Sunday, February 5, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የውጭ ምንዛሪ ከፍፍልን ተግባራዊ ለማድረግ የወጣው መመርያ መጠነኛ ማስተካከያ ተደረገበት

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በባንኮች ተፈጻሚ የነበረውን የውጭ ምንዛሪ ክፍፍልን ተግባራዊ ለማድረግ የወጣው መመርያ ላይ መጠነኛ ማስተካከያ አደረገ፡፡

መመርያው ከወጣ አንድ ዓመት አስቆጥሯል፡፡ በባንኮች ውስጥ በውጭ ምንዛሪ አፈቃቀድ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ ያለመ ነው፡፡ የባንኮችን አሠራር ግልጽነት የተሞላበት ለማድረግ፣ ትኩረት የሚገባቸው ሴክተሮች ቅድሚያ እንዲያገኙ፣ ተገልጋዮችን ቅድሚያ የመጣ ቅድሚያ ያገኛል በሚል መርህ ለማስተናገድ እንዲቻል መመርያው መውጣቱ ይታወሳል፡፡

መመርያው አስመጪዎችና የባንኮች ዋና ደንበኞች ከዚህ በፊት ያገኙት የነበረውን የውጭ ምንዛሪ በቅድሚያ የማግኘት መብት በማንሳት፣ ደንበኞች ከመጡበት ሴክተርና ቅድሚያ የመጣ ቅድሚያ ያገኛል የሚል መርህን መሠረት አድርጎ ለማስተናገድ የተካ ነው፡፡

ከሳምንት በፊት በብሔራዊ ባንክ ማስተካካያ የተደረገለት ይህ መመርያ የተወሰኑ ለውጦችን ብቻ ይዞ መጥቷል፡፡ በዚህ መሠረት ባንኮች በውጭ ምንዛሪ አፈቃቀድ ላይ መረጃዎችን ለብሔራዊ ባንክ ሪፖርት አደራረጋቸው ላይ ለውጥ አድርጓል፡፡

በአዲሱ መመርያ መሠረት ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ጥያቄዎችን፣ ፈቃድ ያገኙ ጥያቄዎችንና የኢንቮይስ ፕሮፎርማ ኮፒ ለብሔራዊ ባንክ በየሳምንቱ ሪፖርት እንዲያደርጉ ይገደዳሉ፡፡ ከአሁን በፊት በነበረው መመርያ ባንኮች የኢንቮይስ ፕሮፎርማ ኮፒ ሪፖርት እንዲያደርጉ አይገደዱም ነበር፡፡

ይህ ማስተካካያ የተደረገው ባንኮች ለደንበኞቻቸው የውጭ ምንዛሪ ጥያቄን ካፀደቁ በኋላ በፈቀዱት መጠን ላይ ከብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ውጪ ለውጥ እንዳያደርጉ፣ የተፈቀደውም መጠን ለሌላ ዓላማ እንዳይውል ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የባንክ ኃላፊዎች ይገልጻሉ፡፡

አሁን ከተሻሻለው መመርያ በፊት ብሔራዊ ባንክ ለሁሉም ባንኮች ቀድሞ በወጣው መመርያ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ያደረገ ቢሆንም፣ በፊት ከወጣው መመርያ ያን ያህል ለውጥ እንዳልመጣ ይናገራሉ፡፡

ከእነዚህም ውስጥ መመርያው ለዕቃ አስመጪዎች፣ ለባንኮች ትልልቅ ደንበኞች፣ እንዲሁም ለትልልቅ ቆጣቢዎች ቅድሚያ እንዲሰጥ ጠይቀው እንደነበር ምንጮች ይናገራሉ፡፡

ነገር ግን በሰጡት አስተያየት መሠረት ምንም ለውጥ አልተደረገም ሲሉ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡

አዲሱ መመርያ ከተሻሻለው በተለየ ቅድሚያ ማግኘት ስለሚገባቸው ሴክተሮች በዝርዝር ያብራራል፡፡ በዚህም መሠረት ጋዝ፣ ነዳጅ፣ መድኃኒቶች፣ እንዲሁም ማዳበሪያ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡ ቅድሚያ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

በተጨማሪም በተሻሻለው መመርያ ለግንባታ ዕቃዎችና መሣሪያዎች የሚውሉ መለዋወጫዎች ቅድሚያ ያገኛሉ፡፡ ነገር ግን ፈቃዱን የሚያገኙት በግንባታ ሥራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች መሆን አለባቸው፡፡ እንዲሁም የመለዋወጫ ዕቃዎቹን ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ማዋል አለባቸው፡፡

ሲፈቀድላቸው መጠኑ ከ50 ሺሕ ዶላር ማለፍ እንደሌለበትም መመርያው ያዛል፡፡ መመርያው በሁሉም ባንኮች እኩል ተፈጻሚ ከሆነ አዎንታዊ ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ሪፖርተር ያናገራቸው ሌሎች ኃላፊዎች ይገልጻሉ፡፡

ባንኮች በመመርያው ላይ ያሉ አንቀጾችን ሲጥሱ ቢገኙ እስከ አሥር ሺሕ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል፡፡ መመርያው ከመጋቢት 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ተፈጻሚ መሆን ጀምሯል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች