Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበነቀምቴ ከተማ ሦስት ሰዎች ተገደሉ

በነቀምቴ ከተማ ሦስት ሰዎች ተገደሉ

ቀን:

  • ሁለት ባጃጆች ሙሉ በሙሉ ሲቃጠሉ በአንድ ሆቴል ላይ ጉዳት ደርሷል

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ወርቁ ጫላ ማክሰኞ ጥቅምት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ እሑድ ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. በከተማዋ የኢሬቻ በዓል ሲከበር ቦምብ ይዘው የመጡ ወጣቶች አሉ በሚል ሰበብ በተነሳው ግጭት ሁለት ሰዎች ሞተዋል፡፡ ሟቾችም በእውቀቱ ውበት ሙሉጌታ፣ ደገባስ ፈቃደ ካባና ኤርሚያስ ባዩ ምትኬ እንደሚባሉ ገልጸዋል፡፡

ደገባስ ፈቃደ ካባ ሕይወታቸው ሊያልፍ የቻለበት ምክንያትም እሑድ በነበረው የኢሬቻ በዓል ለመዋኘት ወደ ወንዝ ገብተው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ከቀሪዎቹ ሁለቱ ሟቾች መካከል አንደኛው የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ፣ ሁለተኛው ደግሞ ጉዳት የደረሰበት ሆቴል ሥራ አስኪያጅ እንደነበር አቶ ወርቁ ገልጸዋል፡፡  

የዩኒቨርሲቲው ተማሪ በኢሬቻ በዓል ላይ ድብደባ ደርሶበት ወደ ሆስፒታል ከሄደ በኋላ በማግሥቱ ሕይወቱ እንዳለፈ ገልጸዋል፡፡ ሁለተኛው ሟች ደግሞ ሁከቱ በተፈጠረበት ዕለት በድንጋይ ተደብድቦ ሕይወቱ ሊያልፍ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በግጭቱ አሥር ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበርና ከእነዚህ መካከል ስድስቱ የሕክምና ዕርዳታ አግኝተው ወደ ቤታቸው እንደተመለሱ ገልጸዋል፡፡ አራቱ ሰዎች ግን ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው በመሆኑ፣ በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል በሕክምና ላይ እንደሚኙ ጠቁመዋል፡፡

በዕለቱ ተነስቶ በነበረው ግጭትም ሁለት ባጃጆች ሙሉ በሙሉ እንደተቃጠሉና በአንድ ሆቴል ላይ የመሰባበር ጉዳት እንደደረሰ ገልጸዋል፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰበትን ምክንያት አስመልክቶም አቶ ወርቁ፣ ‹‹በበዓሉ ላይ አደጋ ለማድረስ የመጡ ሰዎች አሉ በሚል ጥርጣሬ ሰዎች እየተፈተሹ ነበር፡፡ በዚህ ሒደት ቦምብ ይዘው ተገኝተዋል ተብሎ ግጭት ተነስቶ ነው ድብደባው ሲካሄድ የነበረው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ግጭቱ በተፈጠረበት ወቅት የከተማዋ ፖሊስ ከዚህ በላይ በንብረትና በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ሥራ ማከናወኑንና ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር እያዋለ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በተለያዩ ብሔሮች ተወላጆች ላይ ጉዳት መድረሱንም አክለዋል፡፡

በዚህ ግጭት እጃቸው አለበት የተባሉ 16 ሰዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም አቶ ወርቁ አስረድተዋል፡፡

የነቀምቴ ከተማ ፖሊስ መምርያ ኃላፊ ኮማንደር ጌታቸው ኢታና እንዳሉት፣ ግጭቱን ከለላ በማድረግ የግለሰቦችን ሱቆችና መጋዘኖችን የዘረፉ ግለሰቦች አሉ፡፡ ፖሊስ ከኅብረተሰቡ ጋር ባደረገው የጋራ ጥረት ከተማው ተረጋግቷል ብለዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተቀሰቀሰው ግጭት የ33 ሰዎች ሕይወት እንዳለፈና ከ256 በላይ ተጠርጣሪዎች ደግሞ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ከክልሉ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...