Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትጎልቶ የወጣው የእግር ኳሱ የምርጫ ሽኩቻ

ጎልቶ የወጣው የእግር ኳሱ የምርጫ ሽኩቻ

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ ከወትሮው በተለየ ፍጥጫና ሽኩቻ እያስተናገደ ይገኛል፡፡ የምርጫው ውዝግብና ሽኩቻ በአቋምና ብቃት እንዲሁም ለእግር ኳሱ በሚያበረክተው አስተዋጽኦ ላይ ከመሆን ይልቅ ለውድድር በቀረቡት ላይም ሲያጠነጥን ታይቷል፡፡

ብዙዎቹ ዕጩዎች በተለይም ለፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንትነት ለሚወዳደሩ ግለሰቦች ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በአመራርነት ቦታው ላይ የነበሩና አሁንም ያሉ ግለሰቦች ዳግመኛ ለውድድር መቅረባቸው፣ ከሁሉም በላይ እግር ኳሱ በአሁኑ ወቅት በዓለም አገሮች የእግር ኳስ ደረጃ እጅግ በሚያስገርም ፍጥነት ለማሽቆልቆሉ ምክንያት ተደርገው የሚጠቀሱ አመራሮች ለውድድር መቅረባቸው አንደኛውና ዋነኛው መነጋሪያ ሆኗል፡፡ ከዚህ ቀደም በዲሲፕሊን ግድፈት ዕርምጃ የተወሰደባቸው ዕጩዎችም ለምርጫ ውድድሩ ብቅ ማለታቸው ሌላው አከራካሪ ጉዳይ ሆኖ እያነጋገረ ነው፡፡

በሌላ በኩል፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሒልተን ለሚያከናውነው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔና ምርጫ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን ገልጿል፡፡ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ጨምሮ ብዙዎቹ የክልልና የድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ዕጩዎቻቸውን እያሳወቁ ይገኛል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከነዚህ ዕጩዎች መካከል የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሥራ አስፈጻሚ ምርጫ ያቀረባቸው አቶ ኃይለኢየሱስ ፍሥሐ አንዱ ናቸው፡፡ ዕጩው በ2008 ዓ.ም. የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፌዴሬሽኑ የኦዲት ኮሚሽን አባል ሆነው እንዲያገለግሉ የመደባቸው ነበሩ፡፡

ይሁንና ግለሰቡ የተመደቡበትን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት አልቻሉም በሚልና፣ ኮሚሽኑንም በተጠናከረ የሰው ኃይል ማደራጀት ስለሚያስፈልግ አቶ ኃይለ ኢየሱስ ፍሥሐ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኦዲት ኮሚሽን አባልነት የተሰናበቱ መሆናቸው በደብዳቤ ቁጥር እ.ኤ.ፌ-አ.4/1276 በቀን 09/10/2009 ዓ.ም. በፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ ፊርማ የተሰናበቱ ናቸው፡፡

 ስለ ጉዳዩ የወከላቸው የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምን ይላል? የሚለውን ለማጣራት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

እግር ኳሱን ጨምሮ የተለያዩ የስፖርት ተቋማት አቅሙና ዕውቀቱ ባላቸው ባለሙያዎች መመራት እንደሚገባው ተደጋግሞ ሲነገር ቆይቷል፡፡ ይሁንና አሁንም ለብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አመራርነት ለመመረጥ ፍላጎቱና ተነሳሽነቱ እንዳላቸው እየተነገረላቸው ከሚገኙት መካከል አንዳንዶቹ፣ የአቅምና የክህሎት እጥረት  ያለባቸው ለመሆኑ ካለፈው አገልግሎታቸው ለመረዳት እንደማያዳግት የሚናገሩ አሉ፡፡

የዘርፉ ሙያተኞች እንደሚናገሩት ከሆነ፣ በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው እግር ኳሱ የበለጠ ችግር ውስጥ ከመግባቱ በፊት ዕጩዎችን የሚያቀርቡ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የሚያቀርቧቸው ዕጩዎች ከእግር ኳሱ ጋር ሊኖራቸው ስለሚገባው ሚናና ተግባር ግምት ውስጥ ትክክለኛውን ዕጩ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ክልሎች ያቀረቧቸው ዕጩዎችን አስመልክቶ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ዓርብ ምሽት (ጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ.ም.) ድረስ ፌዴሬሽኑ ዝርዝራቸውን በይፋ ባይገልጽም፣ ለፕሬዚዳንትነት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) ከደቡብ፣ አቶ ተካ አስፋው ከአማራ፣ አቶ አንተነህ ፈለቀ ከኦሮሚያ፣ አቶ ጁነዲን ባሻ ከድሬዳዋና አምባሳደር ቶፊቅ አብዱላሂ ከሐረሪ ክልል ተፎካካሪ መናቸው ታውቋል፡፡

ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት የታጩት አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከአማራ፣ አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ (ሥራ አስፈጻሚ የነበሩ) ከደቡብ፣ ኢንጂነር ቾል ቤል (የነበሩ) ከጋምቤላ፣ ወ/ሮ ሶፍያ አልማሙን ከቤኒሻንጉልና ጉሙዝ፣ አቶ አሊሚራህ መሀመድ ከአፋር፣ አቶ አብዱራዛቅ ሐሰን ከኢትዮ ሶማሌ፣ አቶ ታምራት በቀለ ከኦሮሚያ፣ አቶ አበበ ገላጋይ (የነበሩ) ከድሬዳዋና አቶ ተክለወይኒ አሰፋ (የነበሩ) ከትግራይ እንደሆኑ ሲነገር ሰንብቷል፡፡

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...