Tuesday, October 4, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዝንቅየ51 ዓመቱ የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ

  የ51 ዓመቱ የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ

  ቀን:

  በየዓመቱ መስከረም 17 ቀን የሚከበረው የመስቀል በዓል የሚታጀበው በሚለኮሰው ደመራ ነው፡፡ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን (1923-1967) በአዲስ አበባ በዓሉ ከመንፈሳዊነቱ በተጨማሪ ባህላዊ ገጽታውም ጎልቶ ይታያል፡፡ በ1959 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ ከነበረው ልዩ ልዩ መሰናዶ አንዱ በዋዜማው የመንግሥት ሠራተኞች ምዕመናን ባህላዊ እጀ ጠባብ አልባሳትን ተላብሰውና የሚንቦለቦል ችቦ ይዘው በንጉሠ ነገሥቱና በቅዱስ ፓትርያርኩ ፊት ያልፉ እንደነበር አንዱ ማሳያ ይህ ፎቶ ነው፡፡

  • ሔኖክ መደብር

  ***

  ግጥሜ

  እንደው ተሻምቼ

  የውስጤን ስነግረው የማይሰለቸኝ

  ወረኛ ነሽ ኤጭ የማይለኝ

  አንድ ዘመድ አለኝ

  ሀሁን አጣምሬ ፊደሌን ቀምሬ

  ቃላት አባዝቼ ስንኝ አዋግቼ

  ቅኔን አሰምቼ ብዕሬን አንግቼ

  ግጥሜን እጭራለሁ ከውስጤ አውጥቼ

  እሷው ናት ሕይወቴ የዘላለም ሀብቴ

  ስደሰት ስከፋ ቆማ ለሕይወቴ

  ለሊት ተጨንቄ ከእንቅልፌ ስነቃ

  • ንብረት ተካ ‹‹የእኔ ባለ ውለታ›› (2009)    

  *********

  ‹‹ኦክቶበርፌስት››

  ‹‹ኦክቶበርፌስት›› በባቫሪያ ግዛት በሚገኘው የጀርመን ዋና ከተማ ሙኒክ እ.ኤ.አ. ከ1810 ጀምሮ የሚከበር የቢራ ፌስቲቫል ነው፡፡ በዓለም ትልቁ የመጠጥ ፌስቲቫል ሲሆን፣ ከመስከረም ማብቂያ እስከ ጥቅምት የመጀመሪያው ሳምንትም ይከበራል፡፡

  ‹‹ኦክቶበርፌስት›› ማለትም በስድስት ታዋቂ የጀርመን ቢራ ጠማቂዎች የሚዘጋጅና በዚሁ የንግድ ስም የሚጠራ ሲሆን፣ የጠመቃ ጊዜውም የፈረንጆቹ ዓመት በገባ ከሦስተኛው ወር (ማርች) ጀምሮ ነው፡፡ የፈረንጆቹ የሙቀት ጊዜ (ሰመር) እስኪያበቃም ቀስ እያለ እንዲፈላ ተደርጎ፣ ሰመር አልቆ ቅዝቃዜው ከመግባቱ በፊት ለኦክቶበርፌስት ፌስቲቫል በገፍ ይቀርባል፡፡ የቢራው ቀለም በተለይ በቀደሙት ጊዜያት ጥቁር የነበረ ሲሆን፣ ከ1872 ወዲህ ደግሞ አምበር ሬድ (ደማቅ ቀይ) ወደ ፌስቲቫሉ ገብቷል፡፡ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ ደግሞ ፈዘዝ ያለ ቀለም ያለው ቢራ መቅረብ ጀምሯል፡፡ እስካሁንም ድረስ የተወሰኑ የሙኒክ ቢራ አቅራቢዎች ጥቁር ቢራ የሚያቀርቡ ቢሆንም፣ ከ1990 ወዲህ ለኦክቶበርፌስት በብዛት የሚቀርበው ቢራ ወርቃማ ነው፡፡

  በ2013 በነበረው ፌስቲቫል 7.7 ሚሊዮን ሊትር ቢራ ተጠጥቷል፡፡ ኦክቶበርፌስት በጀርመን፣ በለንደንና በሌሎች ከተሞችም በየዓመቱ መከበር ጀምሯል፡፡ በቢራና በተለያዩ ምግቦች በሚደምቀው ፌስቲቫል፣ ቢራ ለማይጠጡ ለስላሳ መጠጦችና ወይንም ይቀርባል፡፡

