አሁን ባለው ሁኔታ መቀጠል ስለማልችል ከአፈ ጉባዔነት ኃላፊነት ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርቤያለሁ ያሉት አቶ አባዱላ ገመዳ ለመልቀቂያ ጥያቂያቸው ምላሽ እስኪያገኙ ድረስ የፓርላማ ጉባዔዎችን መምራት ቀጥለዋል፡፡
ዛሬ የተካሄደውን ስብሰባም አቶ አባዱላ የመሩ ሲሆን በዕለቱም ስምንት አዋጆች ቀርበው ለቋሚ ኮሚቴ ተመርተዋል፡፡
የቤተሰብ ሕግ ማሻሻያ፣ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ፣ የከተማ ፕላን ረቂቅ አዋጆች ከቀረቡት መካከል ይገኙበታል፡፡