Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየአበበ ቢቂላ ስታዲየምና ፕሪሚየር ሊጉ አልተግባቡም

የአበበ ቢቂላ ስታዲየምና ፕሪሚየር ሊጉ አልተግባቡም

ቀን:

በአገሪቱ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦችን ጨምሮ በርካታ ክለቦች ከምሥረታ ጊዜያቸው አንስቶ አብሯቸው የዘለቀው የመዋቅር ክፍተት ዛሬም ለአንድ ክለብ መሠረታዊ ተብለው በሚጠቀሱ ማዘውተሪያና በመሳሰሉት እጥረቶች ተጠፍረው እንዲገኙ ምክንያት ሆኖ መዝለቁ እየተነገረ ይገኛል፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኙ የፕሪሚየር ሊግና ብሔራዊ ሊግ ክለቦችን በብቸኝነት ሲያስተናግድ የቆየው የአዲስ አበባ ስታዲየም በዕድሳት ምክንያት መዘጋቱን ተከትሎ የውድድር ዓመቱ ጨዋታዎች የተፈጥሮ ሳር በለበሰው የአበበ ቢቂላ ስታዲየም እየተከናወነም ነው፡፡ ባለፈው ቅዳሜና እሑድ የፕሪሚየር ሊጉን አሥረኛ ሳምንት ጨዋታ ያስተናገደው የአበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ በሰው ሠራሽ ሳር ምክንያት ተጨዋቾች መጎዳታቸውን አሠልጣኞችና ተጨዋቾች ይናገራሉ፡፡ ከአምስትና ከስድስት አሠርታት በላይ ዕድሜን ያስቆጠሩት እነዚሁ ክለቦች በትልቁ ቀርቶ አሥር ሺሕና ከዚያም በላይ ተመልካቾችን ማስተናገድ የሚችል ስታዲየም መገንባት ሳይችሉ ቆይተው ዛሬ ይህንን ቢሉ ሊያስደንቅ እንደማይገባ በሌላ በኩል የሚናሩ አሉ፡፡ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተጫውተው ውጤት ያገኙም ሆነ ውጤት ያጡ ክለቦች፣ ሰው ሠራሽ የለበሰ ስታዲየም ከፍተኛ ጉልበትና አቅም የሚጠይቅ እንደሆነ፣ ክለቦች ደግሞ ለሜዳው የሚሆኑ ከጫማ ጀምሮ የሚያሟሉ ባለመሆኑ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ቅዳሜ ታኅሣሥ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡናና ባለሜዳው መከላከያን ያገናኘው የአበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ ጨዋታው በሲዳማ ቡና 1 ለ0 አሸናፊነት ቢጠናቀቅም፣ የሁለቱ ቡድኖች አሠልጣኞች ከጨዋታው በኋላ ትኩረት ሰጥተው የተናገሩት ሜዳው ለተጨዋቾች ጉዳት ያለው መሆኑን ነው፡፡ የሲዳማ ቡናው አሠልጣኝ ዘለዓለም ሽፈራው በዕለቱ ጨዋታ አራት ተጨዋቾች ከሁለቱም ቡድኖች ከፍተኛ የሆነ ጉዳት እንዳስተናገዱ ገልጸዋል፡፡ የመከላከያው ገብረመድህን ኃይሌ በበኩሉ፣ እንደዚህ ዓይነት ሰው ሠራሽ ሳር የሚለብሱ ሜዳዎች ጉልበትና አቅም ከመጠየቃቸውም አልፎ ለሰው ሠራሽ ሳር የሚሆን መጫወቻ ጫማ ሳይቀር ይጠይቃሉ ብሏል፡፡ እሑድ ታኅሣሥ 26 ቀን 2007 ዓ.ም. ይኼው የአሥረኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ በ8 ሰዓት በአዲስ አሠልጣኝ መብራት ኃይልን የገጠመው ደደቢት 2 ለ0 ሲረታ፣ በ10 ሰዓት የተገናኙት ቅዱስ ጊዮርጊስና ዳሸን ቢራ ሲሆኑ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዳዋ ሆቴሳ ብቸኛ ጎል ነጥብ ይዞ ወጥቷል፡፡ ውጤቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ቀሪ ጨዋታ እየቀረው ፕሪሚየር ሊጉን 18 ነጥብ ይዞ ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ አስችሎታል፡፡ በብራዚላዊው አሠልጣኝ ዶ ሳንቶስ እየሠለጠነ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ በውድድር ዓመቱ አገሪቱን በመወከል በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ተሳታፊ ነው፡፡ ክለቡ በፕሪሚየር ሊጉ ያለውን የበላይነት አስጠብቆ፣ እግረ መንገዱን ለአኅጉራዊው ተሳትፎ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ቅርበት ያላቸው የክለቡ ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ ሆኖም ቡድኑ ከፊት ለፊቱ የሚጠብቀው አኅጉራዊው ተሳትፎ እንደተጠበቀ፣ በፕሪሚየር ሊጉ ባደረጋቸው የአሥር ሳምንታት ጨዋታ ውጤት ግን ብዙዎቹን የክለቡን ደጋፊዎችና አመራሮች አለማስደሰቱም እየተነገረ ይገኛል፡፡ ሰርቢያዊው የቅዱስ ጊዮርጊስ አሠልጣኝ ሰርዲዮቪች ሚሎቲን ሚቾ፣ ምንም እንኳ በአሁኑ ወቅት የምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ መሆናቸው ቢታወቅም፣ እሑድ ታኅሣሥ 26 ቀን 2007 ዓ.ም. ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዳሸን ቢራ ጋር ያረገውን ጨዋታ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተገኝተው ተከታትለውታል፡፡ የቀድሞ አሠልጣኝ ከጨዋታው ቀደም ብሎ ስታዲየም ሲደርሱ ከደጋፊው የተደረገላቸው የ‹‹እንኳን ደህና መጣህ›› ዓይነት አቀባበል ደመቅ ያለ ነበር፡፡ይኼው አሠልጣኙ የቀድሞ ክለባቸውን አስበው ይሆን? የሚልም ጥርጣሬ እንዳለም የሚናገሩ አሉ፡፡ በሌላ በኩል በክልል ከተሞች በተደረጉ የአሥረኛው ሳምንት ጨዋታች ወደ ወላይታ ድቻ ያቀናው ኢትዮጵያ ቡና ያለ ግብ ተለያይቶ ነጥብ ሲጋራ፣ በሜዳው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ያስተናገደው ሐዋሳ ከነማ 2 ለ0 ተሸንፏል፡፡ ወደ አዳማ ያቀናው ሙገር ሲሚንቶ ከአዳማ ከነማ ጋር 1 ለ1 ሲለያይ፣ በውድድር ዓመቱ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገው ወልዲያ ከነማ ወደ አርባ ምንጭ አቅንቶ በአርባ ምንጭ ከነማ 1 ለ0 ተሸንፎ ተመልሷል፡፡ በሚቀጥለው ቅዳሜና እሑድ 11ኛው ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በአበበ ቢቂላና በክልል ከተሞች ቀጥሎ ይውላል፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በላከው መርሐ ግብር መሠረት፣ ቅዳሜ ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም. በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በ8 ሰዓት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወላይታ ድቻ፣ በ10 ሰዓት መብራት ኃይል ከአዳማ ከነማ ይጫወታሉ፡፡ እሑድ ጥር 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ኢትዮጵያ ቡና ከመከላከያ ሲጫወቱ፣ በክልል ከተሞች ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና ከወልደያ ከነማ፣ አሰላ ላይ ሙገር ሲሚንቶ ከሐዋሳ ከነማ፣ አርባ ምንጭ ላይ አርባ ምንጭ ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ጎንደር ላይ ዳሸን ቢራ ደደቢትን ያስተናግዳል፡፡ ሁሉም የክልል ጨዋታ በተመሳሳይ 9 ሰዓት እንዳረጉም ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...

ግለሰብ ነጋዴዎችን በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ለማድረግ ያለመው ረቂቅ አዋጅ ተከለሰ

በምትኩ የንግድ ተቋማት በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ...

አሳርና ተስፋ!

ከቱሉ ዲምቱ ወደ ቦሌ ጉዞ ልንጀምር ነው፡፡ ገና ከመንጋቱ...