Monday, October 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊትውልደ እንዲሸጥ ታዘዘ ኢትዮጵያዊው የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤጀንሲን በስጦታ አስደመሙ

  ትውልደ እንዲሸጥ ታዘዘ ኢትዮጵያዊው የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤጀንሲን በስጦታ አስደመሙ

  ቀን:

  በአውስትራሊያ የሚኖሩት ትውልደ ኢትዮጵያዊ አገር ውስጥ የማይገኙና ኢትዮጵያ በጣሊያን ከመወረሯ ቀደም ብሎ የተነሱ የጂኦ ስፔሻል መረጃዎችን ለኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤጀንሲ አስረከቡ፡፡
  አቶ ግርማ አብርሃም የተባሉት ትውልደ ኢትዮጵያዊ በተጠናቀቀው ሳምንት በአዲስ አበባ በካርታ ሥራ ኤጀንሲ ቢሮ ተገኝተው 56 ቅጠል ካርታዎችን በወረቀትና በሶፍት ኮፒ ለኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሡልጣን መሐመድ አስረክበዋል፡፡
  በካርታዎቹ ላይ የሠፈሩት መረጃዎች የኢትዮጵያን ድንበሮች፣ የአዲስ አበባን ወሰንና የመሳሰሉትን የያዘ መሆኑን የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለሪፖርተር በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
  ካርታዎቹ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አካባቢ በዴይሊ ቴሌግራፍ ጋዜጣና በሌሎች የመገናኛ ብዙኃን ለሕዝብ ይደርሱ እንደነበር ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡
  መረጃዎቹ ከዚህ ቀደም በካርታ ሥራዎች ኤጀንሲ ያልነበሩ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሡልጣን፣ መረጃው ለታሪክ ተመራማሪዎችና ለፖሊሲ አውጪዎች የሚጠቅም መሆኑንና ሌሎች የኢትዮጵያ የጂኦ ስፔሻል መረጃዎች በሌሎች አገሮችም ሊኖሩ ስለሚችሉ የትውልደ ኢትዮጵያዊው ስጦታ ሌሎችን አስተማሪ ነው ብለውታል፡፡
  ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ ግርማ በበኩላቸው፣ ‹‹ለአገሬ ያበረከትኩት መረጃ በመሆኑና ለታሪክ ተመራማሪዎችና ለፖሊሲ አውጪዎች የሚጠቅም በመሆኑ ደስ ብሎኛል፤›› ብለዋል፡፡
  ይህ በእንዲህ እንዳለ ኤጀንሲው በአገሪቱ ዘጠኙም ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ የሚገኙ 409 የሚሆኑ የተጐዱ ተራራማ ቦታዎች ካርታ ሠርቶ ለአካባቢ ጥበቃና ደን ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት ማስረከቡን አስታውቋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img