Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተቀምጧል

የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተቀምጧል

ቀን:

የገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ አባል ድርጅት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ፣ በመቐሌ ከተማ ማክሰኞ መስከረም 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ተጀመረ፡፡

ከሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በተጨማሪ ነባር አመራር አባላት ጭምር እየተሳተፉበት ነው በተባለው ለአራት ቀናት ቆይታ በሚያደርገው በዚህ ስብሰባ፣ ያለፈው ዓመት ዋነኛ የሚባሉ አፈጻጸሞች እንደሚገመገሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በትግራይ ክልልም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ውይይት ከመደረጉም በላይ፣ በተለይ ባለፈው ዓመት ተግባራዊ የተደረገው ጥልቅ ተሃድሶ አፈጻጸሙ ከእነ ውጤቶቹ በዝርዝር እንደሚታዩና የ2010 ዓ.ም. ዕቅድም ላይ ውይይት እንደሚደረግ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በገዥው ፓርቲም ሆነ በመንግሥት ላይ እየተነሱ ባሉ ተቃውሞዎችና መሠረታዊ በሚባሉ የሕዝብ ጥያቄዎች ላይ ጥልቀት ያለው ውይይት እንደሚደረግ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ 45 አባላት ያሉት ሲሆን፣ በዚህ ስብሰባ የመጪው 13ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች እንደሚያደራጅ ይጠበቃል፡፡

የሕወሓት ሊቀመንበር አቶ ዓባይ ወልዱና ምክትላቸው ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) በጋራ እየመሩት ባለው የማዕከላዊ ኮሜቲ ስብሰባ ላይ አቶ ስብሐት ነጋ፣ አቶ ሥዩም መስፍንና አቶ ዓባይ ፀሐዬን የመሳሰሉ ነባር አመራሮች በታዛቢነት መገኘታቸው ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...