Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበቅርስነት የተመዘገቡ ሕንፃዎች መፍረስ ቅሬታ አስነሳ

በቅርስነት የተመዘገቡ ሕንፃዎች መፍረስ ቅሬታ አስነሳ

ቀን:

 

  • ሕንፃዎቹ እንዲፈርሱና እንዲታሸጉ ያዘዙት ኃላፊ ታስረው ተፈቱ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት በተለምዶ ካዛንችስ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ከ80 ዓመታት በፊት በፋሽስት ጣሊያን እንደታነፁና በቅርስነት እንደተመዘገቡ የተገለጹ ሕንፃዎች መፍረስ ቅሬታ አስነሳ፡፡  

ከካዛንችስ ቶታል ዝቅ ብሎ በፊት ለፊት በፋሽስት ጣሊያን ወረራ ጊዜ ከ80 ዓመታት በፊት የታነፀውና የዘመኑን ኪነ ሕንፃ ገጽታ አመላካች የነበረው ሕንፃ በቅርስነት የተመዘገበ ቢሆንም፣ በክፍለ ከተማው የመሬት ልማት ባንክና ከተማ ማደስ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ትዕዛዝ እንዲፈርስ መደረጉን ሪፖርተር ያገኛቸው ሰነዶች ያመለክታሉ፡፡

- Advertisement -

የቂርቆስ ክፍል ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት፣ የቱሪዝም ልማትና ቅርስ አስተዳደር ዋና የሥራ ሒደት አስተባባሪ አቶ ኩሩ ተስፋዬ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በክፍለ ከተማው ውስጥ በቅርስነት የተመዘገቡ 45 የተለያዩ ታሪካዊ ሕንፃዎችና የእምነት ተቋማት አሉ፡፡ እነዚህን ቅርሶች የመጠበቅና ታሪካዊነታቸውን የማስቀጠል ኃላፊነት ለቅርስና ጥናት ባለሥልጣን የተሰጠ ቢሆንም፣ ሕንፃዎቹ ሲፈርሱ ምንም ዓይነት ዕርምጃ አለመወሰዱን ገልጸዋል፡፡

ጽሕፈት ቤቱ ስለጉዳዩ ለሚመለከተው ባለሥልጣን ከመግለጽ ባለፈ ምንም ማድረግ የሚችለው እንደሌለና ሥልጣኑም እንዳልሆነም አክለዋል፡፡

በአፍራሽ ግብረ ኃይል የፈረሰው ሕንፃ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን፣ የዱር አራዊት ሙዚየምና እስከፈረሰበት ጊዜ ደግሞ የግብርና አዳራሽ ጽሕፈት ቤት ሆኖ ማገልገሉንና አሠራሩ ረቀቅ ያለ ለትውልዱ አስተማሪ የነበረ ሕንፃ እንደነበር አቶ ኩሩ ተናግረዋል፡፡

የክፍለ ከተማው መሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽሕፈት ቤት ሌላውን በቅርስነት የተመዘገበውን ከካዛንቺስ ቶታል አጠገብ የሚገኘውን ታሪካዊ ሕንፃ ለማፍረስ ማሸጉን አቶ ኩሩ አስረድተዋል፡፡ የሕንፃው አካል ቤቶች በመታሸጋቸው የሚያስተዳድረው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጉዳዩን ወደ ሕግ መውሰዱም ታውቋል፡፡

ጉዳዩ በክርክር ላይ እያለ የመሬት ልማት ባንክና ከተማ ማደስ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት በማሸጉ ኃላፊው ሰኞ ጥቅምት 20 ቀን 2010 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው የታሸገበትን ምክንያት ማስረዳት ባለመቻላቸው፣ ግማሽ ቀን ታስረው መፈታታቸው ታውቋል፡፡ ያሸጓቸውን የንግድ ቤቶችና በቅርስነት የተመዘገበውን ሕንፃ እንዲከፍቱ ትዕዛዝ መሰጠቱም ተገልጿል፡፡

መሥፈርቱን ማሟላቱና የከተማውን ማስተር ፕላን እንደማያደናቅፍ፣ እንዲሁም ለ80 ዓመታትን የቆየው ታሪካዊ ሕንፃ አስተማሪነቱ ከግምት ውስጥ ገብቶ በቅርስነት መመዝገቡ እየታወቀ እንዲፈርስ ማድረግ፣ ታሪክን ማጥፋት መሆኑንም በአካባቢው ረዥም ዕድሜ መኖራቸውን የገለጹት አቶ ሥዩም የኋላሸት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...