አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 10 መካከለኛ ቀጠን ያለ ቃርያ
- 2 የሾርባ ማንኪያ በጣም የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
- 2 የሾርባ ማንኪያ ፍሬውና ውኃው ወጥቶ የደቀቀ ቲማቲም
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ነጭ ቅመም
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ዘይት
አዘገጃጀት
- ቀይ ሽንኩርቱን፣ ቲማቲሙን፣ ነጭ ቅመሙንና ጨውን ቀላቅሎ በዘይት ለብለብ ማድረግ
- ቃርያውን በጥንቃቄ መሰንጠቅና ፍሬውን ማውጣት
- የተዘጋጀውን ስንግ በሻይ ማንኪያና በትንሽ ሲላዋ ቃርያው ውስጥ መጠቅጠቅ
- ሲፈለግ ለገበታ ማቅረብ
- ደብረወርቅ አባተ (ሱሼፍ) “የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት” (2003)