Saturday, November 26, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትኢትዮጵያን የሚያካትተው የዞን አምስት ኦሊምፒክ ማኅበራት ፕሬዚዳንትነትን ዑጋንዳ ተረከበች

  ኢትዮጵያን የሚያካትተው የዞን አምስት ኦሊምፒክ ማኅበራት ፕሬዚዳንትነትን ዑጋንዳ ተረከበች

  ቀን:

  የዑጋንዳ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዊልያም ብሊክ የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) የዞን አምስት ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ፡፡

  በካይሮ በተካሄደው ጉባኤ ለሁለት ዓመት ከተመረጡት ብሊክ ሌላ የቅርብ ተቀናቃኛቸው የነበሩትና መጨረሻ ደቂቃ ላይ ከተፎካካሪነት የወጡት የግብፁ ጋሴር ሪያድ ምክትል ፕሬዚዳንትነትን ማግኘታቸውን ካዎዎ ስፖርት በድረ ገጹ ዘግቧል፡፡

  ብሊክ ከምርጫው በኋላ በዞን አምስት የኦሊምፒክ እንቅስቃሴን ለማስፋፋትና የአኖካን ጨዋታዎች እውን ለማድረግ ግንባር ቀደም እንደሚሆኑ ቃል ገብተዋል፡፡ የኬንያ ፍራንሲስ ፖል ጠቅላይ ጸሐፊ፣ የታንዛኒያው ራሺድ ጉላም ዓቃቤ ንዋይ ሆነው ሲመርጡ፣ ለሥራ አስፈጻሚ አባልነትም የደቡብ ሱዳኑ ጁማ ለሚ እና የሱዳኑ ሐሰን ሃሺም ኮልጃይ ተመርጠዋል፡፡

  ብሊክ የዑጋንዳ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት የሆኑት ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ ሲሆን ዘንድሮም ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጠዋል፡፡

  የአኖካ ዞን አምስት አገሮች ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ጂቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዑጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲና ግብፅ ናቸው፡፡

   

  በአጭሩ አኖካ የሚባለው የአህጉሪቱ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር በ1970 እንዲመሠረት ቁልፍ ሚና የነበራት ኢትዮጵያ፣ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ ስታስተናግድ በተደረገው ምርጫ በወቅቱ የስፖርት ኮሚሽነርና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ፀጋው አየለ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል፡፡ የኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ አባሏ ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማይም ከ2001 ዓ.ም. ጀምሮ የአኖካ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል መሆናቸው ይታወቃል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የትርፍ መጠኑን በ127 በመቶ ያሳደገው አቢሲኒያ ባንክ ካፒታሉን በ2.5 ቢሊዮን ብር እንዲያድግ ወሰነ

  የአቢሲኒያ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩ  ካፒታል በ2.5 ቢሊዮን ብር...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ወሰነ

  የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2015...

  ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ያገኘው ፔይሊንክ አክሲዮን ማህበር ምሥረታውን አካሄደ

  ከገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆነ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ለመተግበር ያቀደው...