Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናሰማያዊ ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን እከሳለሁ አለ

  ሰማያዊ ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን እከሳለሁ አለ

  ቀን:

  መስከረም 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ከምኒልክ አደባባይ ተነስቶ ፍፃሜውን መስቀል አደባባይ የሚያደርግ የተቋውሞ ሠልፍ ለማድረግ አቅዶ የነበረው ሰማያዊ ፓርቲ፣ ዕቅዱ እንዳይሳካ አድርጓል ያለውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሠልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ክፍል ላይ ክስ ሊመሠረት እንደሆነ አስታወቀ፡፡

  የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታነህ ባልቻ ለሪፖርተር እንደገለጹት ክስ ከመመሥረት ባለፈም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ፣ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔና ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገቡና መመርያ እንዲሰጡ የሚጠይቅ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡

  ፓርቲው ይህን የገለጸው ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጋራ በጋራ በመኢአድ ጽሕፈት ቤት ሐሙስ መስከረም 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው፡፡

  ፓርቲው ከዚህ ቀደም መስከረም 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሠልፍ ለማድረግ አቅዶ የዕውቅና ደብዳቤ አስገብቶ እንደነበር ያስታወሱት የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር፣ ነገር ግን የመስቀልና የኢሬቻ በዓል የሚከበሩበት ወቅት እንደሆነ ከአስተዳደሩ ተገልጾላቸው ሠልፉን ማስተላለፋቸውን ገልጸዋል፡፡

  ሆኖም ከበዓላቱ ማለፍ በኋላ ተገቢውን ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡ ‹‹በተለይ መስከረም 19 ቀን 2010 ዓ.ም. የከተማ አስተዳደሩ ጽሕፈት ቤት ተገኝተን በአካል ያነጋገርናቸው ኃላፊ የኢሬቻው በዓል ሰላም ይለፍ እንጂ ሰኞ መስከረም 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ማለዳ የዕውቅና ቅጹን ትሞላላችሁ ብለው ከሸኙን በኋላ፣ በቀጠሮው ዕለት ልናገኛቸው አልቻልንም፤›› በማለት አብራርተዋል፡፡

  ‹‹የሰላማዊ ትግል በሮች በተዘጉ ቁጥር የአመፅና የሁከት በሮች መከፈታቸው ግድ እንደሚል ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገራችን ምድር ላይ የተከሰቱት ሕዝባዊ እምቢተኝነቶች ጉልህ ምስክሮች ናቸው፤›› በማለት ፓርቲው ለማከናወን የሚያቅዳቸው ሰላማዊ የተቃውሞ ሠልፎች፣ እነዚህን ጥያቄዎች ለማንሳትና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን ለመግለጽ ያለመ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

   በመሆኑም ፓርቲው በአገሪቱ የተፈጠሩ ፖለቲካዊ አለመግባባቶችን፣ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባትና የመሳሰሉ ጥያቄዎች በማንሳት፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተቃውሞውን ለመግለጽ ቢያቅድም የፖለቲካ ምኅዳሩ በመጥበቡ ምክንያት ሰላማዊ የተቃውሞ መንገዶችን ሁሉ እንደተዘጉበት ገልጸዋል፡፡

  ‹‹ምንን እንኳን ያቀድነውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሠልፍ በፈለግነው ቀን ለማከናወን ባንችልም ትግላችን ግን የሚቋረጥ አይሆንም፡፡ ስለሆነም በመጪዎቹ ሳምንታት ሠልፉን ማከናወናችን የማይቀር ነው፤›› ሲሉ አቶ ጌታነህ አስረድተዋል፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ1997 ዓ.ም. በኋላ የሚቀርቡለትን የፖለቲካ ስብሰባዎችና ተቃውሞ ሠልፎች ዕወቅልን ጥያቄ በአዎንታዊ መንገድ የተመለከተባቸው አጋጣሚዎች እጅግ በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ ይህም የዕውቅና አሠራር ወደ ፈቃድ እንደተሸጋገረ፣ ሽግግሩም ሕጋዊ ሥነ ሥርዓቱን ሳይከተል እንደተካሄደ በመጥቀስ በርካቶች ይተቹታል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...