Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየቀድሞው የብሔራዊ ደኅንነት ኃላፊ ፀረ ሙስና ኮሚሽኑን ከፍተኛ ችግር ፈጥሮብኛል አሉ

የቀድሞው የብሔራዊ ደኅንነት ኃላፊ ፀረ ሙስና ኮሚሽኑን ከፍተኛ ችግር ፈጥሮብኛል አሉ

ቀን:

የብሔራዊ መረጃ ደኅንነትና አገልግሎት የቀድሞ ኃላፊ አቶ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሚካኤል በተጠረጠሩበት ወንጀል በቁጥጥር ሥር በዋሉበት ወቅት፣ በፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድንና በፌዴራል ፖሊስ በመረካከቢያ ሰነድ (ቬርቫል) ተመዝግበው የተወሰዱ ሰነዶቻቸው ሊመለሱላቸው ስላልቻሉ መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ እህት፣ ወንድማቸውንና ጓደኛቸውን ጨምሮ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በአንድ የክስ መዝገብ እንዲከላከሉ ብይን ከተሰጠ በኋላ፣ በብርበራ የተወሰዱባቸው 38 የሳይት ፕላን፣ የተለያዩ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢና ወጪ የተደረገባቸው 15 ሰነዶች፣ የተለያዩ ፍላሾች፣ ኦዲዮ፣ ቪዲዮ፣ አይፓዶች፣ ሞባይል ስልኮች፣ ለሜጋ ማተሚያ ቤት መጽሐፋቸውን ለማሳተም ገንዘብ የከፈሉባቸው ደረሰኞች፣ ለወጋገን ባንክ በሲፒኦ ለውኃ ሥራ የተከፈለበት ሰነድ፣ በአጠቃላይ 592 ሰነዶች ሊሰጧቸው እንዳልቻሉ ለፍርድ ቤት አመልክተዋል፡፡ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው፣ በወቅቱ ለምርመራ የወሰዷቸውን ሰነዶች የሚጠቅሙትንና የማይጠቅሙት ተለይተው በኩርቱ ፌስታል ተመልሰውላቸዋል፡፡ መርማሪዎች የሰጡትም ለአቶ ወልደ ሥላሴ ወንድም መሆኑን ቢናገሩም፣ አቶ ወልደ ሥላሴ በጠበቆቻቸው አማካይነት እንዳልተረከቡ ተናግረዋል፡፡ የመርማሪው ቡድን አባል ያልተመለሱትን ለመመለስም መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል፡፡ አቶ ወልደ ሥላሴ ለሦስት ጊዜያት እንደተፈተሹና በቬርቫል ተፈራርመው በምስክር ፊት ማስረከባቸውን የገለጹ ቢሆንም፣ የኮሚሽኑ መርማሪ አባል ግን ሁለት ጊዜ መሄዳቸውንና ለሁለተኛ ጊዜም የሄዱት ምን ያህል መጻሕፍት አሳትመው ምን ያህሉን እንደሸጡ ለማረጋገጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ በኩርቱ ፌስታል ሰነዶችን በምን አግባብ ሊመልሱ እንደቻሉ እንዲያስረዱ መርማሪውን ሲጠይቃቸው፣ አስፈርመው እንደሰጡ ከመናገር ባለፈ ሊያብራሩ አልቻሉም፡፡ አቶ ወልደ ሥላሴ ግን አለመረከባቸውን በተደጋጋሚ ተናግረዋል፡፡ ለወንድማቸው እንደተሰጠ የሚነገረውም ባዶ ሲዲ መሆኑንም አክለዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ቀሪውን እንዲረከቡና ሲረከቡም እየፈተሹ እንዲሆን እንዲያዝላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ሰነዶቹ ለእነ አቶ ወልደ ሥላሴ ለመከላከል ይጠቅማቸዋል የሚል እምነት እንዳለው ተናግሮ፣ በአግባቡ ሊያስረክቧቸው እንደሚገባም አሳስቧል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ የተረከባቸውና ለማስረከብ ፈቃደኛ የሆነባቸው ንብረቶች፣ ከፍተኛ የግል ባህሪ ያላቸው ዶክመንቶችና በአቶ ወልደ ሥላሴ በራሳቸው የሚስጥር ኮድ የታሠሩ መሆናቸውን የገለጹት ጠበቆቻቸው፣ ራሳቸው ቀርበውና አረጋግጠው እንዲረከቡ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ ሰነዶቹ ለሚያደርጉት የመከላከል ክርክር ስለሚጠቅሙ ለኮሚሽኑም ሆነ ሰነዱን ለያዘው አካል ጥብቅ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው አመልክተዋል፡፡ በኮሚሽኑ አሠራር ምክንያት የተፋጠነ ፍትሕ የማግኘት መብታቸውንም እየተፈታተነው መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ የአቶ ወልደ ሥላሴ እህት ወ/ሪት ሣራና ወንድማቸው አቶ ዘርዓይም ተመሳሳይ ችግር እንደገጠማቸው፣ ማለትም በብርበራ የተወሰዱባቸው ሰነዶች እንዳልተመለሱላቸው አመልክተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ የኮሚሽኑ መርማሪ የገለጻቸው ሰነዶችና ኤሌክትሮኒክ ዶክመንቶች በአስተዳደር በኩል እንዲመልስ፣ በኩርቱ ፌስታል ውስጥ ታስረው ተሰጥተዋል የተባሉትን ሰነዶች ሁሉም መኖር አለመኖራቸውን እያረጋገጡ እንዲረከቡ፣ የጠፋ ወይም የጎደለ ካለ በቀጣይ ትዕዛዝ እንደሚሰጥ በማስታወቅ ለጥር 8 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...