Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበዘንድሮ ታላቁ ሩጫ 48 ሺሕ ተሳታፊዎች ይሮጣሉ

በዘንድሮ ታላቁ ሩጫ 48 ሺሕ ተሳታፊዎች ይሮጣሉ

ቀን:

  • ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች 1.6 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዷል

በየዓመቱ በኅዳር ወር የሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እንደ ወትሮው በመፀው ወቅት 48 ሺሕ ተሳታፊዎችን ያካተተ ቶታል የ2017 የጎዳና ሩጫውን ያስተናግዳል፡፡

የዘንድሮ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ትኩረት ከሰጣቸው ማኅበራዊ ጉዳዮች መካከል፣ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው አካላዊ፣ ሥነ ልቦናዊና ወሲባዊ ትንኮሳዎችን ለመግታት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን መደገፍ ይገኙበታል፡፡ በአፍሪካ ግዙፍ የሚባለው ታላቁ ሩጫ ‹‹100 ሚሊዮን ምክንያቶች ለሴት ልጆች በጋራ ለመሥራት›› በሚል መሪ ቃል እንደሚከናወንም ተገልጿል፡፡  

10 ኪሎ ሜትሩ ዋናው ሩጫ በተጓዳኝ ዘንድሮ ለ13ኛ ጊዜ በሚካሄደው የሕፃናት ሩጫ በሁለቱም ፆታ ከ5፣ ከ8 እና ከ11 ዓመት በታች ባሉ ልጆች መካከል ይደረጋሉ ተብሏል፡፡ የታላቁ ሩጫ ዝግጅት ክፍል ሐሙስ ጥቅምት 2 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሒልተን ይህንኑ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

‹‹ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ›› በሚል መሪ ቃል የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሌሎችን ለመርዳት የሚያካሄደው የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ የዝግጅቱ አንድ አካል ሲሆን፣ በዚህ ፕሮግራም በ2017ቱ ሩጫ ለአራት የበጎ አድራጎት ማኅበራት ከ1.6 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡ በጎ አድራጎት ድርጅቶቹ በሴቶች ሕፃናትና አረጋውያን ላይ አተኩረው የሚሠሩ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት በተመሳሳይ መሪ ቃል በተከናወነው ዘመቻ ከ9.9 ሚሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ 32 የተለያዩ ድርጅቶችን ለመርዳት መቻሉም ተነግሯል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው የታደሙት የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡመድና የፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ አብዱ አምዱ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ ልዩ ልዩ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በሚበዙባቸው አገሮች ሴት ልጆችን በአስገድዶ መድፈር፣ በፆታዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት፣ ያለ ዕድሜ ጋብቻ፣ ጠለፋ፣ ግርዛት እንዲሁም በሌሎች ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሕፃናት ሕይወት ‹‹ላይቃና ተጣመመ፤›› ሲሉም የችግሩን አሳሳቢነትና መጠን ገልጸዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደረጉ ጥናቶችን በመጥቀስ ወደ 62 ሚሊዮን የሚጠጉ ሴት ልጆች የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት እንደማያገኙ፣ ከ100 ሚሊዮን በላይ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሴት ልጆች ደግሞ ተገደው የሚደፈሩበት መሆኑ በኃላፊዎቹ ተገልጿል፡፡ እንደ ኃላፊዎቹ እነዚህን የመሳሰሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ለማውገዝና መልዕክቶችን ወደ ኅብረተሰቡ ለማስተላለፍ ደግሞ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የተሻለ መድረክ ሊኖር እንደማይችልም ተናግረዋል፡፡ በመግለጫው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መሥራችና የበላይ ጠባቂ ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ጨምሮ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮሐንስ ጥላሁንና ሌሎችም ከፍተኛ የግልና የመንግሥት ድርጅት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡   

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...