Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየጣሊያን መንግሥት የ15 ሚሊዮን ዩሮ ብድር በዓለም ባንክ በኩል ለሥራ ፈጣሪ ሴቶች...

የጣሊያን መንግሥት የ15 ሚሊዮን ዩሮ ብድር በዓለም ባንክ በኩል ለሥራ ፈጣሪ ሴቶች አቀረበ

ቀን:

በኢትዮጵያ አነስተኛና ጥቃቅን የሥራ መስኮች ለተሰማሩ ከ20 በላይ ሥራ ፈጣሪ ሴቶች የሚውል የ15 ሚሊዮን ዩሮ (በወቅቱ ምንዛሪ ከ465 ሚሊዮን ብር በላይ) ብድር በዓለም ባንክ በኩል ያቀረበው የጣሊያን መንግሥት፣ በቴክኒክና በሥልጠና መስክም ድጋፍ መስጠት እንደሚፈልግ አስታወቀ፡፡

የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ የአዲስ አበባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጂኔቭራ ሊቲዚያ በኢትዮጵያና በደቡብ ሱዳን የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ከሆኑት ካሮሊን ተርክ ጋር ሰኞ ጥቅምት 20 ቀን 2010 ዓ.ም. ባደረጉት ስምምነት ወቅት እንደተናገሩት፣ የጣሊያን መንግሥት ለኢትዮጵያ የሥራ ፈጣሪ ሴቶች የልማት ፕሮግራም ድጋፍ እንዲውል የሰጠው የ15 ሚሊዮን ዩሮ ከሁለት ዓመት በፊት በኢትዮጵያና በጣሊያን መካከል በተደረሰው የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት አማካይነት የቀረበ ድጋፍ ነው፡፡

ዳይሬክተሯ ካሮሊን እንደገለጹት፣ የጣሊያን መንግሥት ያቀረበው ብድር አዲስ አበባን ጨምሮ በድሬዳዋ፣ በመቐለ፣ በሐዋሳ፣ በባህር ዳር፣ እንዲሁም በአዳማ ለሚገኙ 20 ሺሕ ሴቶች የሚሰጥ ነው፡፡

ከአምስት ዓመት በፊት በተጀመረው ሴት የፈጠራ ሴቶች የሚደገፉበት የልማት ፕሮግራም ከ58 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር የዓለም ባንክን ጨምሮ ከካናዳ፣ ከእንግሊዝ በቅርቡም ከጃፓን መንግሥት የተሰጠውን የ50 ሚሊዮን ዶላር ብድር ማግኘት የቻለ ፕሮግራም ነው፡፡

እንደ ዓለም ባንክ ጥናት ከሆነ በነፍስ ወከፍ በአማካይ ከሚቀርበው የ240 ሺሕ ብር ብድር በመነሳት ከ12 ሺሕ በላይ ሴቶች የብድር ተጠቃሚ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ብድር የወሰዱት 52 በመቶ ሲሆኑ፣ 79 በመቶ የብድሩ ተጠቃሚዎች የገቢ መጠናቸው መጨመሩን፣ 68 በመቶዎቹ ሌሎች የሥራ ዕድል መፍጠር የቻሉበት፣ የሚወስዱት የብድር መጠን እያደገ መጥቶ 800 በመቶ የጨመረበት አካሄድ እንደተመዘገበ የዓለም ባንክ ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል፡፡

የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ በዓለም ባንክ ተቆጣጣሪት ለኢትዮጵያ መንግሥት ያቀረበው ብድር ዝቅተኛ ወለድ የሚታሰብበትና በ40 ዓመታት ውስጥ የሚከፈል እንደሆነ ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...