Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየብሮድካስት ባለሥልጣን ሚዲያው አደገኛ አዝማሚያዎች ይታዩበታል አለ

  የብሮድካስት ባለሥልጣን ሚዲያው አደገኛ አዝማሚያዎች ይታዩበታል አለ

  ቀን:

  የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘርዓይ አስገዶም በብሮድካስት ሚዲያው የሚታይ አሳሳቢ ሁኔታ አለ አሉ፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ያሉት በአገሪቱ እየታየ ያሉ ግጭቶችን ሚዲያው የሚዘግብብትን መንገድ በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው፡፡

  ሚዲያዎች ጠንካራ ባለመሆናቸው ለማኅበራዊ ሚዲያው የተጋለጡ ናቸው ብለው፣ ከግሉም ሆነ ከሕዝብ ሚዲያው የሚታዩ አደገኛ የሆኑ አዝማሚያዎች እየተስተዋሉ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

  ሰሞኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ የተሳሳተ ዘገባ ያቀረቡ የሚዲያ ተቋማትን በሕግ ለመጠየቅ እንቅስቃሴ ይጀመራል ያሉት የግል አስተያየታቸው ነው ያሉት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር፣ አንድ ሚዲያ እንዲህ አይነት ጥፋት ከተገኘበት እንዴት፣ በማንና ምን ይቀጣል የሚለው የሚወሰነው በፍርድ ቤት እንጂ በሌላ የመንግሥት ተቋም አይደለም ብለዋል፡፡

  የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ኢኤንኤን የቴሌቪዥን ጣቢያንና ዛሚ ሬድዮ ጣቢያን የተሳሳተ ዘገባ በማስተላለፍ እንደወቀሷቸው ይታወሳል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...