Wednesday, February 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የዓለም ባንክ የ645 ሚሊዮን ዶላር ብድር አፀደቀ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የዓለም ባንክ በአንድ ሳምንት ውስጥ የ645 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለኢትዮጵያ ለመስጠት ተስማማ፡፡ ባንኩ ብድሩ በዳይሬክተሮች ቦርድ መጋቢት 22 ቀን 2009 ዓ.ም. መፅደቁን አሳውቋል፡፡

ብድሩ በሦስት ምዕራፍ ተከፋፍሎ የሚሰጥ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው የ445 ሚሊዮን ዶላር ብድር የአገሪቱን የውኃ አቅርቦትና የንፅህና አገልግሎትን ለማሻሻል ይውላል ተብሏል፡፡ በዚህም ብድር 3.38 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያንን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በ22 የኢትዮጵያ ሁለተኛ ከተሞች ተግባራዊ ይሆናል፡፡ አገሪቱ ውስጥ ካሉ ከተሞች ውስጥ አዲስ አበባ ብቻ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች እንዷላት ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን ከአጠቃላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አሥር በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው በእነዚህ መስመሮች ተጠቃሚ መሆን የቻሉት፡፡

ሁለተኛው ባንኩ ያፀደቀው 150 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ብድር ደግሞ የአገሪቱን የሎጂስቲክ ሴክተር ለማሻሻል ይውላል፡፡ ብድሩ የሞጆ ደረቅ ወደብን የአገሪቱ የሎጂስቲክስ ማዕከል ለማድረግ ለሚካሄዱ ግንባታዎች የሚውል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አውታሮች ግንባታና በሎጂስቲክስ ዘርፍ ለአቅም ግንባታ ሥራዎችም ይውላል ተብሏል፡፡

ባንኩ በሚሰጠው ብድር የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ የሞጆ ደረቅ ወደብን ከ60 ሔክታር መሬት ይዞታ ወደ 140 ሔክታር ለማስፋፋት አቅዷል፡፡

ሦስተኛው ባንኩ ያፀደቀው ወደ 50 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው ብድር ደግሞ የአገሪቱን ኢንዱስትሪዎች ተፎካካሪነት ለማሳደግ ይውላል፡፡ በዋናነት የአገሪቷን የብሔራዊ ልኬቶች፣ የጥራትና ዋስትና አገልግሎቶችን፣ እንዲሁም የጥራት ማረጋገጥ ሥራዎችን ለማሻሻል ይውላል፡፡

ይህም ኢንዱስትሪዎች በውጭ ገበያ ላይ የሚኖራቸውን ተፎካካሪነት ለማሳደግ ይረዳል ተብሏል፡፡ በዚህም ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች የዓለም አቀፍ ገበያን የጥራት ደረጃ በማሟላት እንዲቀርቡና ተቀባይነትን እንዲያተርፉ እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡    

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች