Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘም በክልል አዋሳኞች የተከሰተ ግጭት በምክንያትነት ቀረበ

ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘም በክልል አዋሳኞች የተከሰተ ግጭት በምክንያትነት ቀረበ

ቀን:

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመው በተለያዩ የክልል አዋሳኞችና አንዳንድ ሥፍራዎች፣ የግጭት ምልክቶች በመታየታቸው ምክንያት መሆኑን መንግሥት አስታወቀ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሐሙስ መጋቢት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በድጋሚ ለተጨማሪ አራት ወራት ለማራዘም ረቂቅ የማራዘሚያ አዋጅ ቀርቦ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡ መራዘሙን አስመልክቶ በምክር ቤቱ ቀርበው ማብራሪያ የሰጡት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት ኃላፊና የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ አዋጁ የነበሩትን ድንጋጌዎች በአብዛኛው እንደያዘ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡

ምንም እንኳን አዋጁ ባለፉት ስድስት ወራት በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት የፈጠረ ቢሆንም፣ አሁንም ድረስ ፀረ ሰላም ኃይሎች ባሏቸው ቡድኖች በተወሰኑ ክልሎች አለመግባባትና ግጭቶች እየተፈጠሩ ነው ብለዋል፡፡ እንዲሁም በራሪ ጽሑፎችን መበተንና መንገድ መዝጋት ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ ማረጋጋትን መስፈን ባለመቻሉ፣ ለአዋጁ መራዘም ምክንያት መሆኑን አቶ ሲራጅ ጠቁመዋል፡፡

በተለይ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አንዳንድ አካባቢዎች አንዳንድ ወገኖች ፀረ ሰላም ተግባር ለማከናወን እየተንቀሳቀሱ ነው በማለት ገልጸዋል፡፡

‹‹በአንፃራዊነት ሰላምና መረጋጋቱ የተሻለ ውጤት ላይ ቢደርስም፣ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ተጨማሪ ጊዜ ስለሚያፈልግ አዋጁ ሊራዘም ይገባዋል፤›› ሲሉ የመንግሥትን እምነት ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡

አዋጁ ከዚህ ቀደም አካቷቸው የነበሩ ክልከላዎችና ድንጋጌዎች ቀስ በቀስ እየተሻሻሉ ቢመጡምና የተወሰኑ ክልከላዎች በከፊልና በሙሉ ቢነሱም፣ በአብዛኛው ክልከላዎቹ አሁንም ይቀጥላሉ ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም የወጡ ደንቦችና መመርያዎች እንዳሉ የሚቀጥሉ መሆኑን፣ በኮማንድ ፖስቱ የተወሰዱ ዕርምጃዎች፣ ውሳኔዎችና በፍትሕ አካላት የተወሰኑ ውሳኔዎች በዚህ በተራዘመው አዋጅም ተፈጻሚነታቸው እንደሚቀጥል የመከላከያ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን፣ ፓርላማው የዘንድሮ የሥራ ዘመኑን ሲጀምር መፅደቁ ይታወሳል፡፡ ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጅ ምክንያት የነበረው ለአንድ ዓመት ያህል የዘለቀው በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የተከሰው አመፅ ነው፡፡ በዚያ አመፅና ሁከት ሳቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የሞቱ ሲሆን፣ በርካቶችም ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡ መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ንብረትም ወድሟል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ በተደረገባቸው ስድስት ወራት ውስጥ ለሦስት ጊዜ ማሻሻያ እንደተደረገበት ይታወሳል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...