Tuesday, May 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፕሪሚየር ሊጉ ለባለ ፈርጣማ በጀት ክለቦች ከባድ ሆኗል

ፕሪሚየር ሊጉ ለባለ ፈርጣማ በጀት ክለቦች ከባድ ሆኗል

ቀን:

በአገሪቱ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች እንቅስቃሴ ላይ አስገራሚ የሚባሉ ክስተቶች መታየት ጀምረዋል፡፡ከፍተኛ በጀት የተመደበላቸው ክለቦች በደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ሲገኙ፣ በአንፃሩ ደግሞ በፕሪሚየር ሊጉ ውድድር የጎላ ስምና ዝና የሌላቸው ዝቅተኛ በጀት ያላቸው ቡድኖች የሊጉ ቁንጮ እየሆኑ መምጣታቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ክለቦች ከፍተኛ በጀት መድበው ውጤቱ በተቃራኒው እየሆነ ለመምጣቱ እንደምክንያት የሚነሳው ደግሞ፣ ቡድኖቹ አሠራራቸውን በመለወጥና ወደተሻለ የውጤት አቅጣጫ የሚወስዳቸውን የአደረጃጀት ክፍተት ያለባቸው በመሆኑ እንደሆነ የሚናገሩ አሉ፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ የዘንድሮው እንቅስቃሴ ይህንኑ እንደሚያመላክት እነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች ያክላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛው ሳምንት ጨዋታ ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ተከናውኗል፡፡ በሊጉ ከፍተኛ በጀት ያላቸውና ለሻምፒዮናው ቅድመ ግምት ተሰጥቶዋቸው የቆዩት ትልልቆቹ ቡድኖች በተጋጣሚዎቻቸው ብልጫ ተወስዶባቸው ሽንፈትን እያስተናገዱ ይገኛል፡፡ ወደ አርባ ምንጭ ያቀናው ቅዱስ ጊዮርጊስ በአርባ ምንጭ ከነማ 1ለ0 ሲሸነፍ፣ ቦዲቲ ስታዲየም ወላይታ ድቻን የገጠመው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና መብራት ኃይል በተመሳሳይ በወላይታ ድቻና በአዳማ ከነማ 1ለ0 ተሸንፈዋል፡፡ ፕሪሚየር ሊጉን በ23 ነጥብ እየመራ የሚገኘው ሲዳማ ቡና ወልዲያ ከነማን አስተናግዶ 1ለ0፣ ኢትዮጵያ ቡና መከላከያን 2ለ0፣ ዳሸን ቢራና ደደቢት 1ለ1፣ እንዲሁም ሙገር ሲሚንቶና ሐዋሳ ከነማ ያለግብ የተለያዩበት ውጤት ተመዝግቧል፡፡ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ የሚገኙትና ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው የሚገኙ የክለብ አመራሮች፣ ‹‹መንግሥት እግር ኳሱን ምክንያት በማድረግ እየባከነ ያለውን በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንዴትና በምን አኳኋን ግልጋሎት እየሰጠ መሆኑን ማጣራትና መስመር ማስያዝ ይጠበቅበታል፣›› በማለት የክለቦቻቸውን ማኔጅመንት ይወቅሳሉ፡፡ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥር 10 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲዮም ሊያከናውነው የነበረው የመከላከያና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ እንዲሁም የደደቢትና የአርባ ምንጭ ከነማ ጨዋታዎች ቅዳሜ ጥር 9 ቀን 2007 ዓ.ም. እንዲደረግ የፕሮግራም ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ እሑድ ጥር 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ሁሉም የክልል ጨዋታዎች በተያዘላቸው ፕሮግራም መሠረት ወልዲያ ላይ ወልዲያ ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ አዳማ ላይ አዳማ ከነማ ከዳሸን ቢራ፣ ሐዋሳ ላይ ሐዋሳ ከነማ ከመብራት ኃይል፣ ቦዲቲ ላይ ወላይታ ድቻ ከሙገር ሲሚንቶ፣ እንዲሁም ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና ይጫወታሉ፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ መሠረት ሲዳማ ቡና 23 ነጥብ ይዞ መሪነቱን እንዳስጠበቀ ሲሆን፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና በጎል ልዩነት ተበላልጠው በ18 ነጥብ ሁለተኛና ሦስተኛ ናቸው፡፡ ወላይታ ድቻና አርባ ምንጭ ከነማ በእኩል 17 ነጥብ በጎል ክፍያ ተበላልጠው አራተኛና አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ መከላከያ 16፣ አዳማ ከነማ 15፣ ደደቢት 14፣ መብራት ኃይል 13፣ ዳሸን ቢራ 13፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 12፣ ሙገር ሲሚንቶ 10፣ ሐዋሳ ከነማ በሰባትና እንግዳው ወልዲያ ከነማ በአምስት ነጥብ ከ1 እስከ 14 ያለውን ደረጃ ይዘው ይገኛሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመስቀል አደባባይ የመግቢያ ክፍያ ለምን?

ወጣቶች፣ ሕፃናትና አረጋውያን ሳይቀሩ መንፈሳቸውን የሚያድሱበት እንዲሁም ሐሳባቸውን በነፃነት...

በሕገ መንግሥቱ የተዋቀረው ‹‹የብሔር ፖለቲካ›› እና ‹‹ሥርዓቱ›› ያስከተለው መዘዝና መፍትሔው

(ክፍል አራት) በዓቢዩ ብርሌ (ጌራ) ባለፈው ጽሑፌ (በክፍል ሦስት) አሁን ያለው...

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብና የመንግሥት መሪ ምሥል

በበቀለ ሹሜ በ2015 ዓ.ም. መጋቢት ወር ውስጥ ይመስለኛል በ‹ሸገር ካፌ›...

ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ያደረገው አዋጅ የፍትሐዊነት ጥያቄ አስነሳ

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ስምንት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ተቋማዊና...