Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየተሽከርካሪዎች የ100 ሺሕ ሰዎች ድርሻ ስምንት ቢሆንም የሚደርሰው አደጋ አሳሳቢ ነው ተባለ

የተሽከርካሪዎች የ100 ሺሕ ሰዎች ድርሻ ስምንት ቢሆንም የሚደርሰው አደጋ አሳሳቢ ነው ተባለ

ቀን:

በኢትዮጵያ ያሉት ተሽከርካሪዎች ከ700 ሺሕ ብዙም ያልዘለሉና የ100 ሺሕ ሰዎች ድርሻም ስምንት ተሽከርካሪ ቢሆንም፣ የሚደርሰው የትራፊክ አደጋ ግን አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በአገር አቀፍ የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት የሕዝብ ግንዛቤና ንቅናቄ መፍጠሪያ ዕቅድ ዙሪያ ‹‹አገር አቀፍ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሃይማኖት መሪዎች ሚና›› በሚል ርዕስ መጋቢት 14 ቀን 2009 ዓ.ም. በተካሄደው የምክክር መድረክ ላይ እንደተገለጸው፣ የተሽከርካሪው ቁጥርና የትራንስፖርት ፈላጊው ጥመርታ ባይጣጣምም፣ ባለው ተሽከርካሪ የሚደርሰው አደጋ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል፡፡

ዓምና ብቻ 4,351 ዜጎች በትራፊክ አደጋ ለሕልፈተ ሕይወት ሲዳረጉ፣ ከ12 ሺሕ የሚበልጡት ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙም ተነግሯል፡፡

ለእነዚህ አደጋዎች መከሰት የተለያዩ ምክንያቶች ቢጠቀሱም፣ ዋና ዋናዎቹ ለእግረኛና ለተሽከርካሪ ቅድሚያ አለመስጠት፤ በሕግ ከተወሰነ ፍጥነት በላይና በቂ ርቀትን ተከትሎ ያለማሽከርከር በግንባር ቀደም የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ከሚደርሱ አደጋዎች የእነዚህ ውስጥም በመቶኛ ሲሰላ 60.3 መቶኛውን ይሸፍናል፡፡

የአሽከርካሪው ስህተት፣ የእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ያለመዳበር፣ የተሽከርካሪው የቴክኒክ ብቃት መጓደል፣ የመንገድ ሁኔታና ሌሎችም ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው አሽከርካሪው ሲሆን፣ ይህም በመቶኛ ሲሰላ 85.9 በመቶ ነው፡፡

በአብዛኛው ሰው ሠራሽ የሆነን ችግር ከመቅረፍ አኳያ መንግሥት የተለያዩ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ነው፡፡ ከሥራዎቹም መካከል በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በ10,000 ተሽከርካሪ የሚደርሰውን የ65 ሰዎች ሞት ወደ 27 ዝቅ ለማድረግ ስትራቴጂካዊና የመንገድ ደኅንነት የአሥር ዓመት የተግባር ዕቅድ ተቀርጾ ወደ ሥራ መገባቱ ይገኝበታል፡፡

ዘመናዊ የብዙኃን ትራንስፖርት ማስገባት፣ የመፈጸም አቅምን መገንባት ሕጎችን የማውጣትና የማሻሻል፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የመዘርጋት፣ ማዕከላዊ የመረጃ ቋት እንዲገነባ የፋይናንስ ድጋፍ የማመቻቸት ተግባር መከናወኑ ችግሩን ለመቅረፍ ከተወሰዱ ዕርምጃዎች ይገኙበታል፡፡

ከዚህም ሌላ ‹‹ከትራፊክ አደጋ የፀዳ የትራንስፖርት አገልግሎት ለአገራዊ ህዳሴ›› በሚል መሪ ቃል ሕዝቡን ያሳተፈ አገራዊ ንቅናቄ በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ከጥር 22 ቀን እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

በአገር አቀፍ ንቅናቄ ብሔራዊ ኮሚቴ ተዘጋጅቶ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ኅብረት ጋር በመተባበር በቀረበው በዚሁ መድረክ ላይ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሸዲ፣ የመንገድ ትራፊክ ደኅንነትን በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ለማስገባት የሚያስችል ሥራ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ለማከናወን በዝግጅት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት ከሙስና የፀዳ እንዲሆንና ሥልጠና የሚሰጡ ተቋማትም ሠልጣኞቻቸውን በሥነ ምግባር፣ በክህሎትና በትምህርት አንጸው እንዲያወጡ ለማድረግ የሚያስችል የቁጥጥር ሥራ በመንግሥት በኩል መሠራት እንደሚኖርበት አሳስበዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...