Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ያቋቋመችው የቴክኒክ ኮሚቴ ስምምነት ላይ መድረስ አልቻለም

ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ያቋቋመችው የቴክኒክ ኮሚቴ ስምምነት ላይ መድረስ አልቻለም

ቀን:

ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ያቋቋሙት የጋራ ቴክኒክ ኮሚቴ ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት በመምረጥ ሒደት ላይ መግባባት አለመቻሉ ተሰማ፡፡ ከእያንዳንዳቸው አገሮች አራት ባለሙያዎች ተወክለውበት የተቋቋመው የጋራ ኮሚቴ ከምሥረታው ጀምሮ የነበሩ ሁለት ስብሰባዎችን በተቀላጠፈ የመግባባት ስሜት ቢጨርስም፣ ቀጣዩ ስብሰባን ግን በተመሳሳይ መከናወን አለመቻሉን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ኮሚቴው የተቋቋመበት ምክንያት ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያን ታላቁ የህዳሴ ግድብን በኢትዮጵያ ሐሳብ አቅራቢነት ያጠናው ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን፣ ሦስቱ አገሮች በጋራ እንዲተገብሯቸው ያላቸውን ሁለት ምክረ ሐሳቦች ተግባራዊ ለማድረግ ነው፡፡ በዚህ መሠረት የተቋቋመው የጋራ ኮሚቴ በመጀመሪያው የአዲስ አበባ ጉባዔው፣ የኮሚቴውን መተዳደሪያ ደንብና ሁለቱን ምክረ ሐሳቦቹን በሚተገብረው ዓለም አቀፍ አማካሪ፣ ሚኒስትሮቹ ይፋዊ የሆነ ውይይት እያደረጉ ባይሆንም በጉዳዩ ላይ በቅርቡ በጋራ ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ለሦስቱ አገሮች ያቀረባቸው ሁለቱ ምክረ ሐሳቦች፣ አንደኛው ኃይድሮሎጂ ሲሙሌሽን ሞዴል ወይም ግድቡ በተለያዩ የዝናብ ወቅቶች እንዴት ይሞላል የሚለው ሲሆን፣ ሁለተኛው ግድቡ በሦስቱ አገሮች ላይ የሚኖረው አካባቢያዊና ማኅበራዊ ጉዳት ምንድነው የሚለው ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ከሴራ ፖለቲካ በስተጀርባ ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁ ኃይሎች

በመኮንን ሻውል ወልደ ጊዮርጊስ የአፄ ቴዎድሮስ መንግሥት የወደቀው ከመቅደላ በፊት...

ስለዘር ፖለቲካ

በሀብታሙ ኃይለ ጊዮርጊስ  ‹‹በቅሎዎች ዝርያችን ከአህያ ነው እያሉ ይመፃደቃሉ›› የጀርመኖች...

አማርኛ ተናጋሪዋ ሮቦት

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሳይንስ ሙዚየም፣ ሚያዝያ 2 ቀን...

ወዘተ

ገና! ከእናቴ ሆድ ሳለሁ፤ ጠላት ሲዝትብኝ ሰምቻለሁ። በዳዴ ዘመኔም፣ በ'ወፌ ቆመችም!'፤ አውዴ ክፉ ነበር...