Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ዙፋን ዘንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ

ትኩስ ፅሁፎች

ይህ ልዩና የተጌጠ ዙፋን (የክብር መቀመጫ) ከ1909-1922 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ ነበር፡፡ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፋሺስት ኢጣሊያ ተዘርፎ ከተወሰደ በኋላ በ1964 ዓ.ም. ወደአገሩ ተመልሶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ተቀምጧል፡፡

ለቡጊ

በግር ጣራ መርገጥ

ሙዚቃ ሲጋልብ መውጣት መውረድ

መፍረጥ፡፡

      ዓይኔን ማገላበጥ

መርበትበት መንቀጥቀጥ

መላጋት መንገድገድ እንደሰከረ ሰው

የናፈቀኝ ይኼ ነው፡፡

ተነስቼ ልዝለል

            ቡጊ ቡጊ ልበል፡፡

      ቡጊ-ቡጊ-ቡጊ

            ከበሮ ሲያጋፋት ሙዚቃ ሲያናፋ

            ልብሴን ጥዬ ልጥፋ

            ልራቆት አብጄ

            ልብረር ካለም ሄጄ፡፡

      ሙዚቃ በጥላው ይምጣ ይሸፍነኝ

      ሁሉንም ያስረሳኝ፡፡

      እንደሳት ቦግ ቦግ

      መውለብለብ መንተግተግ

      መቃጠል መሞቅ ነው

            ይኼ ነው ዳንሱ ይህ ነው፡፡

      ልቤን ያነሳኛል

      ዛር ይሰፍርብኛል፡፡

  • ገብረ ክርስቶስ ደስታ

****

ቀልዳ ቀልድ

 

ልጅ ‹‹አባዬ፤ በጣም አዋቂ ማን ነው፡- አባት ወይስ ልጅ?››

አባት ‹‹አባት እንጂ››

ልጅ ‹‹አይደለም፤ ልጅ ነው በጣም አዋቂ››

አባት ‹‹እንዴት?››

ልጅ ‹‹በእንፋሎት የሚሠራውን ሞተር ማን ፈለሰፈው?››

አባት ‹‹ጀምስ ዋስ››

ልጅ ‹‹ታዲያ ለምን አባቱ አልፈለሰፈውም?››

* * *

አንድ ወኔው በድንገት የከዳው ወታደር ወደኋላ ሲሸሽ አንድ መኮንን ያስቆመውና ‹‹ወዴት ነው እባክህ እንደዚህ የምትፈረጥጠው?›› ቢለው ‹‹ምን ያገባሃል? ይልቅስ ዘወር በል ከፊቴ›› ይለዋል፡፡ መኮንኑም ‹‹ከማን ጋር እንደምትነጋገር ታውቃለህ? እኔ ጄነራል እኮ ነኝ›› አለው፡፡ ወታደሩም ‹‹የፈጣሪ ያለህ ይህን ያህል ወደ ኋላ ሸሽቻለሁ ማለት ነው?›› ብሎ መለሰ ይባላል፡፡

* * *

ሒሳብ መምህር ክፍል ውስጥ ሲያስተምሩ ‹‹የሜዳው ርዝመት 200 ሜትር ነው፡፡ የባቡሩ ፍጥነት 100 ኪሎ ሜትር ነው፤ የእኔ ዕድሜ ስንት ነው?›› የጥያቄውን አደናጋሪነት የተመለከተው ጐበዝ ተማሪ እጁን አውጥቶ ‹‹50 ዓመትዎ ነው መምህር›› አለ፡፡ መልሱ ትክክል ነበርና መምህሩ ተደንቀው እንዴት አሰላኸው ቢሉት ‹‹ቀላል ነው መምህር ታላቅ ወንድሜ 25 ዓመቱ ነው፤ ሰው ሁሉ ግን ግማሽ እብድ ይለዋል›› አላቸው፡፡

– መጽሔተ ሪፖርተር (1990)

