Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናዓቃቤ ሕግ በጦማሪያንና በጋዜጠኞች ላይ ያቀረበውን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ በድጋሚ ታዘዘ

ዓቃቤ ሕግ በጦማሪያንና በጋዜጠኞች ላይ ያቀረበውን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ በድጋሚ ታዘዘ

ቀን:

በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው ከ245 ቀናት በላይ በእስር ላይ በሚገኙት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ላይ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተውን ክስ እንዲያሻሽል ፍርድ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ታኅሳስ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ የጋዜጠኞቹንና ጦማሪያኑን የክስ ሒደት እየመረመረው የሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ ታኅሳስ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. መዝገቡን ቀጥሮ የነበረው፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ አሻሽሎ ያቀረበውን ክስ፣ ተጠርጣሪዎቹ ‹‹ምንም የተሻሻለ ነገር የለም፡፡ ፍርድ ቤት እንዲያሻሽል የሰጠውን ትዕዛዝ ባከበረ መንገድ አላሻሻለም፤›› በማለት ያቀረቡትን የድጋሚ መቃወሚያ መርምሮ ብይን ለመስጠት ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ቀደም ባለው ችሎት በሰጠው ብይን መሠረት ክሱ መሻሻል አለመሻሻሉንና ተጠርጣሪዎቹ ያቀረቡትን መቃወሚያ መመርመሩን አስታውቋል፡፡ በመሆኑም ዓቃቤ ሕግ እንዲያሻሽል ብይን ከተሰጠባቸው ከስድስት በላይ ነጥቦች አሻሽሎ ያቀረበው የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 አንቀጽ 4 በመጥቀስ የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈጸም አቅደዋል፣ ተዘጋጅተዋል፣ አሲረዋል፣ አነሳስተዋል በማለት ከሶ የነበረውን፣ ወደ አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ (2) በመቀየር የኅብረተሰቡን ወይም የኅብረተሰቡን ክፍል ደኅንነት ወይም ጤና ለከፍተኛ አደጋ አጋልጠዋል በማለት ነው፡፡ በተጨማሪም በተመሳሳይ አንቀጽ 3 አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4)ን በመጥቀስ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል በማለት ክሱን አሻሽሎ ማቅረቡን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በህቡዕ ተደራጅተው የሥራ ክፍፍል ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ በመጥቀሱ ማን ምን የሥራ ድርሻ እንዳለው እንዲገለጽ፣ የግንቦት 7 እና የኦነግን ዓላማና ተልዕኮ ስትራቴጂያቸው አድርገው ይንቀሳቀሱ እንደነበር ዓቃቤ ሕግ በክሱ በመግለጹ፣ እንዴት አድርገው ይንቀሳቀሱ እንደነበር በግልጽ እንዲያስረዳ፣ ናትናኤል የተባለው ተጠርጣሪ 48,000 ብር መቀበሉ በክሱ በመገለጹ፣ ከማንና እንዴት እንደተቀበለ አብራርቶ እንዲያቀርብ፣ ቡድንና ድርጅት የሚለውን ለይቶና በስም ጠቅሶ አሻሽሎ እንዲያቀርብ የተሰጠውን ትዕዛዝ፣ ዓቃቤ ሕግ አሻሽሎ አለማቅረቡን ማረጋገጡን ፍርድ ቤቱ በብይኑ አስታውቋል፡፡ በመሆኑም ዓቃቤ ሕግ በብይኑ መሠረት በቶሎ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ለጥር 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...