ማንይንገረው ሸንቁጥ በጻፉት ‹‹ባለአከርካሪዎች›› መጽሐፍ፣ ስለ አሳ ዝርያዎችና ገጽታቸው አስፍረዋል፡፡ ከነዚህም ዛፍ ላይ ከሚወጡ የአሳ ዝርያዎች አንዱ የሆነው ፐርች (Perch) ስለተሰኘው የቀረበው ነው፡፡ እነዚህ አሳዎች በቁመት ከ7 አስከ 20 ሳ.ሜ. ሲደርሱ አነስተኛ መጠን አላቸው፡፡ በስንጥባቸው ሽፋን ላይ የሚገኘውን ተንቀሳቃሽ ሹል የአካልክፍል በመዘርጋት መሬት ሲቆነጥጡ ጭራና የፊት ክንፈ አሳ (እግርን የተካው) በመጠቀም ደግሞ በኃይል ወደፊት ይገፋሉ፡፡ የእነዚህ አሳዎች ስንጥብ ለተወሰነ ጊዜ በአየር ላይ እንዲተነፍሱ ሆኖ የተሻሻለ ሳንባ መሰል አካል ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ውኃ አካባቢ የሚገኝ ዛፍ ላይ መውጣት ችለዋል፡፡