* * *

ሆዳምነት

የዕውቀትን ብርሃን በውስጡ ማየት ትችል ዘንድ ሆድክን ባዶ አድርገው፤ ከርስህ እስከ እልቀትህ ቢሞላ ጥበብ ትርቅሃለች፡፡ ምንም እንኳን ምግብ ለሕይወት የደስታ ምንጭ ቢሆንም ከመጠን በላይ ከተበላ ስቃይ ያመጣል፡፡ ሳይርብህ መዓዛው የሚያውድ ጤናማ ምግብ ብትበላ አውኮ ያስተፋሃል፡፡ በራበህ ጊዜ ደረቅ ዳቦ በመጠኑ ብትበላ ግን ልክ መዓዛው የሚያውድ ጣፋጭ ምግብ ሆኖ ይሰማሃል፡፡

  • ሆድ ከልክ ላለፈ ጣፋጭ ነገሮች ከልክ ያለፈ ጥላቻ አለው፡፡ (ዊልያም ሸክስፒር)

ሰው መጥኖ የመብላት ልማድ ካለው በክፉ ቀን ርሀብን ይቋቋማል፡፡ በቅንጦት ጊዜ ለመብል የኖረ በችግር ቀን ቀድሞ ይሞታል፡፡ ምግብ የሚበላው ሕይወትን ለማኖርና አምላክን ለማመስገን ነው፤ አንተ ግን ሰው ለመብላት ብቻ የሚኖር ይመስልሀል፡፡

  • ለመኖር ብላ እንጂ ለመብላት አትኑር፡፡ (ማርክስ ሲዘሮ) ዘወትር ሲበላ የኖረ የከርስ ምድጃ በችግር ቀን መከራ ያወርዳል፡፡

ከርስ የእጆች መጠፈሪያ ሽቦ፣ የእግር ማሠሪያ ሰንሰለት ነው፡፡ ለሆዱ ተገዥ የሆነ ሰው ለአምልኮ ጊዜ የለውም፡፡ እስከ እልቅትህ ከልክ በላይ፣ በተቃራኒውም ከመጠን ያነሰ አትብላ፤ አንድም በቁንጣን ያለበለዚያም በድካም ትሞታለህና፡፡

ሆድ አምላኩ ለሁለት ሌሊቶች እንቅልፍ አይወስደውም፡፡ እነዚህም አንደኛው ሌሊት በበላው ምግብ ተጨንቆ ሲንፈራገጥ የሚያድርበት፤ ሁለተኛው ሆዱን እንዴት እንደሚሞላ ሲያሰላስል የሚያነጋበት ሌሊት ናቸው፡፡

ሆዳሞች ወጥ ቤታቸው ፀሎት ቤታቸው፣ ምግብ አብሳያቸው ነፍስ አባታቸው፣ ገበታቸው መቅደሳቸው፣ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፡፡ (ቻርልስ ባክ)

  • መሀመድ ካዚም ከምራን (ትርጉም በባይለየኝ ጣሰው) ‹‹የሰዓዲ ጥበቦች፡ ጎለስታንና ቡስታን›› (2004)

***

የአካልን ውስጣዊ ዑደት የሚቆጣጠረውን ሥርዓት ያገኙት የኖቤል አሸናፊዎች

የዘንድሮውን የኖቤል የሕክምና ዘርፍ ሽልማትን አሜሪካውያኑ (ፎቶ ከግራ) ጄፍሪ ሆል፣ ማይክል ሮስባሽ እና ማይክል ዳብልዩ ያንግ አሸናፊ ሆኑ፡፡ የስዊድን የሳይንስ ሮያል አካዴሚ እንደገለጸው፣ አሸናፊሆኑት የሰው ልጅ አካል ውስጣዊ ዑደት የሚቆጣጠረውን ሞሌኪውላር ሲስተምን በማግኘታቸው ነው፡፡  ይፋዊ የሽልማቱ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓትታኅሣሥ መባቻ  በስቶክሆልም ከተማ እንደሚካሄድ ዶቸቨሌ ዘግቧል። የአካልን ውስጣዊ ዑደት የሚቆጣጠረውን ሥርዓት ያገኙት የኖቤል አሸናፊዎች

 

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች