Monday, February 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅደምቢ ዶሎ ከ80 ዓመታት በፊት

ደምቢ ዶሎ ከ80 ዓመታት በፊት

ቀን:

ድንጋይ ዳቦ ሳለ!

ያኔ ድሮ ያኔ – ድንጋይ ዳቦ ሳለ፤

ህዝበ ዓዳም በላቡ አንዳች ጥርብ ድንጋይ እያንከባለለ፤

በወዙ በደሙ እየተማማለ፤ 

መርዌን አንጸ አክሱምን ተከለ፡፡

መጫኛና ጠፍር- ቋንጣ ፍርፍር ሳሉ፡፡

አባቶች በህብረት እየተማማሉ፤

ቱርክን አሳፈሩ፤ ግብጽን አኮሰሙ፤

ጥልያንን አዋርደው ከግራቸው ስር ጣሉ፤

ያኔ

እሾህ ምግብ ሳለ እሸት የሚበላ፤

ሮሃን ገነቡ እነ ይምርሃነ እነ ላሊበላ፡፡

ያኔ

ሁሉ ሙሉ በነበረ ጊዜ፤

ያላንዳች መስገብገብ ያላንዳች አባዜ፡፡

ፋሲልን ገነቡ፤ መቀሌን አስዋቡ፤

አንዳቸው ላንዳቸው ዕየተሳሰቡ፡፡

ያኔ

በነበረ ግዜ ዐፈር መልካም ሽሮ፤

ህዝብ ተሰባስቦ ባንድ ተመካክሮ፤

ታሪክ ሰርቶ አለፈ ድንበር አስከብሮ፡፡

ዛሬ

ዳቦ ድንጋይ ሆኖ ጊዜ ተቀይሮ፤

አዳሜ ተንጫጫ ጠጠረበት ኑሮ፤

ላይስማማ ምሎ፤

ሊጠፋፋ ቆርጦ- ሊያርፈው ተዘናጥሎ፤

ለዛው ሙጥጥ ብሎ- ጠፍቷል ተመናቅሮ፡፡

ዛሬ

ዳቦ ድንጋይ ሆኖ፤

ልቡን አልሰጥ ብሎ፤

ተቃጥሎና ከስሎ፤

ጥቁር ዓለት ወጣው ያለመጠን አርሮ፤

እናም

ዓዳም አያ ጅሎ…..

ችግር አቆራምዶት ያለቅጥ ተርቦ፤

ወንድሙን ያጠፋል ለእንጀራ ለዳቦ፡፡

  • (ጥላሁን ጎሹ ገጽ ላይ የተገኘ)
  •  

የካምቦዲያ እናት የጡት ወተት ሽያጭ

ካምቦዲያ ውስጥ የሚገኝ አምቦሮሲያ የሚባል ኩባንያ ነው፡፡ የእናቶች ጡት ወተትን እያጠራቀመ ለአሜሪካውያን ይሸጣል፡፡ ካምፓኒው የጡት ወተቱን የሚሰበስበው ከደሀ ካምቦዲያዊያን ሲሆን ገዢዎቹ ደግሞ ልጆቻውን የጡት ወተት መመገብ ያልቻሉ አሜሪካውያን እናቶች ናቸው፡፡ ወተቱ ካምቦዲያ ውስጥ ተሰብስቦ በላብራቶሪ ፍሪጅ ውስጥ ይቀመጥና በመጨረሻ ወደ አሜሪካ ይላካል፡፡ ይህ ወተት አሜሪካ ውስጥ ፓስቸራይዝድ ሆኖና ታሽጎ 147 ሚሊ ሊትሩ በሀያ ዶላር ይሸጣል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት አድን ድርጅት የሆነው ዩኒሴፍ ግን ለእናት ጡት ወተት ሲባልና ለገበያ ደሃ እናቶችን መበዝበዝ ተገቢ አይደለም በማለት የኩባንያውን ሥራ ማውገዙን የኤኤፍፒ ዘገባ ያመለክታል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይም የካምቦዲያ መንግሥት ይህን የእናት ጡት ወተት ንግድ ለጊዜውም ቢሆን እንዲቆም ማድረጉን ገልጿል፡፡

                        *********************

የ100 ፈሪ ዓመት አዛውንቷ በፈቃደኝነት እስር ቤት ገቡ

የ99 ዓመቷ የዕድሜ ባለፀጋ ኔዘርላንዳዊቷ ወ/ሮ አኒ፣ 100ኛ ዓመታቸውን ለመድፈን ጥቂት ቀርቷቸዋል፡፡ እኚህ አዛውንት በዚህ ዕድሜዬ የምፈልገው ያሉት ነገር የእስር ቤት ልምድ በመሆኑ፣ በፈቃደኝነት እስር ቤት መግባታቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡ አዛውንቷ ከእስር ቤት ለመግባት የሚያስችል ምንም ሪከርድ የሌለባቸው ቢሆንም፣ ፖሊስ እሳቸውን ከእስር ቤት ለማስገባት በመተባበር መሥራቱን አስታውቋል፡፡ የአዛውንቷ አካባቢ ነዋሪዎችም ፖሊስ ይህን ትብብር በማድረጉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

                        *********************

እንደ ሻንጣ ተጭኖ ከመንገደኞች ጋር በአውሮፕላን የተጓዘው እባብ

በአላስካ አየር መንገድ በረራ ላይ የተገኘውን እባብ በመመልከታቸው፣ መንገደኞችም ሆኑ የበረራ አስተናጋጇ አልተደናገጡም፡፡ ይልቁንም የበረራ አስተናጋጇ እባቡን አፈፍ አድርጋ በመያዝ የሻንጣ  ማስቀመጫ ውስጥ ከትታ ዘጋችበት፡፡ ብዙ ጊዜ እንደ አይጥ፣ እባብና ሌሎችም መሰል እንስሳት አውሮፕላን ውስጥ ሲገኙ መጯጯህና መደናገጥ የሚፈጠር ቢሆንም፣ ይህኛው ጉዞ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ በሰላም ቀጥሏል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...