Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሽብርተኝነት ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩ ሁለት እንግሊዛውያን በጽኑ እስራት ተቀጡ

የሽብርተኝነት ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩ ሁለት እንግሊዛውያን በጽኑ እስራት ተቀጡ

ቀን:

– ከሁለት ዓመታት በላይ ታስረዋል

ጀመአተ ሙስሊም ጀሀድ አሸባሪ ቡድን በሚባል በህቡዕ ተደራጅቶ በሚንቀሳቀስ አሸባሪ ድርጅት ውስጥ፣ አባል ሆነው ‹‹በሸሪዓ የሚተዳደር እስላማዊ መንግሥት እንመሠርታለን›› የሚል ዓላማ ይዘው ሲንቀሳቀሱ መገኘታቸው ተገልጾ በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩ ሁለት እንግሊዛውያንና አንድ የሶማሊያ ዜጎች፣ በጽኑ እስራት እንዲቀጡ ጥር 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ተወሰነባቸው፡፡ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ከሁለት ዓመታት በፊት ኅዳር 25 ቀን 2005 ዓ.ም. የመሠረተውን ክስ ሲመረምር የከረመው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ ጽኑ እስራት የወሰነባቸው የእንግሊዝ ዜጐች፣ በቅጽል ስሙ አቡ ጠሊብ በሚል የሚጠራው ሚስተር አሊ አድሮስ መሐመድ፣ በቅጽል ስሙ መሐመድ አህመድ የሚባለው ሚስተር መሐመድ ሸሪፍ አህመድ ሁሴን፣ እንዲሁም የሶማሊያ ዜጋ ነው የተባለው አህመድ መሐመድ አልሚ ይባላሉ፡፡ ፍርደኞቹ የሃይማኖታዊ ‹‹አይዲዮሎጂ›› ዓላማ ለማራመድና በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር በማሰብ፣ እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ ተልዕኳቸውን በማስፋፋት ሲደራጁ ከቆዩ በኋላ፣ የመን ከሚገኘው የኦነግ ክንፍ ከሆነውና ራሱን የኦሮሚያ ነፃነት ኃይሎች ኅብረት (ኦነኃኅ) አመራሮች ጋር በመነጋገርና አብሮ ለመሥራት መስማማታቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ ዓሊ አድሮስ የተባለው አንደኛ ተከሳሽ ራሱ ቀደም ብሎ በህቡዕ የተደራጀው ቡድን አባል ከሆነ በኋላ፣ መሐመድ ሸሪፍን በመመልመልና አባል አድርጐ በ2004 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ መግባታቸው ተገልጿል፡፡ የጀምአተ ሙስሊም ጀሀድ ቡድን ሁለቱንም ባዘዛቸው መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በኋላ አዳማ ናዝሬት እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡ ተንቀሳቃሽ ስልክ ተገዝቶላቸው በሶማሊያና በየመን ካለው የህቡዕ ቡድን አባላት ጋር ሲደዋወሉ እንደነበር፣ መሐመድ ሸሪፍ ከቡድኑ አመራር ከሆነውና በውጭ ከሚገኘው አቡ ኢሣ መሐመድ 500 ዶላር መቀበሉን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አካቷል፡፡ ፍርደኞቹ የጀመአተ ሙስሊም ጀሀድ አሸባሪ ቡድን አባል በመሆን በህቡዕ በመንቀሳቀስ አባላትን ለመመልመል፣ ለማደራጀት፣ ወታደራዊ ሥልጠና ለመውሰድና በሸሪዓ የሚተዳደር እስላማዊ መንግሥት የመመሥረት ዓላማ በመያዝ፣ የሽብር ቡድኑን ዓላማና ተልዕኮ ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ በመሆኑም ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ በፍርደኞቹ ላይ የሰዎችና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦባቸዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ማስረዳቱን ፍርድ ቤቱ ጠቁሞ እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡ ተከሳሾቹ የዓቃቤ ሕግን ክስ ማስተባበል አልቻሉም በማለት ጥፋተኛ ብሎ ቅጣት ወስኖባቸዋል፡፡ ተከሳሾቹ አሸባሪ ድርጅትን ለመርዳት በማሰብ ከሚኖሩበት እንግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት፣ ከአሸባሪ ድርጅት ጋር ተቀላቀለው መንግሥትን ለመውጋት መንቀሳቀሳቸው ዓላማው ከባድ ቢሆንም፣ በዕቅድ የቀረና የደረሰ ጉዳት ስለሌለ የወንጀል ደረጃውን ፍርድ ቤቱ ዝቅተኛ ብሎታል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ተከሳሾች የወንጀል ሪከርድ ስለሌለባቸው፣ የቀድሞ ፀባያቸው መልካም እንደሆነ ስለሚታሰብ እንደ ቅጣት ማቅለያ ተይዞላቸዋል፡፡ በተለይ አንደኛ ተከሳሽ የካንሰር ሕመምተኛ መሆኑ ስለታወቀ እንደ ማቅለያ ተይዞለታል፡፡ ሁሉም የቤተሰብ ኃላፊ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ በመጨረሻ አንደኛ ተከሳሽ በአራት ዓመት ከስድስት ወራት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡ ሁለቱ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በአራት ዓመታት ከስምንት ወራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡ ፍርደኞቹ ከሁለት ዓመታት በላይ ታስረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...