Saturday, May 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ይድረስ ለሪፖርተርስለ ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማብራሪያ

ስለ ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማብራሪያ

ቀን:

ባለፈው እሑድ መጋቢት 17 ቀን 2009 ዓ.ም. በወጣው የአማርኛ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ኮርፖሬሽናችን ስለሚገነባው የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዘገባ ተላልፏል፡፡ በቅድሚያ የፓርክ ልማቱን በመጀመሪያ የጋዜጣ ገጽ ላይ በማኖራችሁና እየተደረገ ያለውን ጥረት በማጉላታችሁ፣ በኮርፖሬሽኑ ስም ምሥጋናዬን ለማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡ ይኸው እንደተጠበቀ ሆኖ በቀረበው ዘገባ ላይ የሚከተሉት እንዲታረሙ አሳስባለሁ፡፡

  1. የኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚገነባው 337 ሔክታር ላይ ሳይሆን በ279 ሔክታር መሆኑ፣ ግንባታውም በሁለት ምዕራፍ ሳይሆን በአንድ ጊዜ አሁን በተጀመረው አኳኋን ተገንብቶ መጋቢት 2010 ዓ.ም. ይጠናቀቃል፡፡
  2. በኢንዱስትሪ ፓርኩ በዋነኛነት የፋርማሲቲዩካልና የፋርማሲቲዩካል መሣሪያዎችን በማምረት ፓርኩ የፋርማሲዩቲካል ማዕከል (HUB) ሆኖ እንዲያገለግል ታቅዶ እየተሠራ ያለ በመሆኑ፣ በእርምት መልክ ለክቡራን የጋዜጣው ደንበኞች ዳግም ግልጽ ሆኖ በሚታይ የጋዜጣ ክፍል ላይ እንዲወጣ እንጠይቃለን፡፡

(ሲሳይ ገመቹ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...