‹‹አሁን በደረስኩበት ደረጃ በዚህ ኃላፊነት ለመቀጠል የማያስችሉኝ ሁኔታዎች ስላሉና ፍላጎቱም ስለሌለኝ ለመልቀቅ ድርጅቴንና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጠይቄያለሁ፡፡››
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል ተብሎ መሰንበቻውን በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ መሆናቸውን ተከትሎ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የተናገሩት፡፡ አፈ ጉባኤ አባ ዱላ በመግለጫቸው፣ ድርጅታቸውና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁኔታውን አይተው ሕጋዊ መስመሩን ተከትሎ ጥያቄያቸው ተገቢውን ምላሽ እንደሚያገኝ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ጥያቄያቸው ተገቢውን ምላሽ ሲያገኝ የምክር ቤት አፈ ጉባኤነቱን ለመልቀቅ የፈለጉባቸውን ምክንያቶች በዝርዝር እንደሚያስረዱም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