Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየካርታ ሥራና የታብሌት ኮምፒዩተር ግዥ መዘግየት የሕዝብና ቤት ቆጠራውን እንዳራዘመ ተገለጸ

የካርታ ሥራና የታብሌት ኮምፒዩተር ግዥ መዘግየት የሕዝብና ቤት ቆጠራውን እንዳራዘመ ተገለጸ

ቀን:

የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የካቲት 4 ቀን 2010 ዓ.ም ለሚደረገው አራተኛው የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ አስታወቀ፡፡ በቅርቡ በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ሥፍራዎች በተፈጠረው ግጭት በሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀል በቆጠራው ላይ ተፅዕኖ እንደማይፈጥር ገለጸ፡፡ የካርታ ሥራ፣ የታብሌት ኮምፒዩተርና የፓወር ባንክ ግዥ መጓተት ለመዘግየቱ በምክንያትነት ተጠቅሰዋል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ማክሰኞ ጥቅምት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ኤጀንሲው ከቆጠራው ጋር በተያያዘ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ የመሥራት ኃላፊነት እንዳለው፣ ነገር ግን በዜጎች መፈናቀል ሳቢያ ቆጠራው ላይ ተፅዕኖ እንዳይፈጠር ከሁለቱ ክልሎች መንግሥታትና ከሌሎች የሚመለከታቸው የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች እየተሠራ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

‹‹ያም ሆነ ይህ ማንም ዜጋ ሳይቆጠር አይታለፍም፤›› ሲሉ አቶ ቢራቱ ተናግረዋል፡፡ ኅዳር ወር 2010 ዓ.ም. ይደረጋል ተብሎ ቅድመ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየው ይህ አገር አቀፍ ቆጠራ በተለያዩ ምክንያቶች ለየካቲት 4 ቀን 2010 ዓ.ም. እንዲራዘም ተደርጓል፡፡ ጋምቤላ ክልል ውስጥ አንዳንድ ቦታዎች በጎርፍ ምክንያት ካርታ ውስጥ ባለመካተታቸው፣ የካርታ ሥራው እስከ ነሐሴ 2009 ዓ.ም. ድረስ እንደተራዘመ ተገልጿል፡፡ ይህም ለቆጠራው መዘግየት እንደ አንድ ምክንያት ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም ቆጠራውን ለማካሄድ እንዲያገለግሉ በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በኩል እንዲገዙ የታዘዙት 180 ሺሕ ዲጂታል ታብሌት ኮምፒዩተርና ፓወር ባንክ ግዢዎች ከታቀደላቸው ጊዜ በላይ መውሰዳቸው፣ ለቆጠራው  መራዘም ሌላ ምክንያት ሆኗል፡፡

ወደ 3.5 ቢሊዮን ብር ተመድቦለት ዝግጅት እየተደረገበት ላለው ቆጠራ  ከተገዙት 180 ሺሕ ታብሌቶች ውስጥ 120 ሺሕ ያህሉ ወደ አገር ውስጥ እንደገቡ ተገልጿል፡፡ ነገር ግን የጉምሩክ ሥርዓት አልፈው ኤጀንሲው እጅ እንዳልገቡ አቶ ቢራቱ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ታብሌቶች ከመጡም በኋላ ለቆጠራው የሚያስፈልጉ የተለያዩ አፕሊኬሽኖች እንደሚጫንባቸው፣ በቆጠራው ለሚሳተፉ ባለሙያዎች ሥልጠና በቀጣዮቹ ሁለት ወራት እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሕገ መንግሥቱ መሠረት በየአሥር ዓመቱ የሚደረገው አገር አቀፍ ቆጠራ 190 ሺሕ የሚሆኑ ባለሙያዎች፣ ቆጣሪዎችና አስተባባሪዎች ይሳተፉበታል፡፡ ከሌላው ጊዜ በተለየ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘው ይህ ቆጠራ፣ የመረጃ መሰብሰብ ሥራው አማርኛን ጨምሮ በአራት ቋንቋዎች ማለትም በኦሮሚኛ፣ በአፋርኛ፣ በሶማሌኛና በትግርኛ ይከናወናል ተብሏል፡፡

ከየካቲት 4 ቀን ጀምሮ 2010 ዓ.ም. ለአሥር ቀናት ይዘልቃል ተብሎ የተገመተው ቆጠራ፣ በስድስት ወራት ውስጥ ለሕዝብ ውጤቱ ይፋ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...