Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአሜሪካ ኮንግረስ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ በቀረበለት የውሳኔ ሐሳብ ድምፅ እንዲሰጥበት...

የአሜሪካ ኮንግረስ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ በቀረበለት የውሳኔ ሐሳብ ድምፅ እንዲሰጥበት ተጠየቀ

ቀን:

የአሜሪካ ኮንግረስ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ በቀረበለት የውሳኔ ሐሳብ ላይ ድምፅ እንዲሰጥበት፣ በአሜሪካ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጥያቄ አቀረቡ፡፡

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾቹ ጥያቄያቸውን ለኮንግረሱ በደብዳቤ ያቀረቡት፣ ኮንግረሱ በውሳኔ ሐሳቡ ላይ ለመወያየት የያዘውን ቀነ ቀጠሮ ባልታወቀ ምክንያት በመቀየሩ መሆኑ ታውቋል፡፡

ኮንግረሱን በቀረበለት ኤችአር 128 በመባል በሚታወቀው የውሳኔ ሐሳብ ላይ እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 2 ቀን 2017 ለመወያየት ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም፣ ባልታወቀ ምክንያት ቀነ ቀጠሮው መሰረዙን የኮንግረሱ የጊዜ ሰሌዳ ያሳያል፡፡ ይህንን በመቃወም በኮንግረሱ ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር ደብዳቤ የጻፉት ዘጠኝ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በጋራ በመሆን ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እነዚህ ደብዳቤ የጻፉ ተሟጋቾች በአሜሪካ የአማራ ማኅበር፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሴንተር ፎር ጀስቲስ ኤንድ አካውንተቢሊቲ፣ ኢትዮጵያ ሒውማን ራይት ፕሮጀክት፣ ፎረም ሐውስ፣ ሒውማን ራይትስ ዎች፣ ኦሮሞ አድቮኬሲ አሊያንስ፣ ሶሊዳሪቲ ሙቭመንት ፎር ኤ ኒው ኢትዮጵያና ቶርቸር ኤንድ አቦሊሽን ሰርቫይቨርስ ሰፖርት ኮኦሊሽን የሚባሉ ናቸው፡፡

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾቹ በደብዳቤያቸው እንደገለጹት፣ ኮንግረሱ በውሳኔ ሐሳቡ ላይ ለመወያየት የያዘውን ቀጠሮ ያስተላለፈው የኢትዮጵያ መንግሥት የውሳኔ ሐሳቡ ላይ ኮንግረሱ ድምፅ የሚሰጥ ከሆነ፣ በፀረ ሽብርተኝነት ላይ ከአሜሪካ ጋር የሚኖረውን ትብብር ሊያቋርጥ ይችላል ከሚል ሥጋት ነው፡፡

በውሳኔ ሐሳቡ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት እንዲከበርና ሁሉንም ያማከለ መንግሥት እንዲፈጠር ጥሪ የሚያደርግ በመሆኑ ሊስተጓጎል አይገባም በማለት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾቹ ጠይቀዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

ኤችአር 128 የተሰኘው የውሳኔ ሐሳብ ስሚስ ክርስቶፈር በተባሉ የኮንግረሱ አባል አማካይነት እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2017 የመነጨ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የውሳኔ ሐሳቡ ከዓመታት በፊት በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ተከስቶ በነበረው ተቃውሞ የመንግሥት የፀጥታ አካላት ግድያ መፈጸማቸውን፣ የፖለቲካ አቀንቃኞች፣ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሐሳባቸውን በመግለጻቸው ብቻ መታሰራቸውን፣ የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ የፖለቲካ ተቀናቃኞችን ለማፈን ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን በመጥቀስ ያወግዛል፡፡

ተቃዋሚዎች ሐሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲያቀርቡ፣ እንዲሁም የመንግሥት ታጣቂዎች ኃይል ከመጠቀም እንዲቆጠቡም ይጠይቃል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎችን ሰብዓዊ መብት የሚያከብርና የማያስከብር ከሆነ፣ የአሜሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ በድጋሚ እንዲያጤን፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተሳተፉ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናትና ከእነሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣል ይጠይቃል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ይህ የውሳኔ ሐሳብ እንዳይፀድቅ የውትወታ ተቋም ቀጥሮ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት ደግሞ፣ የውሳኔ ሐሳቡ ከዚህ በዘለለ መራመድ አይችልም፡፡ ‹‹አሜሪካ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ሐሳባቸውን የመግለጽ መብት አላቸው፤›› ሲሉም ጉዳዩ ከመደመጥ መብት እንደማያልፍ ሞግተዋል፡፡

‹‹የውሳኔ ሐሳቡ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለኮንግረሱ በድጋሚ ሲቀርብ የሚሆነውን ያኔ እናያለን፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡

ኤችአር 128 በአንድ የኮንግረሱ አባል የቀረበ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት የ71 የኮንግረሱን አባላትን ድጋፍ ማግኘት እንደቻለ ታውቋል፡፡  

ይህ ሰነድ በኮንግረስ እጅ በሚገኝበት ወቅት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ የተቃውሞ ሠልፎች ተደርገዋል፡፡ አብዛኛዎቹ በሰላማዊ ሁኔታ የተጠናቀቁ ቢሆንም፣ በተወሰኑት ላይ የሰው ሕይወት አልፏል፡፡ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡

በቅርቡ የአሜሪካ ሴኔት አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝንና የክልክ ፕሬዚዳንቶችን በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ማነጋገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡  

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...