Wednesday, April 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅቀዳሚው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት

ቀዳሚው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት

ቀን:

በፋሺስት ኢጣሊያ በ1928 ዓ.ም. ሰማዕት ለሆኑት አቡነ ጴጥሮስ፣ ከ1933 ዓ.ም. ድል በኋላ በአዲስ አበባ የቆመው የመጀመርያው የመታሰቢያ ሐውልት በፎቶው (በ1941 ዓ.ም. የተነሳ) የሚታየው ነበር፡፡ የአቡኑ አለባበስ ‹‹የአርመን ጳጳሳት አለባበስ ይመስላል›› በሚል ሐውልቱ እንዲነሳ ተደርጎ፣ በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሙዚየም እንዲቀመጥ ሲደረግ፣ በምትኩ አሁን በአደባባዩ የሚታየው ሐውልት እንዲተከል ተደርጓል፡፡

(ሔኖክ መደብር)

* * *

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

/ ኵልክሙ (በአማርኛ)

አንፃር ቅኔ

ኢትዮጵያ እምነ÷ ጥንተ ኑባሬሽ ተዐውቆ

ስምሽ በቀለመ ወርቅ ተጽፏል ደማምቆ።

/ መወድስ ቅኔ (በአማርኛ)

እምኵሎሙ ኬክ ወአይስክሬም

ወተት አድርጓት እግዜር ማርና ወተት ባፈለቀች

የኢትዮጵያ ወተት ምን ይወጣው አሉ ልጆች።

ከማርነቷም በዘለለ

እንደሳት ታፋጃለችና አይጣሏት ሰዎች።

በከመ እቡያን መሳፍንት

በርሷ አለመኖር ዓለም እህል ውኃቸው የመረረች።

ለዓለም

ሰው ካለስ የተከበረ በሰላም ወዳድ ዜጎች

ስሙም እንዳበበች ጸደ ልዕልና ትኖራለች።

እስመ በልዕልና ዐጸድ የሚጠብቋት እጆች

ከስምም በላይ ስምም ያለው ሰው እንዳላቸውም ያውቁ ሕዝቦች።

 

ኃይለ ልዑል ካሣ፣ አዲስ አበባ (ጥቅምት ፳፻፲ .ም.)

* * *

ቭላድሚር ፑቲን ውሻ ተበረከተላቸው

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን 65ኛ የልደት በዓላቸውን መስከረም 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ማክበራቸውን ተከትሎ ምርጥ ዝርያ ያለው ውሻ ከቱርክሜኒስታን ፕሬዚዳንት ተበረከተላቸው፡፡

ውሻ ወዳጁ ፑቲን በዓለም ልዩና ‹‹አላባይ›› የተባለውን ውሻ ከፕሬዚዳንቱ በርዲ ሙካሚዶቭ ከተቀበሉ በኋላ፣ የቡችላውን ግንባር እንደሳሙ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ፑቲን ውሻውን በሩሲያኛ ‹‹ቨርኒ›› ማለትም ታማኝ ሲሉ ስም አውጥተዋል፡፡

ቭላድሚር ፑቲን ውሻ ተበረከተላቸው

* * *

46 ዓመታት ያስቆጠረ የታሸገ ሾርባ ለምግብ ባንክ በዕርዳታ ተሰጠ

በቤታቸው ያለውን የምግብ ክምችት በቅጡ የማያውቁ ሰዎች በተለይ ምግብ መለገስ ሲያስቡ ምግቡ መቼ እንደተገዛ ማየት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንዲሁ በልግስና ስም የሆነ ያልሆነውን ለተቸገሩት መስጠትም ሰብአዊነት አይደለም፡፡ ስካይ ኒውስ ያሠፈረውም፣ 46 ዓመታት ያስቆጠረ እሽግ ሾርባና 35 ዓመታት ያስቆጠረ ጣፋጭ በቆሎ ለምግብ ባንክ በዕርዳታ መሰጠቱን ነው፡፡

ለምግብነት አልቆ የተዘጋጀው የኩላሊት ሾርባ የታሸገበት ቆርቆሮ ላይ ዋጋው እንደተለጠፈ የተገኘ ሲሆን፣ የተመረተውም እ.ኤ.አ. ከ1971 በፊት ነው፡፡

የካርዲፍ ምግብ ባንክ ሠራተኛዋ ሄለን ቡል፣ ሰዎች የምግብ ዕርዳታ መስጠታቸውን እንጂ ጥቅም ላይ የሚውል ስለመሆኑ አያረጋግጡም፡፡ ብዙውን ጊዜ አዛውንቶች ከሞቱ በኋላ ልጆች ቤት ውስጥ ያለውን ዕቃ በዕርዳታ ሲሰጡ ይኼ ያጋጥማል ብላለች፡፡

የሾርባ አምራቹ ሄንዝ ዜናውን አስመልክቶ በሰጠው መልስ፣ ምርቱ ከ35 ዓመታት በፊት መቆሙን አመልክቶ፣ የኩላሊት ሾርባው ምግብ ባንክ ሳይሆን ሙዚየም መላክ ነበረበት ብሏል፡፡

46 ዓመታት ያስቆጠረ የታሸገ ሾርባ ለምግብ ባንክ በዕርዳታ ተሰጠ

  

* * *

ሁለት ጭንቅላት ያላት ግልገል ወለደችው ፍየል

መሰንበቻውን በደቡብ ወሎ ቦረና የተሰማው አንዲት ፍየል ሁለት ጭንቅላት ያላት ግልገል ስለመውለዷ ነበር።

ኤፍቢሲ እንደዘገበው፣ መስከረም 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በቦረና ወረዳ 019 መንደዩ ቀበሌ ልዩ ቦታው ታች ቦረቦር በሚባለው አካባቢ የምትገኝ ፍየል፣ ባልተለመደ መንገድ ከአንገቷ በላይ ሁለት አፍና አራት ዓይን ያላት ግልገል ወልዳለች።

የፍየሏ ባለቤት አቶ ምረቱ ታረቀ እንደገለጹት፣ ፍየሏን ከገዛት ከሦስት ወር በኋላ እንደወለደችና ግልገሏ ከተወለደች ጀምሮ መቆም አትችልም። እንዲሁም በራሷ መጥባት ስላልቻለች ፍየሏን እያለበ በመጋት እስካሁን እየተንከባከቧት እንደሚገኙም ተናግረዋል።

የቦረና ወረዳ የእንስሳት ጤና አገልግሎት ባለሙያ ዶ/ር ንጉሡ ብርሃኑ እንዳመለከቱት፣ ከአንገት በላይ ሁለት አፍና አራት ዓይን ኖሯቸው የሚፈጠሩት ፈርትላይዝ መሆን ያለበት እንቁላል ሳይሰበር ሲቀር ነው፡፡ ሁለት የተለያዩ እንቁላሎች ለመንታ ታስበው ሳይሰበሩ ዘግይተው ማህጸን ላይ ሲጣበቁ የሚከሰትበት ዕድል እንደሚኖር መላ ምቶች እንደሚያሳዩም ገልጸዋል።ሁለት ጭንቅላት ያላት ግልገል የወለደችው ፍየል

* * *

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...