አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) ተልጦ የተፈጨ ድንች
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
- 1 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
- 3 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
- 1 የሻይ ማንኪያ መከለሻ
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
አዘገጃጀት
- ቀይ ሽንኩርት በውኃ ብቻ ማቁላላት
- ትንሽ ውኃ ጨምሮ ጠብ እያደረጉ ማብሰል
- ዘይት ጨምሮ ሽንኩርት መብሰሉን ማረጋገጥ
- አዋዜ መጨመርና ድብን አድርጐ ማቁላላት
- ድንቹን መጨመር
- ርጥብ ቅመም መጨመርና ጨው ማስተካከል
- መከለሻ ነስንሶ ወጡ እንደ ሽሮ ደረቅ ብሎ ሲንተከተክ አውጥቶ ቀዝቀዝ ሲል ለገበታ ማቅረብ
- ደብረወርቅ አባተ (ሱሼፍ) “የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት” (2003)