Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ልናገርለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ማሟላት ያለባቸው አነስተኛ መሥፈርቶች

ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ማሟላት ያለባቸው አነስተኛ መሥፈርቶች

ቀን:

በስንታየሁ ግርማ

ናሽናል ዲሞክራቲክ ኢንስቲትዩት የተባለ ተቋም ዲሞክራሲያዊ ተግባራትን ለማከናወን የፖለቲካ ፓርቲዎች ማሟላት ያለባቸው አነስተኛ መሥፈርቶች አስቀምጧል፡፡ እነዚህ መስፈርቶች ሰባት ሲሆኑ እነሱም፣ ለሰብዓዊ መብቶች ክበር መስጠት፣ ሕጋዊ ምርጫ መንግሥት የመመስረቻ ብቸኛ መንገድ መሆኑን መቀበል፣ ለምርጫ ሒደቶች ክብት መስጠት፣ ብጥብጥ ላለማስነሳት ቁርጠኛ መሆን፣ ለሌሎች ፓርቲዎችና ተወዳዳሪዎች ክብር መስጠት፣ መርሆዎችን፣ የፖሊሲ ፕሮፖዛሎችንና የተገኙ ውጤቶችን ኮሙኒኬት ማድረግ፣ የፖለቲካ ተሳትፎን ማበርታት፣ በኃላፊነት ማስተዳደር ናቸው፡፡ ኢንስቲቲዩቱ እንደሚለው ፖለቲካ ማለት በጋራ ለመኖር ኅብረተሰቡን የማደራጀት ሒደት ነው፡፡ በዲሞክራሲ ሥርዓት ውስጥ ዜጎች በፖለቲካ ጉዳዮችና ሒደቶች መሳተፍ አለባቸው፡፡ ዜጎች በሕዝባዊ ጉዳዮች ፍላጎቶቻቸውን ማንፀባረቅ አለባቸው፡፡ በምርጫ መሳተፍ አለባቸው፡፡ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት አብርሃም ሊንከን ዲሞክራሲ ማለት፣ “የሕዝብ መንግሥት በሕዝብ የተመረጠ ለሕዝብ የሚያገለግል፤” ብሏል፡፡ ይህንን ለማድረግ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ዲሞክራሲ እንዲያብብ ደግሞ ናሽናል ዲሞክራቲክ ኢንስቲቲዩት እንደሚለው ከላይ የተጠቀሱትን አነስተኛ መሥፈርቶች ፓርቲዎች ሊያሟሉ ይገባል፡፡ እነዚህ መሥፈርቶች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እያገኙ ነው፡፡ ምንም እንኳን እንደየአገሩ ተጨባጭ ሁኔታዎች የሚጨመሩ ቢኖሩም፣ ቲና ኦኔይል የተባሉ የአሜሪካ ኮንግረስ አፈ ጉባዔ” “All Politics is Local” ይላሉ፡፡ ለሰብዓዊ መብቶች ክብር መስጠት ኢንስቲቲዩቱ እንደሚለው በከፍተኛ ደረጃ ሁሉም ዲሞክራቲክ ፓርቲዎች ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ ተጠቃሚ ስለሚሆኑ እነዚህ ፓርቲዎች ድንጋጌዎችን ማክበር ይገባቸዋል፡፡ እነዚህ መብቶች በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ እነዚህ ድንጋጌዎች ለማክበር ፓርቲዎች በፆታ፣ በሃይማኖት፣ በዘርና በመሳሰሉት መመዘኛዎች ልዩነት ማድረግ የለባቸውም፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች በሥልጣን ላይ ያሉ ዲሞክራቲክ ፓርቲዎችና ለሌሎች ፓርቲዎች እነዚህ ዲሞክራሲያዊ ድንጋጌዎች እንዳይጥሱ በፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ገደብ ሊጥሉ ይችላሉ፡፡ ይህንን ሲያደርጉ ግን ሕጋዊ ሥርዓትን ተከትለውና ፓርቲዎች አቤት የማለት መብታቸውን አክብረው መሆን አለበት፡፡ ሕጋዊ ምርጫ ብቸኛ የመንግሥት መመሥረቻ ዘዴ መሆኑን መቀበል ዲሞክራቲክ ፓርቲዎች የሕዝቡ ፍላጎት ሊተገበር የሚችለው በሕጋዊ ምርጫ ብቸኛው የመንግሥት መመሥረቻ ዘዴ መሆኑን ሲቀበሉና ሲስማሙ ነው፡፡ በተጨማሪም በምርጫ መሸነፍን ለመቀበል የተስማሙ መሆን አለባቸው፡፡ በምላሹም ዲሞክራቲክ ፓርቲዎች ፍትሐዊ ምርጫ እንዲካሄድ መጠበቅ ይችላሉ፡፡ በሥልጣን ላይ ያለው ፓርቲ በእጁ ያለውን የመንግሥት ሀብት ከመጠን በላይ መጠቀም የለበትም፡፡ ዲሞክራቲክ ፓርቲዎች በአጠቃላይ ሚዛኑ ፍትሐዊ የሆነን ምርጫ መቀበል አለባቸው፡፡ የምርጫ ሒደቶችን ማክበር ፓርቲዎች የምርጫ ሂደቶችን ማለትም የመራጮች ምዝገባ ሕጎችን፣ የምርጫ ጣቢያ ሥነ ሥርዓቶችንና የመራጭነት የምዝገባ ሒደቶችን ማክበር አለባቸው፡፡ ኢንስቲትዩቱ እንደሚለው ዲሞክራቲክ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ሲወዳደሩ የአገሪቱን ሕጎችና ልምዶች መቀበል አለባቸው፡፡ በሕገወጥ የምርጫ ቅስቀሳ ድርጊቶች መሳተፍ አይገባቸውም፡፡ የተወዳዳሪዎቻቸውን የምርጫ ቅስቀሳዎች ማደናቀፍ የለባቸውም፡፡ ፓርቲዎች ደጋፊዎቻቸው በሁሉም የምርጫ ሒደቶች እንዲሳተፉ መቀስቀስ አለባቸው፡፡ ይህንንም ለተቀናቃኞች መፍቀድ ይኖርባቸዋል፡፡ የምርጫ ሒደቶችን ማክበር የሚለው አወዛጋቢ የምርጫ ውጤቶችን በተመለከተ አቤቱታቸውን ካቀረቡ በኋላ፣ ሕጋዊ አካላት የሰጡትን ውሳኔ መቀበልን ይጨምራል፡፡ ዲሞክራቲክ ፓርቲዎች በተወሰነ ሁኔታ ክፍተት ያለበት ቢሆን እንኳ በአጠቃላይ ሲመዘን ፍትሐዊ የሆነን የምርጫ ውጤት በመቀበል፣ ፍፁም ያልሆነውን የዲሞክራሲ ሥርዓት በኃይል ለመጣል መሞከር አይገባቸውም፡፡ ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ በሰላማዊ መንገድ ቅሬታቸውን መግለጽ ይችላሉ፡፡ ይህንን በማድረጋቸው ከረጅም ጊዜ አኳያ ዲሞክራሲያዊ መረጋጋት በመፍጠር የበለጠ ፍትሐዊ የምርጫ ውድድር ሥርዓት እንዲሰፍን ያደርጋሉ፡፡ ፓርቲዎች “ሕጉ ውጤቱን ይወስናል” የሚለውን መርህ መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡ ለሌሎች ፓርቲዎችና ለነፃ ውድድር ክብር ሊሰጡ ይገባል ሁሉም ዲሞክራቲክ ፓርቲዎች አባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው አስተያየቶቻቸውን በነፃ የመግለጽ መብት አላቸው፡፡ እነዚህ መብቶች ደግሞ ገዢው ፖርቲና የመንግሥት ተቋማት ማስከበር ግዴታቸው ነው፡፡ ለነፃ ውድድር ምቹ አካባቢም መፍጠር አለባቸው፡፡ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለዲሞክራሲ ውሳኔ አሰጣጥ ተገዢ መሆናቸውን ለሌሎች ፓርቲዎችና ሌሎች በማኅበረሰቡ ላይ ጥቅሞችን በማክበር ይገልጻሉ፡፡ ፓርቲዎች በተለይም በሥልጣን ላይ ያሉ ፓርቲዎች ሌሎች ወገኖችና ዜጎች በተናጠልም ሆነ በቡድን በሰላማዊ መንገድ የመቃወም መብት እንዳላቸው መቀበል ያስፈልጋቸዋል፡፡ ፓርቲዎች መቻቻልን ባህል ሊያደርጉት ይገባል፡፡ ወደ ግጭት ላለማምራት ቁርጠኛ መሆን በዲሞክራሲ ሥርዓት ውስጥ ያሉ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲዎች ብጥብጥን እንደ ፖለቲካ መሣሪያ መጠቀም የለባቸውም፡፡ ዲሞክራቲክ ፓርቲዎች ብጥብጥንና ሁከትን ማበረታታት የለባቸውም፡፡ የጥላቻ ንግግርም ተገቢ አይደለም፡፡ ፓርቲዎች ፕሮግራማቸውን ከብጥብጥ መንገዶች ውጪ መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ይህንን እንዳያደርጉ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ባሉ ሚዲያዎች ሐሳቦቻቸው የሚዲያ ሽፋን ሊያገኙ ይገባል፡፡ መርሆዎቻቸውን የፖሊሲ ፕሮፖዛላቸውንና ውጤቶቻቸውን “ኮሙኒኬት” ማድረግ አለባቸው ፓርቲዎች መርሆዎቻቸውን፣ የፖሊሲ አማራጮቻቸውንና የተገኙ ስኬቶቻቸውን ለአባሎቻቸው፣ ለደጋፊዎቻቸውና ለሌሎች ዜጎች “ኮሙኒኬት” ማድረግ አለባቸው፡፡ ሕጋዊ ዲሞክራቲክ ፓርቲዎች ሕዝቡ እንዴት እንደሚተሳሰር በዋና ዋና እሴቶችና መርሆዎች ላይ ስምምነት ሊደርሱ ይገባል፡፡ ውጤታማ ፓርቲዎች ጥልቅ ራዕይ በመንደፍ በሕዝቡ ውስጥ ሊያሰርፁ ይገባል፡፡ የፓርቲው ራዕይ መርሆዎች በሰነድ በማዘጋጀት በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡ እነዚህ ሰነዶች የፓርቲውን መለያ ለማወቅ ያስችላሉ፡፡ ምንም እንኳን ፕሮግራማቸውን ለማስተዋወቅ ሚዲያው ሚና ያለው ቢሆንም፣ ፓርቲዎች ዜጎች በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ለመስጠት እንዲችሉ መረጃ ማግኘት መቻላቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ ፓርቲዎችና መሪዎቻቸው የፓርቲውን መልዕክት በፕሬስ መግለጫዎች፣ በቃለ መጠይቅ፣ በሚዲያና በፓርቲ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ማስተላለፍ ይገባቸዋል፡፡ የፖለቲካ ተሳትፎን ማበረታታት ፓርቲዎች ፕሮግራሞቻቸውን ለማስፈጸም በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ሕዝቡ በስፋት እንዲሳተፍ ማድረግ አለባቸው፡፡ በአነስተኛ መሥፈርት ፓርቲዎች ደጋፊዎቻቸው በምርጫ ዕለት ድምፅ መስጠታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ ፓርቲዎች ሐሳባቸውን የሚቃወሙ ወገኖችን በመዋቅራዊ፣ በፖለቲካዊና በሌሎች ተመሳሳይ መሰናክሎች እንዳይገልጹ መገደብ አይገባቸውም፡፡ በታሪክም አጋጣሚ ተገቢውን ውክልናና ተሰሚነት ያላገኙ ለምሳሌ ሴቶች፣ ብሔሮችና ሌሎች አናሳ የኅብረተሰብ ክፍሎች ማሳተፍ ተገቢ ድጋፍ ያስገኛል፡፡ በኃላፊነት ማስተዳደር በምርጫ በተናጠልም ሆነ በጋራ መንግሥት የሚመሠርቱ ፓርቲዎች በኃላፊነት ማስተዳደር ይገባቸዋል፡፡ በምርጫ ወቅት ለማሳካት ቃል ከገቧቸው ግቦች መካከል የተወሰኑትን እንኳን በተግባር ማሳየት ይገባቸዋል፡፡ የፓርቲዎችን ግቦችና የአገሪቱን አጠቃላይ ጥቅም ማጣጣም ይኖርባቸዋል፡፡ በሥልጣን ያሉ ፓርቲዎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሐሳባቸውን የሚገልጹባቸውን መንገዶች ማመቻቸት ይኖርባቸዋል፡፡ በአገራችን ካሉ ፓርቲዎች ይህንን ስንቶቹ ያሟላሉ? ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...