Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየጀርባ አጥንት መጣመም ችግር ላለባቸው 80 ወጣቶች የማቃናት ሥራ ተከናወነላቸው

የጀርባ አጥንት መጣመም ችግር ላለባቸው 80 ወጣቶች የማቃናት ሥራ ተከናወነላቸው

ቀን:

  • ‹‹በዓለም ከፍተኛ የጀርባ አጥንት መጣመም የሚታየው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው››

የአዲስ አበባ ቃጠሎና ድንገተኛ ሆስፒታል (አቤት)፣ በኅብለ ሰረሰር ቀዶ ሕክምና የጀርባቸውን አጥንት የማቃናት አገልግሎት በነፃ እንዲያገኙ ከመዘገባቸውና የጀርባ አጥንት መጣመም (ስኮላይሰስ) ችግር ካለባቸው 2,400 ታዳጊ ወጣቶች መካከል ለ80 ያህሉ አገልግሎቱን መስጠቱንና ሕክምናውም ቀጣይ መሆኑን አስታወቀ፡፡

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ሥር የሚገኘው ይኼው አቤት ሆስፒታል ጥቅምት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፣ በኢትዮጵያ በዓይነቱ ልዩና የዘመኑን ቴክኖሎጂ የተላበሰውን ሕክምና የጀርባ አጥንት መጣመም ላለባቸው ወጣቶች ተደራሽ ያደረገው ከግብፅ ኮፒቲክ ቤተ ክርስቲያን ጋር በመተባበር ነው፡፡

ቀዶ ሕክምናውንም ያካሄደው በሰሜን አሜሪካ ሺካጎ ከተማ ከሚገኘው ሊዮላ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የተውጣጣውና በጠቅላላው አሥር የሚሆኑ ቀዶ ሐኪሞችን፣ ሰመመን ሰጪዎችንና ነርሶችን ያቀፈው ቡድን ነው፡፡

- Advertisement -

ቡድኑ የቀዶ ሕክምናውን ያከናወነው ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ በየሦስት ወራት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ የመጀመርያውን፣ የሁለተኛውና የሦስተኛውን ዙር ቀዶ ሕክምና እስካለፈው ዓመት ድረስ እንዳገባደደ፣ አራተኛውን ዙር ተመሳሳይ ሕክምና ደግሞ ከጥቅምት 1 ቀን እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ በጥሩ ሁኔታ እንዳጠናቀቀና አምስተኛውን ዙር ሕክምናም በቅርቡ እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሺካጎ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በስኮላይሰስ ስፔሻሊቲ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና የተቸራቸው፣ በትውልድ ግብፃዊ በዜግነት አሜሪካዊ የሆኑና የቡድኑ መሪ ፕሮፈሰር ከማል ኢብራሂም እንደገለጹት፣ ሳንዲያጎ የሚገኘው ቤዚን ፋውንዴሽን ኦርጋናይዜሽን ለቀዶ ሕክምና አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን በመለገስና የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ለቡድኑ ተልዕኮ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

ኒውዮርክ የሚገኘው ጄዊሽ ጆይንት ዲስትሪቢውሽን ኮሚቴ ኦርጋናይዜሽን ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ የስኮላይሰስ ችግር ያለባቸውን ወገኖች በመለየት እንደተባበረ፣ የግብፅ ኮፒቲክ ቤተ ክርስቲያን ዕገዛም ላቅ ያለ እንደነበር አስታውቀዋል፡፡

ቡድኑ ሁለት ዓላማዎች እንዳሉት፣ አንደኛው ችግሩ ላለባቸው ወገኖች የቀዶ ሕክምና አገልግሎት መስጠት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ለኢትዮጵያውያን የቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች የስኮላይሰስ ስፔሻሊቲ ሥልጠና መስጠት ነው፡፡ በዚህም የተሳካ ውጤት እንደተገኘ ነው ፕሮፈሰሩ የተናገሩት፡፡

