Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኤርትራ በአሜሪካ በተጣለባት የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ሳቢያ እሰጥ አገባ ጀመረች

ኤርትራ በአሜሪካ በተጣለባት የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ሳቢያ እሰጥ አገባ ጀመረች

ቀን:

የኤርትራ መንግሥት በአሜሪካ በተጣለበት የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ምክንያት፣ የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የሚያጣጥል መግለጫ አወጣ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የፀጥታው ምክር ቤት የማዕቀብ ቁጥጥር ኮሚቴ የካቲት 7 ቀን 2009 ዓ.ም. ያጠናቀረው ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ ከሰሜን ኮሪያ ተገዝቶ በቻይና በኩል ወደ ኤርትራ በመጓጓዝ ላይ የነበረው ኮንቴይነር የተከለከሉ የጦር መሣሪያ ቁሳቁሶች ተገኝተውበታል፡፡

የጦር መሣሪያ ቁሳቁሶች የያዘው ኮንቴይነር ኤሪቴክ ኮምፓይተር ጥገናና ኮሙዩኒኬሽንስ ቴክኖሎጂ ለተባለውና ተቀማጭነቱ አስመራ ለሆነው ኃላፊቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ባለቤትነት የሚጓጓዝ መሆኑ ቢገለጽም፣ የፀጥታው ምክር ቤት የማዕቀብ ጉዳዮች ቁጥጥር ኮሚቴ (ፓነል) ግን የተመድን የጦር መሣሪያ ክልከላ ሕግ የሚጥስና ሕገወጥ መሆኑን ደርሶበታል፡፡

የተመድ ሪፖርት ከወጣ በኋላ ሰሞኑን የአሜሪካ መንግሥት በኤርትራ ላይ የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ጥሏል፡፡ ማዕቀቡን ለመጣል ምክንያት የሆነው ኮንቴይነር ውስጥ ከተገኙት የጦር መሣሪያ ቁሳቁሶች፣ የጦር ሜዳ ሬዲዮኖች የያዙ 45 ሳጥኖች መገኘታቸው ነው፡፡

የተመድ የቁጥጥር ኮሚቴ ባለሙያዎች ድርጊቱ ለሁለተኛ ጊዜ የተፈጸመ መሆኑን ያረጋገጡ ሲሆን፣ ኤርትራ በተመድ ማዕቀብ ከተጣለባት ከሰሜን ኮሪያ የምታካሂደው ወታደራዊ ትብብርና የጦር መሣሪያ ግዢ አካል ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ኮሚቴው በጥርጣሬ የያዛቸው የጦር መሣሪያ ቁሳቁሶች ግሎኮም በተባለ ድርጅት የተመረቱ መሆናቸውን የሚገልጽ ሲሆን፣ ጉዳዩን ለማጣራት የቁጥጥር ኮሚቴው ደብዳቤ በጻፈበት ቅፅበት ድርጅቱ ድረ ገጹን መዝጋቱ በሪፖርቱ ተጠቁሟል፡፡

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ፣ ዕርምጃው የተሳሳተ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ውጤት እንደሆነ ገልጿል፡፡ ቀደም ሲል የአሜሪካ መንግሥት በኤርትራ ላይ የሚያካሂደው የማጥላላትና የስም ማጥፋት ዘመቻ የቀጠለ ነውም ብሏል፡፡ የአሁኑን የጦር መሣሪያ ማዕቀብም ተችቷል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2009 የኤርትራ መንግሥት አልሸባብን መደገፉን አጣሪ ኮሚቴው ባቀረበው ሪፖርት መሠረት፣ የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ማዕቀብ የጣለ ሲሆን፣ ለሁለተኛና ለሦስተኛ ጊዜ ማራዘሙ ይታወሳል፡፡

ሪፖርተር ጉዳዩን በተመለከተ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትን ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...