Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

እንዲህ ነን!

ትኩስ ፅሁፎች

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ እሌኒ ገብረመድኅን (ዶ/ር) ከጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስትር ጌርድ ሙለር ጋር በአዲስ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል

አልመለስ ቢሉ!

አዘነች ይሉኛል
የት አለ ሐዘኑ

ተጎዳች ይሉኛል
ምኑ ነው ጉዳቱ

ከዓይኔ  ፈሶ ፈሶ
መች ሞላ ገደሉ

ሲቆረቆር  ወሎ
አልተበሳ ምድሩ

ምን ሞታት ይበሉ ልንገራቸው እኔ

ዓይኖቼ፣ እጆቼ፣ አንጀቴና ልቤ አይምሮዬ ብዬ

ውሸቱን ነው እንጂ ተስናብቶ ሄዷል ኮብልሏል ገላዬ

ለውዷ እናቴ፣  ለፍቅር እህቴ፣ ለአስተማሪው ወንድሜ::

ከወ/ሮ ሄኖኬ ወልደ መድሕን

* * *

ከዴንቨር ለዘጠኝ ወር የጠፋው ድመት ዳላስ ተገኘ

ሀርቪ የተሰኘ ድመት ከዴንቨር በጠፋ በዘጠኝ ወሩ  ዳላስ ውስጥ በአንድ ትልቅ ግንባታ ሳይት ላይ ከሚገኝ 25 ጫማ ርዝመት ካለው ጉድጓድ ውስጥ መገኘቱን ኤንቢሲ ዘገበ፡፡ ድመቱ እንዴትም ይሁን እንዴት የተጓዘው ርቀት 794 ማይል ሲሆን ድመቱን ከጥልቁ ጉድጓድ ለማውጣት የዳላስ ከተማ የእንስሳት አገልግሎት ተቋም መገኘት የግድ ሆኖ ነበር፡፡ ሀርቪን ከጉድጓዱ የማውጣት ሥራም ስድስት ሰዓት ያህል ወስዶ ነበር፡፡ ድመቱ ጭቃ ተጋግሮበት የነበረ ቢሆንም ከጉድጓዱ የወጣው በጤና ነበር፡፡

* * *

ፈረንሣይ ፕላስቲክ ኩባያና ሰሃን ጥቅም ላይ እንዳይውል አገደች

በተለያየ መንገድ አወጋገዳቸው ለአየር ንብረት ለውጥ አስተዋጽኦ ይኖረዋል የተባሉትን የፕላስቲክ ኩባያ፣ ሰሃን፣ ሹካና ማንኪያ ያሉ ነገሮች አገልግሎት ላይ እንዳይውሉ ፈረንሣይ ሕግ ማውጣቷን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡ ፈረንሣይ ያወጣችው ይህ ሕግ የአውሮፓ ኅብረት የቁሳቁሶችን ነፃ የንግድ ዝውውር እንደሚፃረር እየተገለጸ ነው፡፡ ቢሆንም ግን በርካታ የአውሮፓ ኅብረት የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪዎች ሕጉን እያወደሱት ነው፡፡ ይህ ሕግ ተግባራዊ ይሆናል የተባለው እ.ኤ.አ. 2020 ላይ ቢሆንም ፈረንሣይ የኅብረቱን ስምምነቶች እየተፃረረች በመሆኑ የአውሮፓ ኅብረት ዕርምጃ እንዲወስድ ቅስቀሳ እያደረጉ ያሉ ቡድኖችም አሉ፡፡   

* * *

‹‹መሐረቤን ያያችሁ››

‹‹መሐረቤን ያያችሁ›› የኢትዮጵያን ከ1980ዎቹ መጨረሻ ወዲህ ያለውን ማኅበራዊ ሕይወት መቼቱን ያደረገው ያጫጭር ታሪኮች መድበል ነው፡፡ ሙሉጌታ አለባቸው የደረሳቸውን ዐጫጭር ታሪኮች መድበሉን ዛሬ መጋቢት 27 ቀን 2009 ዓ.ም. በ12 ሰዓት በሞዛይክ ሆቴል ያስመርቃል፡፡

* * *

የሒስ መድረክና ዓውደ ርዕይ

      “ሐሳብን በሐሳብ መፈተን” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ወርኃዊ የሒስ መድረክና ዓውደ ርዕይ ቅዳሜ መጋቢት 30 እና እሑድ ሚያዝያ 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው በትራኮን ሕንፃ ላይ ይካሄዳል፡፡

     ቅዳሜ በ8 ሰዓት ለሒስ መድረክ የሚቀርበው መጽሐፍ በምሕረት ደበበ (ዶ/ር) የተጻፈው ‘‘የተቆለፈበት ቁልፍ’’ ሲሆን፣  በዕለቱ የመወያያ ሐሳብ የሚያቀርቡት ዘካሪያስ ዐምደብርሃን (ዶ/ር) ናቸው፡፡ ከሒስ መድረኩ በተጓዳኝ ክብሩ መጽሐፍ፡ ሊትማን ቡክስና እነሆ መጻሕፍት በጋራ ያዘጋጁት የመጽሐፍ ዕቁብን ጨምሮ ከ25-50 በመቶ ቅናሽ የሚደረግበት የመጻሕፍት ዓውደ ርዕይ ይኖራል፡፡

* * *

 

እንዲህ ነን!

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ እሌኒ ገብረመድኅን (ዶ/ር) ከጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስትር ጌርድ ሙለር ጋር በአዲስ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች