በጣና ሐይቅ ከሚገኙት የዓሳ ዝርያዎች አንዱ ‹‹ፈጣጤ›› የሚባለው ነው፡፡ ‹‹ላቢዩባርበስ ማክሮታልመስ›› ይባላል፡፡ መካከለኛ መጠን ያለው (በሰውነት መጠን በጭንቅላት ልክና ስፋቱ) አብዛኛውን ጊዜ ትልልቆቹ ዝርያዎች ግልጽ የሆነ የማጅራት ጋማ ያላቸው ናቸው፡፡ ከ53 እስከ 425 ሚሊ ሜትር ርዝመት ያላቸው ዝርያዎች ተስተውለዋል፡፡ ጭንቅላታቸው ከርቭ በአማካይ በጣም ያነሰ ሲሆን በመጠኑ ወደ ታች የተደፋ ጎድግዳ ቅርጽ ነው፡፡ የላይኛውና የታችኛው መንጋጋ አማካይ ርዝመት ያለውና የታችኛው መንጋጋ ከላይኛው መንጋጋ አፍ ሲዘጋ ተመጣጣኝ ነው ወይም በትልልቆቹ ዝርያዎች ይረዝማል፡፡ አፉ መጠነኛ ስፋት ያለውና ቀጫጭን ከናፍር እንዲሁም የታችኛው ባለመስመሮች ወይም የማያቋርጥ ነው፡፡ ቅርፊቶቻቸው በአማካይ አጫጭርና ቀጫጭን ናቸው፡፡ የኋለኛው ጭራ በመስመር ቁጥር በአማካይ ከ30-34 ሲሆን ነገር ግን የመስመር ቁጥር በአማካይ ብዙ ሲሆን (ከ23-26) ነው፡፡
በሕይወት ያሉ ዝርያዎች በጣም ቢጫማና መደቡ ብርማ የሆነ ቀለም ያላቸው ሲሆን ጥቁር ቡናማ ጀርባ አላቸው፡፡ አየር መስገቢያዎቻቸው ቡናማ ዙሪያ አንዳንድ ጊዜ ደብዛዛ ነጠብጣብ በጠርዙ ላይ ይኖረዋል፡፡ በአልኮል ውስጥ መሠረታዊው ቅርፅ ቀላል ጠርዞችና ደብዛዛ ጀርባ ይኖረዋል፡፡ የመደቡ ቀለም ቢጫማ ቡኒ ነው፡፡
በሐይቁ በሙሉ ቦታ በጭቃማ፣ አሸዋማ፣ ድንጋያማ የሐይቁ ወለል ይገኛል፡፡ (አለት እምብዛም አይወድም) አብዛኛውን ጊዝ ከሦስት ሚሊ ሜትር ጥልቀት በላይ ይገኛል፡፡ በ17 የአንጀት ይዘት ውስጥ ላቢዩባርበስ ማክሮታልመስ በዋነኛነት ነፍሳትን (እጭም ሆነ ትልልቅ ነፍሳትን) ትንንሽ ዝርያዎቹ እንዲሁ ዙፕላክቶን ይመገባል፡፡ ትልልቆቹ ዝርያዎች አንዳንድ ጊዜ በተናጠል በዋነኛነት ዓሳዎችን ይመገባሉ፡፡
- አበበ ጌታሁን (ፕሮፌሰር) ጽፈውት የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ለመታሰቢያ ቴምብር ያሳተመው (መጋቢት 2009)