የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) በዚህኛው በጀት ዓመት ምንም ዓይነት ተጨማሪ በጀት እንደማይኖር ለዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ተናገሩ፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች የፕሮግራም በጀት አሠራርን በደንብ እንዲተገብሩም ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች የበጀት አጠቃቀማቸውን ለማየትም የባለፈውን ዓመት የበጀት ሪፖርታቸውን እንዲያቀርቡም ተጠይቀዋል፡፡
በተለያዩ ጊዜያት የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በሚያቀርባቸው የኦዲት ሪፖርቶች ውስጥ በተወቃሽነት ሰፊውን ስፍራ የሚዙት ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከመንገድ ቀጠጥሎ በ2010 በጀት ዓመት ከተመደበው 321 ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ 23 በመቶውን በጀት በማግኘት ትልቁን ድርሻ ይዘዋል፡፡