  ኦክቶበርፌስትን በሚያከብሩ አካባቢዎች የተሳታፊ ቁጥር ቢለያይም፣ በጀርመን ሙኒክ በሚካሄደው ፌስቲቫል ከስድስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች እንደሚታደሙ ቱዴይ በድረ ገጹ አስፍሯል፡፡

  ‹‹ኦክቶበርፌስት››

   

  ሕይወት የታደገ አይፎን

  የአገራችን ሰዎች ‹‹ቀን ካልደረሰ›› ይላሉ፤ ምንም ቢመጣ ሰው ያለ ቀኑ እንደማይሞት ለመግለጽ በላስ ቬጋስ የመኸር (ሃርቨስት) ሙዚቃ ፌስቲቫል ላይ በመታደም የነበረች ሴት ሕይወት በአይፎን ምክንያት መትረፏም ‹‹ቀን ካልደረሰ›› ያስብላል፡፡ ሜትሮ ዩኬ እንደዘገበው፣ ሴትዮዋ ከማንዳላ ቤይ ሆቴል ላይ የሚርከፈከፈው ጥይት ለማምለጥ በመሮጥ ላይ ነበረች፡፡ የዕድል ነገር ሆኖ ከተርከፈከፈው ጥይት አንዱ እሷ ላይ ሳይሆን አይፎንዋ (የእጅ ስልክ) ላይ በማረፉ ከጉዳት/ሞት ተርፋለች፡፡

  የ64 ዓመቱ ሚሊየነር ስቴፈን ፓድዶክ በፈጸመው ጭፍጨፋ 59 ሞተው 527 ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወቃል፡፡

  ሕይወት የታደገ አይፎን

                  

  የኢንዶኔዥያዊው ከዘንዶ ጋር መደባደብ

  በፓልም ዘይት እርሻ ውስጥ ጠባቂ የሆነው ሮበርት ናባባን ከሥራው ወደቤቱ ሲሄድ ዘንዶ መንገድ ላይ ተጋድሞ  ያጋጥመዋል፡፡ በወቅቱም ሰዎች በሥፍራው ማለፍ አቅቷቸው ቆመው ነበር፡፡

  በሰሜናዊ ምዕራብ ኢንዶኔዥያ ‹‹ኢንድራግሪ ሁሉ›› ከተባለው ከተማ የዘንዶው መጋደም ያስቸገራቸውን ሰዎች ለመርዳትም ይቀላቀላል፡፡ ዘሎ ዘንዶውን ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፡፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ከዘንዶው ጋር ከተደባደበ በኋላም ዘንዶውን ይገድለዋል፡፡ ሜትሮ ዩኬ እንደሚለው፣ ናባባን እጆቹን በዘንዶው ንክሻ የተጎዳ ሲሆን፣ በሆስፒታል እየታከመም ነው፡፡ 23 ኢንች የሚረዝመውን ዘንዶው እንዴትና በምን እንደገደለው ግን ማወቅ አልተቻለም፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎችም ዘንዶውን በገመድ ጎትተው ግንድ ላይ ሰቅለውት በምስል ታይቷል፡፡ ሕፃናትም ተንጠልጥለው ሲጫወቱበት እንዲሁ፡፡

  የኢንዶኔዥያዊው ከዘንዶ ጋር መደባደብ

  በ38 ሚልዮን ዶላር የጨረታ ዋጋ የተሸጠው የቻይና ሳህን

  ‹‹ሩ ዌር›› ይሉታል፡፡ በቻይና ከአንድ ሺሕ ዓመት በፊት በነበረው በሶንግ ዘመነ መንግሥት ከሸክላ ይሠራ የነበረ የቤት ቁሳቁስ መገለጫ ነው፡፡ ታዲያ በዚያ ዘመን የነበሩ እውነተኛ የሸክላ ዕቃዎችን ማግኘት በተለይ ለተጫራቾች ፈተና ነው፡፡ ቢቢሲ እንዳሠፈረው፣ ግን ሰሞኑን ለጨረታ የቀረበው የዘመኑ ሸክላ ሳህን፣ በ38 ሚሊዮን ዶላር በጨረታ ተሸጧል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ባይገለጽም፣ ለዕቃው እውነተኛነት ተብሎ የተከፈለ ዋጋ መሆኑንም አሥፍሯል፡፡

  20 ደቂቃ በፈጀ የጨረታ ጊዜ የተሸጠው አረንጓዴያማ ሳህን የቡሩሽ ማጠቢያ እንደነበር አጫራቹ ሶትባይስ አስታውቋል፡፡

  በ38 ሚልዮን ዶላር የጨረታ ዋጋ የተሸጠው የቻይና ሳህን

   

   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img