Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበፍትሕ ጥያቄ የተወጠረው እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥቅምት 30 የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ ያደርጋል

በፍትሕ ጥያቄ የተወጠረው እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥቅምት 30 የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ ያደርጋል

ቀን:

  • ክልሎች የዕጩዎቻቸውን ማንነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዋናነት ከሚተችባቸው ጉዳዮች መካከል በጉባኤ የፀደቁ ደንብና መመርያዎችን የማስፈጸም አቅም ውስንነት ይጠቀሳል፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ፣ ዘንድሮም በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ ሰመራ ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ የሥራ አስፈጻሚና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያከናውናል፡፡

ይሁንና በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ከ45 ቀን በፊት ለክልሎችና ክለቦች መድረስ ያለበት የጉባኤው አጀንዳ እስካለፈው ሰኞ መስከረም 29 ድረስ አጀንዳው ለክልሎችም ሆነ ክለቦች እንዳልደረሰ እየተነገረ ይገኛል፡፡ በዚህም ምክንያት ዕጩዎችን የማቅረብ ሥልጣንና ኃላፊነት ያለባቸው ክልሎች፣ የዕጩዎቻቸውን ማንነት ለማሳወቅ ተቸግረናል ይላሉ፡፡ የአገልግሎት ዘመኑን ካጠናቀቀው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የፌዴሬሽኑን ደንብና መመርያዎች ከማስፈጸም ይልቅ አንዳንዶቹ በጥቅምት መጨረሻ በሚደረገው አዲስ የሥራ አስፈጻሚና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውክልና የሚሰጧቸውን ክልሎች በማፈላለግ ላይ መሆናቸው ይነገራል፡፡

ከነባሮቹ አመራሮች የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ ለሁለተኛ ጊዜ የነበራቸውን ኃላፊነት ይዘው ለመቀጠል ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ውክልና ማግኘታቸው ተሰምቷል፡፡ ከሌሎችም ክልሎች ቀደም ሲል በአገሪቱ ትልቅ የሥልጣን ቦታ ላይ የነበሩና አሁንም በኃላፊነት በማገልገል ላይ የሚገኙ ግለሰቦች በቀጣይ የአመራርነቱን ቦታ ለመያዝ እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ታማኝ ምንጮች ይገልጻሉ፡፡

በሌላ በኩል ለዚህ ምርጫ ዕጩዎቻቸውን የሚያቀርቡ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ቀደም ሲል ከነበረው ተሞክሮ በመነሳት፣ ለወደፊቱ ቢያንስ እግር ኳሱን ወደ ተሻለ ደረጃ ሊወስዱ የሚችሉ ዕውቀቱና ክህሎቱ ብቻ ሳይሆን ለዘርፉ ውጤታማነት ቁርጠኝነት ያላቸውን ዕጩዎች ሊያቀርቡ እንደሚገባ የሚናገሩ አሉ፡፡ ከእነዚህ አስተያየት ሰጪዎች መካከል የአዲስ አበባ እግር ኳስ አሠልጣኞች ማኅበር ይጠቀሳል፡፡

ማኅበሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቀጣይ በሚያደርገው ምርጫ ዕጩ ሆኖ ቢቀርብ ድጋፉን እንደሚሰጥ በመግለጽ ለአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ መስከረም 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በደብዳቤ ጠይቋል፡፡ ማኅበሩ ድጋፉን እንደሚሰጠው ያስታወቀው አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌን ሲሆን፣ አሠልጣኙ በተለይም በእግር ኳሱ የተጫዋችነት ሕይወቱንና ከሙያ ጋር ያለውን የሙያ ክህሎትና ዕውቀት በመዘርዘር፣ እግር ኳሱ በተለይም በአሁኑ ወቅት ከገባበት የወጡትም ሆነ የአወቃቀር ችግሮች እንዲላቀቅ የጎላ ድርሻ እንደሚኖረው በማመን መሆኑን ጭምር ለአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ይጠይቃል፡፡

ማኅበሩ ሲቀጥል አቶ ዮሐንስ ሳሕሌ በአሁኑ ወቅት በእግር ኳስ አሠልጣኝነትና በሌሎችም ከዘርፉ ጋር በተገናኙ በልዩ ልዩ ሙያዎች ላይ በማገልገል ላይ መሆኑን በመግለጽ ወደ አመራርነት ቢመጣ እግር ኳሱ ከነበረበት ውስብስብ ችግርና ትርምስ የፀዳ እንዲሆን የበኩሉን ድርሻ ይወጣል ብሎ እንደሚያምንም አስታውቋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹በየቦታው ምርት እየገዙ የሚያከማቹ ከበርቴ ገበሬዎች ተፈጥረዋል››

አቶ ኡስማን ስሩር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር...

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...