Wednesday, October 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየዓለም የምግብ ቀን በኢትዮጵያ

  የዓለም የምግብ ቀን በኢትዮጵያ

  ቀን:

  ማክሰኞ ጥቅምት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ቀን ይከበራል፡፡ በዋናነት ‹‹በምግብ ዋስትናና በገጠር ልማት ኢንቨስት በማድረግ የስደት ገጽታን እንቀይር!›› በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች እንደሚከበር ተገልጿል፡፡ በበዓሉ አከባበር ላይ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳመነ ዳሮታ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአገር ውስጥ፣ ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችና ዳያስፖራ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ካሳ ወልደ ሰንበት፣ የዓለም ምግብ ድርጅት (FAO) ረዳት ተወካይ አቶ ሐሰን ዓሊ ጥቅምት 2 ቀን 2010 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫው እንደተጠቆመው በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2015 ብቻ 240 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ድንበር አቋርጠው ተሰደዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2013 ደግሞ ከኢትዮጵያ 567 ሺሕ ዜጎች ድንበር ተሻግረው ተሰደዋል፡፡ በኢትዮጵያ ስደትን ለመቀነስና ድህነትን ማስወገድ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ በ2009 በጀት ዓመት ለ1.6 ሚሊዮን ሰዎች ሥራ መፈጠሩ፣ በ2010 ዓ.ም. ደግሞ 1.8 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑን በመግለጫው ወቅት ተብራርቷል፡፡

   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img