Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናአቶ ብርሃኑ አዴሎ በቀረበባቸው ቅሬታ በድጋሚ ተነሱ

አቶ ብርሃኑ አዴሎ በቀረበባቸው ቅሬታ በድጋሚ ተነሱ

ቀን:

አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከአዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተርነት ኃላፊነታቸው በሕዝብ ቅሬታ ምክንያት እንዲነሱ ተደረገ፡፡ አቶ ብርሃኑ በሕዝብ ቅሬታ ምክንያት ከኃላፊነታቸው ሲነሱ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ላለፉት ስምንት ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ብርሃኑ፣ ታኅሳስ 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጻፈ ደብዳቤ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጻፈው ደብዳቤ አቶ ብርሃኑ ከኃላፊነታቸው የሚነሱበትን ምክንያት ባያብራራም፣ ከታኅሳስ 24 ቀን ጀምሮ መነሳታቸውን ይገልጻል፡፡ ተቋሙን በተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩም የተቋሙ የፓተንት ክፍል ዳይሬክተር አቶ ግርማ በጅጋ ተሹመዋል፡፡ አቶ ብርሃኑ በአሠራር ችግሮች ከሠራተኞች ቅሬታዎች ይነሱባቸው እንደነበር፣ ከተቋሙ ደንበኞች ማለትም የንግድ ምልክት የሚያወጡ ወይም ምልክቶቻቸው እንዲከበሩ የሚፈልጉ የንግድ ተቋማትና ግለሰቦች ቅሬታ ይቀርብባቸው እንደነበር ምንጮች አስረድተዋል፡፡ እነዚህ ቅሬታዎች በቀጥታ ለተወካዮች ምክር ቤት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት እንደቀረቡ ምንጮች አስረድተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ችግሮቹን የሚያጣራ ኮሚቴ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካይነት ተዋቅሮ የማጣራት ተግባራት ሲከናወኑ እንደነበሩ የሚያስታውሱት ምንጮች፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሯ ወ/ሮ ደሚቱ አንቢሳና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሩ አቶ አሚን አብዱልቃድር ከአጣሪ ኮሚቴ አባላቱ መካከል እንደነበሩም ገልጸው፣ ከኃላፊነት የተነሱትም ከዚሁ ጋር በተያያዘ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አቶ ብርሃኑ እስከ 1998 ዓ.ም. ድረስ የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትርና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ነበሩ፡፡ በወቅቱ ከተወለዱበት የደቡብ ክልል ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች አዲስ አበባ ድረስ በመምጣት በአቶ ብርሃኑ ላይ የተፈራረሙትን የቅሬታ አቤቱታ (ፔቲሽን) ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ማስገባታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የተቋቋመ አጣሪ ኮሚቴ ባቀረበባቸው ሪፖርት ከካቢኔ ጉዳይ ሚኒስትርነታቸውና ከኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲነሱ መደረጉም አይዘነጋም፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ አቶ ብርሃኑ አዴሎን ለማነጋገር በተደጋጋሚ የግል ስልካቸው ላይ በመደወል ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...