Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከአምስት የሚበልጡ የውጭ አገር ዜጎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቆመ

ከአምስት የሚበልጡ የውጭ አገር ዜጎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቆመ

ቀን:

ምክንያቱ በግልጽ ባይታወቅም ቁጥራቸው ከአምስት የሚበልጡ የውጭ አገር ዜጎች ታኅሳስ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ ቦሌ ቲኬ ሕንፃ አካባቢ በፖሊስ ተይዘው መወሰዳቸው ተጠቆመ፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ቻይና አፍሪካ አደባባይ ፊት ለፊት በሚገኘው ቲኬ ሕንፃ ላይ በሚገኘው ሰንበርድ ካፌ አጠገብ ድንገት በተነሳ ግርግር በአካባቢው ለተወነሰ ጊዜ ውክቢያ ተፈጥሮ፣ አካባቢው በሰዎች ተሞልቶ እንደነበር በሥፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ ቁጥራቸው ከአምስት ከሚበልጡ ቻይናውያን ከሚመስሉ የውጭ ዜጎች ጋር ግብግብ ፈጥረው የነበረ ሲሆን፣ ፖሊሶቹ ግለሰቦቹ በሰው ሕይወት የተጠረጠሩ እንደሆኑ ሲገልጹ ሕዝቡ ሊረጋጋ መቻሉን የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ የውጭ ዜጎቹን ፖሊስ የትኛው ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዳቸው ባይታወቅም ይዘዋቸው እንደሄዱ የገለጹት እማኞቹ፣ ወደ ፌዴራል ወንጀል ምርመራ (ማዕከላዊ) ሳይወስዷቸው እንዳልቀሩ ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡ የውጭ ዜጎቹ በሰው ነፍስ ስለሚፈለጉ መሆኑን የያዟቸው ፖሊሶች ሲናገሩ ተሰምቷል በመባሉ ሪፖርተር ጉዳዩን ለማጣራት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን የጠየቀ ሲሆን፣ አንድ የኮሚሽኑ ባልደረባ ወደ ኮሚሽኑ ምንም የመጣ ነገር የለም ብለዋል፡፡ የሞተ ሰው ቢኖር ኖሮ የሚመለከተው ኮሚሽኑን በመሆኑ ወደነሱ ይመጣ እንደነበር፣ ምናልባት ፖሊሶች አባባሉን የተጠቀሙት በወቅቱ የተፈጠረውን ግርግር ለማስቆም እንጂ እንደሚባለው የነፍስ ጉዳይ እንዳልመሰላቸው አስረድተዋል፡፡ ከፌዴራል ወንጀል ምርመራ (ማዕከላዊ) ምክንያቱን ለማወቅ የተደረገው ሙከራ ባይሳካም፣ ዜጎቹ የተጠረጠሩት በሰው ነፍስ ሳይሆን በሌላ ጉዳይ ነው ተብሏል፡፡ ፖሊስ ዝርዝሩን ከመግለጽ ተቆጥቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...