Saturday, May 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዝንቅ‹‹እንዲህ ተውበናል!›› ካሮዎች በደቡብ ኢትዮጵያ

‹‹እንዲህ ተውበናል!›› ካሮዎች በደቡብ ኢትዮጵያ

ቀን:

ሐሳብ

ግራ ቀኝ ግራ

አይምሮዬ – አሞራ

- Advertisement -

      በሮ – በሮ – በሮ

      . . . ሔዶ

ከጠሐይ – ተማግዶ

      በእሳት ተበልቶ

      አመድ ይሆንና

      ያቦን ይጀምራል

      ወዜን ይፈጭና፡፡

  • አገኘው አዳነ ድልነሳው ‹‹ጨለማን ሰበራ›› (1987)

*********

በማሳቹሰትስ የውኃ ማጣሪያ ላይ ለደረሰ የእሳት አደጋ ወፎች ተኮነኑ

በማሳቹሰትስ በሚገኘው የውኃ ማጣሪያ ሕንፃ ላይ ከሳምንታት በፊት ለተከሰተው የእሳት አደጋ ወፎች ተወቀሱ፡፡ በውኃ ማጣሪያው ሥፍራ የወፍ ጎጆ ቀልሰው የሚኖሩ ወፎች የውኃ ማጣሪያ አካባቢ የሚገኙ የኤሌክትሪክ ሽቦ መሸፈኛ ፕላስቲኮችን በማኘካቸውና ሽቦው ግልጽ በመሆኑ ሳቢያ፣ ከወፍ ጎጆዎቹ ጋር ተገናኝቶ እሳት ፈጥሯል ተብሏል፡፡ የውኃ ማጣሪያው ከፊል ሕንፃ በእሳቱ የወደመ ሲሆን፣ ማጣሪያውም ለዓመት ያህል አገልግሎት ላይሰጥ ይችላል መባሉን አሶሸየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

*******

በቸኮሌት ኬክ የተሠራው የትራምፕ ምስለ ቅርፅ በቱርክ የቸኮሌት ፌስቲቫል ቀረበ

በቱርክ ኢስታንቡል በተከበረው የቸኮሌት ፌስቲቫል ላይ የአሜሪካው ፕሬዚንት ዶናልድ ትራምፕ ምስለ ቅርፅ በቸኮሌት ኬክ ተሠርቶ ለዕይታ በቅቷል፡፡

በቱርካዊቷ ሼፍ ቱባ ጊካሊ የተሠራው የትራምፕ ምስለ ቅርፅ፣ ሁለት ቀናት የፈጀ ሲሆን፣ ያለበሰቻቸውን ኮትና ያደረጉትን ከረባት ለምግብ ከሚውሉ የቸኮሌትና ኬክ ግብዓቶች የተሠሩ እንደነበሩ አሶሸየትድ ፕሬስ አስፍሯል፡፡

ጊካሊ እንደምትለው፣ የትራምፕን ዝና በተደጋጋሚ በተለያዩ ሚዲያዎች መስማቷ፣ በፌስቲቫሉ ምስለ ቅርፃቸውን ይዛ ብቅ እንድትል አድርጓታል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ማብቂያ በኢስታንቡል የመከላከያ ኃይል ሙዚየም በተከናወነው የቸኮሌት ፌስቲቫል፣ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ መሪ ሟቹ ኔልሰን ማንዴላ፣ የጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንጌላ መርከል እንዲሁም በ40 ዓመቱ በጥይት የተገደለው እንግሊዛዊው የሮክ ኤንድ ሮል አቀንቃኝና የቢቲልስን ባንድ ካቋቋሙት አንዱ ጆን ሌነን ምስለ ቅርፅ በጊካሊ ተሠርቶ ቀርቧል፡፡ ከሁሉም ሥራዎች ሦስት ሳምንት የፈጀባትና ፈታኝ የነበረው የጀርመኗን አንጌላ መርከል ምስለ ቅርፅ መሥራት እንደነበር ጊካሊ ተናግራለች፡፡

*********

የጆን ኤፍ ኬኔዲ ባለቤት ከእንግሊዙ ዲፕሎማት ጋር የተጻጻፉት የፍቅር ደብዳቤ በ98,500 ፓውንድ ተሸጠ

እ.ኤ.አ. በ1963 የተደገሉት የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆን ኦፍ ኬኔዲ ባለቤት ጃኪ ኬኔዲ በወቅቱ በአሜሪካ የእንግሊዝ አምባሳደር ከነበሩበት ዴቪድ ጎር ለቀረበላቸው የጋብቻ ጥያቄ ‹‹አይሆንም›› ብለው የመለሱ ደብዳቤ በ98,500 ፓውንድ መሸጡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ የጆኔፍ ኬኔዲ የቅርብ ጓደኛና ቤተሰብ የነበሩት አምባሳደር ጎር፣ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ከሞቱ ከአራት ዓመት በኋላ ነበር ለጃኪ የጋብቻ ጥያቄ ያቀረቡት፡፡

እ.ኤ.አ. በ1968 ድብቅ ጋብቻ እንዲፈጽሙ አምባሳደር ጎር ለጃኪ ሐሳብ ያቀረቡ ቢሆንም፣ ጃኪ በጻፉት ደብዳቤ ‹‹በጣም እንተዋወቃለን፣ ብዙ ነገሮችን አብረን ተካፍለናል፣ አብረንም አጥተናል፡፡ አሁን አንተ እንዳሰብከው ዓይነት ባይሆንም በእኔና አንተ መካከል ያለው ፍቅርና ሕመም መቼም አይበጠስም፣ አንተ ልክ እንደምወደው ወንድሜ ነህ፡፡ አሠልጣኜ ነህ፡፡ እኔ የማውቀው አንተ ለጆን ኤፍ ኬኔዲ ያለህ ያልተነካ ፍቅርና ስሜት ለኔም እንደሆነ ነው፤›› ሲሉ አስፍረዋል፡፡ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ከተገደሉና ጃኪም በ1968 ሌላ ባል እስኪያገቡ በነበሩበት ዓመታት በጃኪና በጎር መካከል 18 የደብዳቤ ልውውጦች የተደረጉ ሲሆን፣ እነዚህም ለጨረታ ቀርበው በ98,500 ፓውንድ ተሸጠዋል፡፡ ጎር እ.ኤ.አ. በ1985 የሞቱ ሲሆን፣ የደብዳቤ ስብስቦቹን ለጨረታ ያቀረበው የልጅ ልጃቸው ነው፡፡

******

ካምቦዲያ የእናት ጡት ወተት ሽያጭን አገደች

የካምቦዲያ እናቶች የጡት ወተታቸውን ለልጆቻቸው ከማጥባት ይልቅ ለአሜሪካ ሴቶች ይሸጡ የነበረ ቢሆንም፣ ሰሞኑን ዕገዳ ተጥሎባቸዋል፡፡ ላለፉት ሁለት ዓመታት ካምቦዲያውያቱ የጡት ወተታቸውን አምብሮሲያ ላብስ ለተባለ ኩባንያ ሲሸጡ የከረሙ ሲሆን፣ ኩባንያውም ወተቱን አቀነባብሮ ለአሜሪካ ገበያ ያቀርብ ነበር፡፡ በአሜሪካም በቂ የጡት ወተት የሌላቸው ሴቶች ለልጆቻቸው ይሸምቱት ነበር፡፡

ዩኒሴፍ የእናት ጡት ወተት መሸጥ ችግረኛ የሆኑ እናቶችን መበዝበዝ ነው ማለቱን ተከትሎና የካምቦዲያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከእናት ጡት ወተት ባለፈ የሰውነት አካል መቸብቸቡን ደርሼበታለሁ በማለቱ የካምቦዲያ መንግሥት እናቶች የጡት ወተታቸውን እንዳይሸጡ አግዷል፡፡

ብዙ አገሮች የወተት ባንክ ያላቸው ሲሆን፣ ባንኮቹ የሚረዱትም የእናት ጡት ላጡ ልጆች ነው፡፡ አንዳንድ ድረ ገጾችና ኔትወርኮች ደግሞ የእናት ጡት ወተት ይሸጣሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...