Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየአትሌቲክሱ ሌላው ፈተና ጾታዊ ጥቃትና ዕድሜ

የአትሌቲክሱ ሌላው ፈተና ጾታዊ ጥቃትና ዕድሜ

ቀን:

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማክሰኞ መስከረም 23 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሆቴል ባዘጋጀው መድረክ የአትሌቲክሱን ቀጣይ ዕጣ ፈንታ በሚመለከት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በውይይቱ ከያካባቢው የተውጣጡ ሙያተኞችና ባለድርሻ አካላት፣ አሠልጣኞች፣ ማናጀሮችና የማናጀር ተወካዮች ተካፋይ ነበሩ፡፡ የአትሌቲክስ ሥልጠናና ውድድር፣ ጾታዊ ጥቃትና በስፖርት የተከለከሉ አበረታች ንጥረ ነገሮች የተመለከቱ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ችግሩን በሚገባ ያመላከተ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ የውይይቱን አስፈላጊነት አስመልክቶ እንደተናገረው፣ አትሌቲክሱ በተለይም በአሁኑ ወቅት ከደረሰበት ደረጃ አኳያ  በነበረው መቀጠል እንደማይቻል ገልጾ፣ ችግሩን ከመሠረቱ ዓይቶና ፈትሾ ወደ ትክክለኛው መስመር መግባት ይገባል፡፡  የቆየው ችግር የአንድ አካል ብቻ ተደርጎ መወሰድ እንደሌለበትና በጋራ ፈትሾ ለጋራ ውጤታማነት በጋራ መሥራት እንደሚያስፈልግ፣ ለዚያ እንደነዚህ የመሰሉ መድረኮች አስፈላጊነት ለአፍታም ቸል ሊባል አይገባም፡፡

 ጾታዊ ጥቃትን አስመልክቶ አንዳንድ አሠልጣኞችና የማናጀር ተወካይ አሠልጣኞች በተለይ በሴቶች አትሌቶች ላይ የሚያደርሱባቸው ጫናና በደል እንዲህ ቀላል ነው ተብሎ ሊታለፍ እንደማይገባው በራሳቸው በአሠልጣኞቹ አንደበት ሲነገር ተደምጧል፡፡ ‹‹እርስ በርሳችን እንተዋወቃለን፣ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም ስም ጠቅሰን መነጋገር እንችላለን፣ ለብሔራዊ ቡድን አስመርጥሻለሁ፣ ማናጀር አገኝልሻለሁ እያልን በየጫካው አስገድደን የምንደፍራቸው አትሌቶች ምን ያህል እንደሆኑ እኛ ቀርቶ የፌዴሬሽኑ ኃላፊዎች ሳይቀር በግልጽ የሚያውቁት የአደባባይ ምስጢር አይደለም ወይ?›› በማለት በአሠልጣኝነት ሽፋን ሲፈጸም የቆየው ወንጀል በሙያተኞቹ አንደበት ሲነገር ተደምጧል፡፡

በእምነት ብቻ ምንም የማያውቁ ታዳጊ አትሌቶች ነገን በማሰብ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባና መሰል ከተሞች በማምራት የ“አሠልጥኑን” ጥያቄ ለአሠልጣኞች እንደሚያቀርቡላቸው የሚናገሩት የመድረኩ ተሳታፊ አሠልጣኞች፣ አትሌቶቹ የቱንም ያህል ችሎታና ብቃት ቢኖራቸው አሠልጣኙ እሱ የሚፈልገውን ቅድመ ሁኔታ የማያሟሉ ከሆነ ያሰቡትን ማሳካት እንደማይችሉ በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ጭምር ስለሚነገራቸው የሚጠየቁትን ሁሉ እንደሚፈጽሙ ተናግረዋል፡፡

ከጾታዊ ጥቃት በተጨማሪ ዕድል ቀንቷቸው ለብሔራዊ ቡድን የመመረጥ አልያም በሌሎች አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ተሳትፈው ገንዘብና መሰል ጥቅማ ጥቅሞች ሲያገኙ በማናጀሮችና የማናጀር ተወካዮች መልካም ፈቃደኝነት ካልሆነ የደከሙበትን ጥቅም ጭምር እንደማያገኙ ነው በመድረኩ ሲነገር የተደመጠው፡፡ በእነዚህና መሰል የአሠልጣኞች ወከባ በርካታ አትሌቶች ዜግነት የሚቀይሩ ቁጥር እንደሌላቸውም ተነግሯል፡፡ ፌዴሬሽኑም ይህንኑ ያውቀዋል ተብሏል፡፡ ይህ ጉዳይ እንደ አትሌቲክሱ ገዝፎ ባይወጣም በእግር ኳሱ አካባቢም ተመሳሳይ ሙያዊ የሥነ ምግባር ጉድለቶች ሲከሰቱ ታይቷል፡፡

ሌላው በዚሁ መድረክ ከፍተኛ ውግዘትና ቅሬታ የቀረበበት የአትሌቶች የዕድሜ ጉዳይ ነው፡፡ በቅርቡ ኢትዮጵያን በመወከል ወጣት አትሌቶች በተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ለተካፈለው ቡድን መንግሥትና ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የገንዘብ ሽልማት ማበርከታቸው ይታወሳል፡፡ ይሁንና ወጣት ተብለው በውድድር የተሳተፉት አትሌቶች ካስመዘገቡት ውጤት ይልቅ ዕድሜያቸው ሚዛን ደፍቶ ሲያነጋግር መሰንበቱ ይታወሳል፡፡

ይህንኑ አስመልክቶ መድረኩ፣ ፌዴሬሽኑም ሆነ ክለቦች እስካሁን በነበረው አካሄድ መቀጠል እንደሌለባቸው አጽንኦት ሰጥቶ ተነጋግሯል፡፡ የዕድሜ ጉዳይ አንድ መፍትሔ ሊበጅለት እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡  

      

 

 

 

 

  

 

          

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹በየቦታው ምርት እየገዙ የሚያከማቹ ከበርቴ ገበሬዎች ተፈጥረዋል››

አቶ ኡስማን ስሩር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር...

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...