Saturday, June 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናክልሎችን ከአጎራባች ክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች የሚያቀናጅ አገር አቀፍ የከተማ ፕላን ሊዘጋጅ ነው

ክልሎችን ከአጎራባች ክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች የሚያቀናጅ አገር አቀፍ የከተማ ፕላን ሊዘጋጅ ነው

ቀን:

የአዲስ አበባና የአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን በገጠመው ተቃውሞ ከተሰረዘ በኋላ፣ የፌዴራል መንግሥት በመላ አገሪቱ የተቀናጀ የከተማ ፕላን ለመፍጠር ያረቀቀው አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡

ረቂቁ በሥራ ላይ የሚገኘውን የከተማ ፕላን አዋጅ ቁጥር 574/2000 ሙሉ በሙሉ የሚተካ ሲሆን፣ ዓላማውም በሥራ ላይ ያለው አዋጅ ላይ የታዩ የአፈጻጸም ችግሮችን መቅረፍ ስለመሆኑ የረቂቁ ማብራሪያ ይገልጻል፡፡

አጠቃላይ ዓላማውም ከአገሪቱ ፖሊሲና የዕድገት አቅጣጫ ጋር የተጣጣመና የተቀናጀ የልማት ፕላን እንዲኖር ማድረግ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ከተሞች የከተማ ገጠርና የከተማ ከተማ ትስስርን ማጠናከር፣ እንዲሁም ተመጋጋቢና የተመጣጠነ የአከታተም ሥርዓት በመፍጠር ከተሞችን የልማትና የዕድገት ማዕከል ማድረግ መሆኑ በረቂቁ ላይ ተገልጿል፡፡

- Advertisement -

በዚሁ መሠረት በረቂቁ አንቀጽ ሰባት ላይ የፕላን ዓይነትና ተዋረዶች ተዘርዝረዋል፡፡ እነዚሁም አገራዊ የከተማ ፕላን፣ ክልላዊ የከተማ ልማት ፕላን፣ የከተማ አቀፍ ልማት ፕላንና ስኬቶች ፕላን ናቸው፡፡

አገራዊ የከተማ ፕላን በአገር ደረጃ የከተማ ልማትና የአከታተም ሥርዓትን የሚያሳይ የፕላን ዓይነት እንደሆነ፣ በይዘቱም የአገሪቱን ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና ዕቅዶች መሠረት በማድረግ ዋና ዋና የልማት ቀጣናዎችን፣ የአገሪቱን ሥርዓተ ከተማና የመሬት አጠቃቀም ሥርዓት ያካትታል፡፡

እንዲሁም ከተሞች ከገጠርና ከተሞች ከከተሞች ጋር ያላቸውን ትስስር፣ አኅጉራዊና ዓለም አቀፍ ትስስርን የሚያመለክት ማብራሪያ ይዟል፡፡

ክልላዊ የከተማ ፕላን ደግሞ በክልል ደረጃ የከተማ ልማትና የአከታተም ሥርዓትን የሚያሳይ የፕላን ዓይነት ሆኖ አገራዊና ክልላዊ ፖሊሲዎችን፣ ዋና ዋና የልማት ቀጣናዎችን፣ የክልሉን ሥርዓተ ከተማ እንዲሁም የመሬት አጠቃቀም ሥርዓትን የሚያብራራ መሆን እንደሚጠበቅበት በረቂቁ ተገልጿል፡፡

ከተሞች ከከተሞች ጋር ያላቸውን ትስስርና በክልሎች መካከል ያለውን ትስስር የሚያመለክት ማብራሪያ ማካተት ይጠበቅበታል፡፡

ረቂቁ የሕግ ሰነዱ ክልል ለሚለው የሚሰጠው ትርጓሜ፣ ‹‹በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 47(1) የተመለከተው ማንኛውም ክልል ሲሆን፣ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችንም ይጨምራል፤›› ይላል፡፡

ከተማ አቀፍ ፕላን ደግሞ በከተማ አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጅ ሆኖ መዋቅራዊ ፕላን፣ ስትራቴጂካዊ ፕላን፣ መሠረታዊ ፕላንና ስኬች ፕላን ዓይነቶችን እንደሚያካትት በረቂቁ ተመልክቷል፡፡

መዋቅራዊ ፕላን የሕዝብ ቁጥራቸው ከ100,000 በላይ ለሆኑ ከተሞች የሚዘጋጅ ሆኖ፣ ከተማው በአቅራቢያው ከሚገኙ የገጠር አካባቢዎችና ከሌሎች ከተሞች ጋር የሚኖረውን ትስስር፣ ከተማው የሚያድግበትን መጠንና አቅጣጫ ማካተት ይኖርበታል፡፡

ስትራቴጂካዊ ፕላን ደግሞ የሕዝብ ቁጥራቸው ከ20 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ለሆኑ ከተሞች የሚዘጋጅ እንደሆነ ያመለክታል፡፡

የከተማ ነዋሪዎች፣ ባለድርሻ አካላት፣ ወይም ማንኛውም ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ፕላን እንዲዘጋጅ ሐሳብ ካመነጩ ፕላን እንደሚዘጋጅ በረቂቁ ተካቷል፡፡ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ይህንን አዋጅና አዋጁን ተከትለው የሚወጡ ደንቦችና መመርያዎች በሁሉም ክልሎች መፈጸማቸውን እንደሚከታተል፣ ጉድለቶች ካሉም ተገቢውን ማስተካከያ የማድረግ ኃላፊነት በረቂቁ ተሰጥቶታል፡፡

ረቂቁ ሐሙስ ጥቅምት 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ለፓርላማ በቀረበበት ወቅት የቀረበው ጥያቄ አንድ ብቻ ሲሆን ይኸውም፣ ‹‹ፓርላማው ይህንን አዋጅ የማፅደቅ ሥልጣን አለው ወይ? ሕገ መንግሥታዊስ ነው ወይ? የሚለውን የሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንዲያጤነው፤›› የሚል ነበር፡፡ በዚሁ መሠረት አዋጁ ለሚመለከተው ለከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ ተመርቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...