በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም በሕገወጥ መንገድ 551,771 ዶላር ወደ ውጭ ለማሸሽ ሲሞክሩ ድንበር ላይ በተያዙ ግለሰቦች ላይ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
በዚህም መሠረት ፍርድ ቤቱ ገንዘቡን ሲያስተላልፉ በተያዙት በአቶ ሀበኔ አረብኑር ላይ የስምንት ዓመት እስራትና የ100 ሺሕ ብር ቅጣት ሲወስን፣ በአቶ ሐመድ መሐመድ ላይ ተመሳሳይ እስራትና የገንዘብ መቀጮ ውሳኔ ማስተላለፉን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ የተያዘው 551,771 ዶላር ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች እንዲውል ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ገቢ መሆኑን አስረድተዋል፡፡