Tuesday, February 27, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

አይኤምኤፍ በኢኮኖሚው ላይ የተጋረጡ የቅርብ ጊዜ ሥጋቶችን በምክረ ሐሳቡ ጠቆመ

ተዛማጅ ፅሁፎች

  • ተስፋ ሰጪ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በመካከለኛው ጊዜ እንደሚኖር ተንብይዋል

የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የቅርብ ጊዜ (ዓመታት) ሥጋቶች ናቸው ያላቸውን በመለየት፣ መንግሥት የፖሊሲ ዕርምጃዎችን ከወዲሁ መውሰድ እንዲጀምር ምክረ ሐሳቡን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አቀረበ፡፡

በሚስተር ጁሊዩ ኢስኮላኖ የተመራው የአይኤምኤፍ የባለሙያዎች ቡድን ከመስከረም 3 ቀን እስከ መስከረም 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በመገኘት፣ ያለፈው በጀት ዓመት የአገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ግምገማ አድርጓል፡፡ በዚህ መሠረት የቅርብና የመካከለኛ ጊዜ ኢኮኖሚው መፃኢ ተስፋዎችንና ሥጋቶችን በመዳሰስ ነው፣ ምክረ ሐሳቡን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምና ለሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ያቀረበው፡፡

ይህንን አስመልክቶ አይኤምኤፍ ባወጣው መግለጫ መሠረትም የውጭ ብድር የዕዳ ጫናና ተያያዥ ሥጋቶች፣ እንዲሁም አገሪቱ በአሁኑ ወቅት የገጠማት የክፍያ ሚዛን ትልቁ ክፍል (Current Account) ጉድለት ለቀጣዮቹ አጭር ዓመታት ጎልተው በመውጣት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን እንደሚገዳደሩት ጠቁሟል፡፡ በመሆኑም አገሪቱ ላለፉት ዓመታት በመሠረተ ልማቶች ላይ ያፈሰሰችው ኢንቨስትመንት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ ማምጣት እስኪጀምር፣ እየተገነቡ ያሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በሁለት እግራቸው ቆመው ኤክስፖርት ማድረግ እስኪጀምሩ ድረስ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፖሊሲ አማራጮችን በመጠቀም የተዛባውን የወጪ ንግድ ማስተካከልና የውጭ ዕዳን መቀነስ እንደሚገባ ምክረ ሐሳባቸውን አቅርቧል፡፡

ይህንንም በተሳካ ሁኔታ ለመፈጸም የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል እንደገባው ጥብቅ የበጀት ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባው፣ በተጨማሪም በመንግሥት ወጪ በተለይም በውጭ ብድር የሚገነቡ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ማዘግየት ይገባዋል በማለት አይኤምኤፍ ምክረ ሐሳቡውን አቅርቧል፡፡

በ2009 የበጀት ዓመት የኢኮኖሚ አፈጻጸምን በተመለከተ አይኤምኤፍ ባደረገው ግምገማ፣ ኢኮኖሚው በዘጠኝ በመቶ ማደጉን አስታውቆ ይህም በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ውስጣዊና ውጫዊ መሰናክሎች ውስጥ የተገኘ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡

ለአብነት ያህልም በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ድርቅ በድጋሚ ባገረሸበትና የዓለም የግብርና ምርቶች ዋጋ ባሽቆለቆለበት ሁኔታ ውስጥ የተገኘ አፈጻጸም መሆኑን ጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም መንግሥት ጥብቅ የሆነ የበጀት ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረጉ ከተፈቀደው የበጀት ጉድለት በታች፣ ማለትም ዓመታዊ አጠቃላይ ምርቱን (ጂዲፒ) 2.5 በመቶ ብቻ ሆኖ መፈጸሙን እንደ ጥንካሬ አውስቷል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች