Monday, March 20, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየአፍሪካ የዞን አራት የቼዝ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል

የአፍሪካ የዞን አራት የቼዝ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል

ቀን:

የአፍሪካ ዞን አራት (4.2) የቼዝ ሻምፒዮና መጋቢት 23 ቀን 2009 ዓ.ም. በጅማ ከተማ ይጠናቀቃል፡፡ ከመጋቢት 24 ቀን ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው ሻምፒዮናው በዞኑ ተወዳዳሪዎች መካከል ከፍተኛ ፉክክር ሲደረግበት ቆይቷል፡፡

በጅማ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተው ውድድሩ የግብፅ፣ የዑጋንዳና የኬንያ ተሳታፊዎች ከፍተኛ ፉክክር ማድረግ ችለዋል፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ 13 አገሮች ሲያሳትፍ የቆየው ሻምፒዮናው በቼዝ ውድድር ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸው (ፊዴ ማስተር የሆኑ) እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፉ ተወዳዳሪዎችም ተገኝተውበታል፡፡

የግል የበላይነት በሚፈለገው የቼዝ ውድድር የኢትዮጵያ ተወዳዳሪዎች ከ4.5 በላይ ውጤት በማምጣት የማስተርስ ደረጃን ለመጎናጸፍ ያደረጉት ፉክክር ትኩረትን ስበዋል፡፡

በውድድሩ የረጅም ጊዜ ልምድ እንዳላቸው የተነገረላቸው የቀድሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ሳህሉ ገብረወልድ በሻምፒዮናው ላይ ተሳታፊ ነበሩ፡፡

በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑት የኢንተርናሽናል ማስተር ማዕረግና የገንዘብ ሽልማት ከማግኘታቸውም በተጨማሪ፣ አፍሪካን ወክለው በዓለም የቼዝ ሻምፒዮና ላይ እንደሚካፈሉ ታውቋል፡፡ በጅማ ከተማ ውድድሩ ማካሄዱ ለስድስት ልጆች ዕድል መፍጠሩና በሻምፒዮናው ላይ መሳተፍ መቻላቸው ትልቅ ልምድ እንዲያገኙ እንደረዳቸው፣ የጅማ ከተማ የቼዝ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ተሾመ በቀለ ለሪፖርተር ገልፀዋል፡፡

በጅማ ከተማ የሚገኙት የቼዝ ተወዳዳሪዎች በተለያየ ጊዜ ዞናቸውንና ክልላቸውን በመወከል አመርቂ ውጤት ያመጡ ሲሆን፣ በዚህ ውድድር ላይ መሳተፋቸው ትልቅ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡

በዞን 4.2 በሻምፒዮና ላይ ከፍተኛው ውጤት ግብፅ የበላይነት ሲኖራት ዑጋንዳና ታንዛኒያ ተከታይ  አገሮች ናቸው፡፡

ቼዝ በዓለም ላይ የሚገኙ የቤት ውስጥ ስፖርቶች አንዱ ሲሆን ከግማሽ ቢሊዮን በላይ አዘውታሪዎችም እንዳሉት ይነገራል፡፡ ከጨዋታ ባሻገርም የሰውን አዕምሮን የማስፋት አቅም እንዳለውና በተለይ ሕፃናት ትምህርታቸው ላይ ትኩረት እንዲሰጡ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግላቸው ይነገራል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ዜጎች የተፈተኑበት የኑሮ ውድነት

በኢትዮጵያ በየጊዜው እየተባባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት የበርካታ ዜጎችን አቅም...

በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደረጉ ድጋፎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው ተጠየቀ

በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደረጉ ድጋፎች ዘላቂነት እንዲኖራቸውና በተቀናጀ መልኩ...

ወደ ኋላ የቀረው የሠራተኞች ደኅንነት አጠባበቅ

በአበበ ፍቅር ለሠራተኞች የሚሰጠው የደኅንነት ትኩረት አናሳ በመሆኑ በርካታ ዜጎች...