የአንጎልና የኅብለሰረሰር ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስትና የአቤት ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ብርሃኑ ኃይለሚካኤል (ዶ/ር)፣ ‹‹በዓለም ከፍተኛ የሆነ የጀርባ አጥንት መጣመም (ሰኮላይሰስ) ችግር የሚታየው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ይህም ሆኖ ግን እስካሁን እሳቸውና ሌሎችም የሥራ ባልደረቦቻቸው ከቡድኑ ጋር አብረው በመሥራታቸው ጠቃሚ ሙያ መቅሰማቸውን ገልጸው፣ በቀሰሙትም ሙያ መሠረት ራሳቸውን ችለው የተጠቀሰውን ቀዶ ሕክምና አገልግሎት መስጠት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሐኪሞችንም የማሠልጠን ዓላማ ሰንቀው እንደተነሱ አስረድተዋል፡፡

የስኮላይሰስ መንስዔ ምንድነው? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ዶ/ር ብርሃኑ ሲመልሱ፣ ‹‹የበሽታው መንስዔ ሁለት ነው፡፡ አንደኛው ምክንያቱ የማይታወቅ (ሃዲዮፖሲስ) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ኢንፌክሽን ነው፡፡ ለዚህም የአጥንት ቲቢን ማንሳት ይቻላል፡፡ ቲቢው በሕክምና ቢድንም አጥንትን የማጣመምና የማጉበጥ ችግር ያስከትላል፤›› ብለዋል፡፡

የጀርባ አጥንት መጣመም ወይም መጉበጥ ችግር በአዋቂዎችም ላይ እንደሚታይ፣ ነገር ግን ለታዳጊ ወጣቶች ቅድሚያ ሊሰጥ የቻለው በሁለት ምክንያቶች መሆኑን፣ አንደኛው ምክንያት ወጣቶች ባደጉ ቁጥር የአጥንታቸው መጉበጥና መጣመም እየባሰ ስለሚሄድ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ የትምህርት ቤት ጓደኞቻቸው ጀርባህ ጎበጠ፣ ተጣመመ፣ ወዘተ በማለት እያፌዙባቸው ከፍተኛ የሆነ የሥነ ልቦና ችግር ላይ በመውደቃቸውና በዚህም ተነሳ ትምርታቸውን እስከማቋረጥ በመድረሳቸው መሆኑን ዶ/ር ብርሃኑ አመልክተዋል፡፡  

የኮሌጁ የሕክምና ዘርፍ ምክትል ፕሮቨስት ብርሃኔ ረዳኢ (ዶ/ር)  የግብፅ መንግሥት፣ ኮፒቲክ ቤተ ክርስቲያንና በኢትዮጵያ የግብፅ ኤምባሲ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ጋር አብረው መሥራት ከጀመሩ ሰባት ዓመታት እንደሆናቸውና በዚህም ኮሌጁ አሁን ለደረሰበት ዕድገት ባለውለታዎች ለመሆን እንደበቁ አመልክተዋል፡፡

ባለውለታቸውም ከሚገለጽባቸው ሥራዎቻቸው መካከል ቀደም ሲል ስድስት የዲያሌሲስ ማሽኖችን፣ አልትራሳውንድና ኢንዶስኮፒ የተባሉ የሕክምና መሣሪያዎችን በነፃ ማበርከታቸው ይገኝበታል፡፡ ከዚህም ሌላ የልብ ሕክምና ማዕከል ሥራ እንዲጀምርና 20 ታካሚዎችም ተገቢውን ሕክምና እንዲያገኙ ማድረጋቸው፣ የሕክምና ባለሙያዎችን በአገራቸውና ወደ ሌላም አገር ልከው በማሠልጠናቸውና፣ ታዋቂ የሆኑ የውጭ ሐኪሞች እዚህ መጥተው የሕክምና አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችሉ ሁኔታዎች ማመቻቸታቸው ካከናወኗቸው ተግባራት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ የግብፅ አምባሳደር ሚስተር አቡበከር ሀፍሚ ሁለቱ አገሮች በተለይም በጤናው ዘርፍ በጋራ መሥራታቸው የተጀመረውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የበለጠ ያጠናክረዋል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡   

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...