Tuesday, November 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  አገሪቱን ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ በማሳጣት የተጠረጠሩ ቡና ነጋዴዎች ታሰሩ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  ከእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የብቃት ማረጋገጫ ሰጪ ባለሙያዎች ጋር በመመሳጠር፣ መንግሥት ማግኘት የነበረበትን ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማሳጠት የተጠረጠሩ ሁለት ቡና ነጋዴዎች በቁጥጥር ሥር  ውለው እየተመረመሩ ነው፡፡

  አቶ አብዱልቃድር ጀማልአብዱል ቃድርና አቶ አህመድ ረታ ዓሊ የተባሉት ተጠርጣሪዎች፣ በ2005 ዓ.ም. እና በ2006 ዓ.ም. በጀት ዓመት፣ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ 247.31 ቶን (2473.1 ኩንታል) ኤክስፖርት የሚሆን ቡና ገዝተው ነበር፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ግዢውን የፈጸሙት በቂ ካፒታል ሳይኖራቸው ከእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የብቃት ማረጋገጫ ሽያጭ ባለሙያዎች ጋር በመመሳጠር የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት በማቅረባቸው መሆኑን፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የፋይናንስ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ለፍርድ ቤት ገልጿል፡፡

  ተጠርጣሪዎቹ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ የገዙትን ኤክስፖርት የሚደረግ ቡና በገቢዎችና ጉምሩክ አማካይነት ወደ ውጭ መላክ የነበረባቸው ቢሆንም፣ ሳይልኩ መቅረታቸውን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት መርማሪ ፖሊስ አስረድቷል፡፡ በመሆኑም አገሪቷ ማግኘት የነበረባትን 928,100 ዶላር ወይም 17,077,667 ብር የውጭ ምንዛሪ እንድታጣ ማድረጋቸውንም አክሏል፡፡ ምርመራውን በሰውና በሰነድ አጣርቶ ለመላክ ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ፖሊስ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

  ፍርድ ቤቱ 12 ቀናት እንደሚበቃው በመግለጽ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ ለመጋቢት 27 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች