣ ሴቶች ፊታቸውን በፐርል ማስዋብ መጀመራቸውን ያሳያል፡፡ ንቅሳትና የተለያዩ የመዋቢያ ቅባቶችን መጠቀም የተለመደ ሲሆን፣ አሁን ፊትን በፐርል ማስዋብ አንድ አማራጭ ሆኖ ቀርቧል፡፡ ፐርሉን በማጣበቂያ ከቅንድባቸው፣ ከንፈራቸው፣ አፍንጫቸውና ግንባራቸው ላይ በመለጠፍ እየተዋቡበት መሆኑን ዘገባው ያሳል፡፡

* * *

ምሳ ለማግኘት ያለፉትን 14 ዓመታት በሙሉ ቀብር የሄዱ አዛውንት

የ65 ዓመቷ ተሬሳ ዶይል ያለፉትን 14 ዓመታት የማያውቁትን ሰው ቀብር ሁሉ ታድመዋል፡፡ ሚረር እንዳሰፈረው፣ ዶይል ሁሌም በብስክሌታቸው ከአቅራቢያቸው ከሚገኝ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ለቀብር የሚሄዱትን ሁሉ ይከተሉ ነበር፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ምሳ ማግኘት ነው፡፡

በብሪክሻየር የሚገኘው ሆሊ ሪዲሚር ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ኖሃ ኮኖሌ፣ ‹‹ለምን ሁሌ ቀብር ትመጫለሽ ብዬ ስጠይቃት ‹ይኼ ግዴታዬ ነው› ብላኛለች፡፡ በመሆኑም ከቤተ ክርስቲያን ላግዳት አልችልም›› ብለዋል፡፡

ከቀብር በኋላ በሚኖር ግብዣም ያለማንም ጥሪ ተገኝተው ምሳ በልተው እንደሚሄዱ ተናግረዋል፡፡ ምሳ ለማግኘት ያለፉትን 14 ዓመታት በሙሉ ቀብር የሄዱ አዛውንት  

* * *

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...